ማርሱስ

ከውክፔዲያ

ማርሱስጀርመን መምኅር ዮሐንስ አቬንቲኑስ ባሳተመው ዜና መዋዕል ዘንድ፣ የጀርመንና ሳርማትያ ፮ኛው ንጉሥ ነበረ። ከአባቱ ሄርሚኖን ቀጥሎ ለ46 ዓመታት (ምናልባት 2065-2019 ዓክልበ. ግድም) ነገሠ። ዋና ከተማው አሁን ማርስበርግ የሚባል ቦታ ሲሆን ማርሲ የተባለው ጀርመናዊ ነገድ ከርሱ እንደ ተወለዱ ይላል።

በማርሱስ ዘመን በግሪክ ውስጥ የዖጊጌስ ጥፋት ውኃ ተከሠተ። በዚህ ዘመን የግብጽ ፈርዖን ኦሲሪስ አፒስማረሻ ጥበብ በየቦታው ሲያስተምር ዞሮ ወደ አውሮፓ ገባ። የጥራክያ አምባገነን ሊኩርጉስን ገድሎ አገሩን ከዳኑብ ወንዝ እስከ ደማስቆ ለአለቃው ማሩስ ሰጠ። እንዲሁም ኦሲሪስ ልጁን ማከዶንኤማጥያ ላይ ሾመው፤ ይህም አገር ከዚያ ጀምሮ መቄዶን ይባል ጀመር። ከዚያ በኋላ ኦሲሪስ አፒስ እራሱ ለጊዜ በግሪክ መንግሥታት ላይ ገዝቶ የዳኑብ ወንዝ ምንጭ ለማግኘት ተጓዘ። በማርሱስ ግዛት (ጀርመን) ሲቆዩ ኦሲሪስና ሚስቱ / እኅቱ ኢሲስብረት ሥራ፣ ግብርና፣ ማዳበር፣ የመድኃኒት ዕፅዋት ጥቅም፣ እና ቢራገብስ መጠመቅ ሁሉ እንዳስተማሩ ይባላል። አበንስበርግባየርን በአፒስም በዚሁ ዘመን እንደ ተሠራ ይለናል። በመጨረሻ የጊጋንቴስ ወገን ከጣልያን ለማባረር ኦሲሪስ አፒስ ወደዛ ሄዶ ለ፲ ዓመታት ነገሠ። ማርሱስ ግን በልጁ ጋምብሪቪዩስ ተከተለ።

ቀዳሚው
ሄርሚኖን
የቱዊስኮኔስ (ጀርመን) ንጉሥ
2065-2019 ዓክልበ. ግድም
ተከታይ
ጋምብሪቪዩስ