ሚስኪቶ

ከውክፔዲያ


የሚስኪቶ አገር (ቀይ)

ሚስኪቶማዕከል አሜሪካ የሚኖር ብሔር ነው። መሬታቸው ከካሜሮን ርእሰ ምድር ሆንዱራስ ጀምሮ እስከ ሪዮ ግራንዴ ወንዝ ኒካራጓ ድረስ ይዘረጋል። የራሳቸው ሚስኪቶ ቋንቋ አለ። ነገር ግን የእስፓንኛ እና የሚስኪቶ እንግሊዝኛ ፓቷ ተናጋሪዎች በትልቅ ወገን ይገኛሉ። የሚስኪቶ እንግሊዝኛ ፓቷ የመጣ ከእንግሊዞች ጋራ ብዙ ጊዜ በማገናኘታቸው ነበር። ብዙዎቹ ክርስቲያኖች ናቸው።

በጊዜ ላይ ያመለጡ ባርዮች ከነሱ ጋር ስደት ስላገኙ ዘራቸው ተደባልቆ ክልስ ሆነ። መሬታቸውን ለመድረስ አስቸጋሪ በመሆኑ እስፓንያውያን ሰፊ አገሩን ሲወረሩ ለሚስኪቶዎቹ ብዙ ውጤት አልነበረም።

የሚስኪቶ ባሕላዊ ኅብረተሠብ በጣም የተደራጀ ነውና የተወሰነ ፖለቲካዊ ሥራዓት አለው። ንጉስ ቢኖሯቸውም ሙሉ ሥልጣን ግን አልነበራቸውም። ከነገስታታቸው ብዙዎች የሚታወቁ ከአፈታሪክ ስለሆነ የነሱ ታሪካዊ መረጃ ሁልጊዜ ግልጽ አይደለም። መንግሥታቸው ከ1617 ዓ.ም. በፊት ጀምሮ በታሪኩ መጀመርያ የተመዘገቡት ንጉሳቸው ኦልድማን ነበሩ። በአባታቸው ዘመን ከእንግሊዞች ተገናኝተው ኦልድማን ወደ እንግሊዝ አገር ተልከው ከእንግሊዝ ንጉስ ከ1ኛ ቻርልስ ጋር ተዋወቁ። በ1732 ዓ.ም. የሚስኪቶ ንጉሥ የወዳጅነት ውል ከእንግሊዝ ጋራ ተፈራርመው በ1741 ዓ.ም. በእንግሊዝ መከታ ውስጥ ገብተው "ኗሪ ተቆጣጣሪ" ተሾመላቸው።

ሥልጣን በንጉሱና በአገረ ገዥ በሻለቃ ከ1740ዎቹም ጀምሮ በባሕር ኃይል አለቃ መካከል ተከፋፍሎ ነበር። በአሜሪካ ነጻነት ጦርነት ጊዜ (1767-1775) የሚስኪቶ መንግሥት በእንግሊዞች ዘንድ አገልግሎ በስፓንያ ቅኝ አገሮች ላይ አደጋ በመጣል ብዙ ድል አገኘ።

ነገር ግን በ1775 ዓ.ም. እንግሊዝ ድል ስለሆነ በፓሪስ ሰላም ቃል ኪዳን ውል የባሕር ዳር ክልል መልቀቅ ነበረበት። በ1779 ዓ.ም. እንግሊዞች በሙሉ ወጥተው ጨርሰው ስፓንያውያን መጀመርያ በሚስኪቶ መሬት ቢደርሱም ሚስኪቶዎቹ ግን ስለ ቁጥራቸውና ስለ አርበኞቻቸው አውራጃቸውን ከማሰልጠናቸው አልተዉም። እንግሊዞች ቢወጡም የሚስኪቶ አገር ይፋዊ ባልሆነው መከታ ወስጥ ቀረችና ብዙ ጊዜ ከእስፓንያውያን ጋር ሲከራክሩ ብሪታኒያ በጉዳዩ ውስጥ ጥልቅ ብላ ገብታለች።

እንግሊዝ አገር በማዕከል አሜሪካ በተለይም በቤሊዝምጣኔ ሀብት ሀሳብ ስለነበራት ሚስኪቶዎቹ ጠመንጃ እና ሌሎች አዲስ መሣሪያዎች ሊያገኙ ቻሉ። ከዚያ በኋላ ሚስኪቶዎቹ "ዛምቦ" ከሚባሉት ክልሶች ጋር በስፓንያውያን መስፈርያዎች በሆንዱራስ ላይ አደጋ በመጣል የተማረኩትን ኗሪዎች በባርነት ወደ አውሮፓ ሳይወሰዱ ያድኗቸው ነበር። ደግሞ የሌሎቹን ጐሣዎች ሰዎች ሲማርኩ ወደ ጃማይካ ይሸጧቸው ወይም ሴቶቻቸውን ያግቧቸው ነበር። ከዚህ የተነሣ በባሕላቸውም ካንድ የበለጠ ሚስት ማግባት ስለ ተፈቀደ ቁጥራቸውን ቶሎ አበዙ።

ፖለቲካዊ ሥራዓታቸው በስፓንያውያን ግዛት ዘመንና በማእከል አሜሪካ አገሮች ፌዴራሲዮን አገዛዝ ዘመን ላይ ሚስኪቶዎች ነፃነታቸውን እንዲጠብቁ አስቻላቸው። ከ1851 ጀምሮ የእንግሊዝ መንግሥት መከታ ለሆንዱራስ በሚከተለውም አመት ለኒካራጓ ተሰጠ። የሚስኪቶ መንግሥት ራስ-ገዥ ሁኔታ ምንም ቢሰጥም ኒካራጓ ግን ወደፊት ንጉሶቻቸውን አልተቀበለችም። በ1886 ዓ.ም. ምድራቸው በኒካራጓ መንግሥት ተያዘ። በኒካራጓ መንግሥት መቸም አልተሰለጠኑምና እስከ ዛሬ ድረስ ብዙዎች የኒካራጓ ዜጎች መሆናቸውን እራሳችውን አይቆጠሩም።

1970ዎቹ1980ዎቹ, የኒካራጓ ኰሙኒስት ሳንዳኒስታ መንግሥት በጦርነት 8500 ሚስኪቶዎች ከቤቶቻቸው ሲያሳድዱ እስከ መቶ መንደሮችም ድረስ ሲያጥፉ ሚስኪቶዎቹ ከጎረቤቶቻቸው ከራማሱሙ ጐሣዎች ጋራ ሲያባብሩ ሚሱራሳታ የሚባል ግምባር አቆሙ። ይህ ጸረ-መንግሥት ወገን የኮንትራዎች ወንበዶች ክፍል ነበረ።

የሞስኪቶ ንጉሶች[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

 • 1617-1679 - ኦልድማ
 • 1679-1710 1ኛ ጀረሚ የሞስኪቶ ንጉስ
 • 1710-1721 2ኛ ጀረሚ የሞስኪቶ ንጉ
 • 1721-1731 1ኛ ፒተር
 • 1731-1747 1ኛ ኤድዋርድ
 • 1747-1768 1ኛ ጆርጅ
 • 1768-1793 2ኛ ጆርጅ ፍሬደሪክ
 • 1793-1816 1ኛ ጆርጅ ፍሬደሪክ አውግስጦስ
 • 1816-1834 ሮበርት ቻርለስ ፍሬደሪክ
 • 1834-1857 2ኛ ጆርጅ አውግስጦስ ፍሬደሪክ

ወራሽ አለቆች[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

 • 1857-1871 ዊሊያም ሄንሪ ክላረንስ
 • 1871-1880 ጆርጅ ዊሊያም አልበርት ሄንዲ
 • 1880-1881 አንድረው ሄንዲ
 • 1881-1882 ጆናታን ቻርልስ ፍሬደርክ
 • 1882-1900 ሮበርት ሄንሪ ክላረንስ
 • 1900-1920 ሮበርት ፍሬደሪክ
 • ከ1970 ጀምሮ ኖርቶን ከስበርት ክላረንስ