የአሦር ነገሥታት ዝርዝር

ከውክፔዲያ
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎች, ፍለጋ

የአሦር ነገሥታት ዝርዝር ከብዙ ቅርሶች ተገኝቷል። ከነዚህ ዋንኛው እራሱ «የአሦር ነገሥታት ዝርዝር» የተባለው ጽሑፍ ነው። ይህ ጽሑፍ ከ3 ቅጂዎች ሲታወቅ፣ ከ2 ሳርጎን አስቀድሞ (ወይም እስከ 730 ዓክልበ. ድረስ) የነገሡትን ነገሥታት ይዘረዝራል። ከ1 ኤሪሹም ጀምሮ ሰነዱ ለያንዳንዱ ንጉሥ የዘመኑን አመታት ቁጥር ይሰጣል። ስለዚህ ዝርዝሩ የተቀናበረው በ2 ሳርጎን ዘመን እንደ ሆነ ይታመናል።

በአሦራዊው መቆጠሪያ፣ እያንዳንዱ አመት በሊሙ (ሹም) ስም ይባል ነበር። ለአንዳንድ ንጉስ ዘመን፣ እነዚህን የአመት ስሞች የሚዘርዝሩ ተጨማሪ ዜና መዋዕሎች ተገኝተዋል። በተለይም በቅርብ ጊዜ (በ1995 ዓ.ም.) በካነሽ ፍርስራሽ (በዛሬው ቱርክ አገር) ከ1 ኤሪሹም እስከ አሹር-ዱጉል ድረስ የነበሩት የአመት ስሞች ተገኝተዋል። የአመት ስም ዝርዝሮች በብዛት ከዋናው የነገሥታት ዝርዝር ጋር ይስማማል። ከሺህ አመት በላይ አሦራውያን የአመቶችን ቁጥር በደንብ ስለ ለዩ፣ እነዚህ ቅርሶች የጥንታዊ ዘመን ታሪክና ዕድሜ መጠን ለማወቅ እጅግ ይረዳናል።

ከ1 ኤሪሹም አስቀድሞ [ለማስተካከል]

  • «በድንኳን የኖሩ 17 ነገስታት»፦ ቱዲያ፣ አዳሙ፣ ያንቂ፣ ሳሕላሙ፣ ሐርሐሩ፣ ማንዳሩ፣ ኢምሱ፣ ሃርሱ፣ ዲዳኑ፣ ሃኑ፣ ዙአቡ፣ ኑአቡ፣ አባዙ፣ ቤሉ፣ አዛራህ፣ ኡሽፒያ፣ አፒያሻል።
  • «አባቶቻቸው የታወቁት 10 ነገሥታት»፦ አፒያሻል የኡሽፒያ ልጅ ነበር፣ ሐሌ የአፒያሻል ልጅ፣ ሳማኒ የሐሌ ልጅ፣ ሐያኒ የሳማኒ ልጅ፣ ኢሉ-መር የሐያኒ ልጅ፣ ያክሜሲ የኢሉ-መር ልጅ፣ ያክሜኒ የያክሜሲ ልጅ፣ ያዝኩር-ኢሉ የያክሜኒ ልጅ፣ ኢላ-ካብካቡ የያዝኩር-ኢሉ ልጅ፣ አሚኑ የኢላካብካቡ ልጅ።
  • «የአመት ስም ቁጥር የማይታወቅላቸው፣ ስሞቻችውም በጡብ የሚገኙ 6 ነገሥታት»፦ ሱሊሊ የአሚኑ ልጅ፣ ኪኪያ፣ አኪያ፣ 1 ፑዙር-አሹር፣ ሻሊም-አሁም፣ ኢሉሹማ

የአሦር ነገሥታት ከ1 ኤሪሹም እስከ አሦር ውድቀት (እስከ 617 ዓክልበ.) ድረስ [ለማስተካከል]