ሃይማኖት
Appearance
(ከሀይማኖት የተዛወረ)
ሃይማኖት አንድ ሕብረተሠብ የሚያምንባቸው ጽኑ እምነቶች መሠረት ነው። በዓለም ውስጥ በርካታ ልዩ ልዩ ሃይማኖቶች አሉ።
ዋና ዓለማዊ ሃይማናቶች ክርስትና፣ እስልምና፣ አይሁድና፣ የሕንዱ ሃይማኖት እና ቡዲስም ናቸው። እነዚህ ሃይማኖቶች በአንዳንድ አገር በይፋ የመንግሥት ሃይማኖት ሁኔታ አላቸው። ከነዚህ መጀመርያ ሦስቱ. ክርስትና፣ እስልምናና አይሁድና፣ ሁላቸው ከአብርሐም ስለ ተነሡ፣ «አብርሃማዊ ሃይማኖቶች» ተብለዋል። ሒንዱኢዝምና ቡዲስም ግን ከሕንድ ተነሡና «ሕንዳዊ» ወይም «ዳርማዊ ሃይማኖቶች» ተብለዋል።
ሌሎች ሃይማኖቶች በአሁኑ ሰዓት በየትም አገር የመንግሥት ሃይማኖት ባይሆኑም፣ ባለፉት ዘመናት በታሪክ መንግሥታት ይኖራቸው ነበር፦ በተለይ ዛርጡሽና፣ ጃይኒስም፣ ሲኪስም፣ ዳዊስም፣ የኮንግ-ፉጸ ትምህርት፣ ሺንቶና የተለያዩ ኗሪ ወይም አረመኔ ሃይማኖቶች የቀድሞ መንግሥታት ነበሯቸው፤ የጠፉት ሃይማኖቶች ማኒኪስም እና አሪያኒስም ደግሞ የቀድሞ መንግስታት ነበሯቸው።
በተጨማሪ መቸም መንግስት ያልነበረላቸው በርካታ ሌሎች አነስተኛ ሃይማኖቶች ወይም እምነቶች አሉ ወይም በታሪክ ተገኝተዋል።
በአንዳንድ አስተሳሰብ ማርክሲስም-ሌኒኒስም በሃይማኖት ፈንታ የአንዳንድ መንግሥት ፍልስፍና፣ ትምህርት ወይም ርዕዮተ ዓለም በመሆኑ በውኑ እንደ አንድ ሃይማኖት መቆጠሩ ተገቢ ነው።