Jump to content

ሥነ ጥምረት

ከውክፔዲያ
3 የተየያየ ቀለም ያላቸውን ኳሶች አጠቃላይ መሰደሪያ (መደርደሪያ) ዘዴዎች -- በሥነ ጥምረት ሲሰሉ 3!= 3*2*1 = 6 ናቸው። ማለት ኳሶቹን ለመሰደር 6 አይነት መንገዶች አሉ ለማለት ነው

ሥነ ጥምረትሒሳብ ቅርንጫፍ ሲሆን የሚያጠናውም ሊቆጠሩ የሚችሉ ጠጣር የሂሳብ ነገሮችን (መዋቅሮችን) ነው። ሥነ ጥምረት በውሱን ወይም አእላፍ ተቆጣሪ ስብስቦች ላይ ተግባራዊ ሲሆን ይታያል።

ሥነ ጥምረት የጠጣር ሒሳብ አካል ሲሆን ትኩረቱ የሚያይለው ከአንድ ስብስብ ሊወጡ የሚችሉ ምርጫዎችን በመቁጠር፣ ነገሮች ሊይዙት የሚችሉትን ቅጥ አይነት በሒሳብ በመድረስ፣ እኒህ ቅጦች እንዴት ሊደረስባቸው ይቻላል የሚለውን ጥያቄ በመመለስ ነው። በሥነ ጥምረት ስር ከሚገኙ የሒሳብ ዘርፎች፣ ግራፍ ኅልዮት እና ሥነ መካለል ዋና ዋናዎቹ ናቸው።