ሰማሪዎን (ዕብራይስጥ፦ /ጽማሪ/) በኦሪት ዘፍጥረት 10 ከከነዓን ልጆች አንዱ ነበረ። በፊንቄ ጠረፍ ላይ ጹሙር (ጹሙሩ) በአሁኑ ሶርያ የተባለው ከተማ ስሙን ከርሱ እንዳገኘው ይባላል።
አለቃ ታዬ እንደ ጻፈው፣ በኩሽ ንጉሥ 1 ሳባ 15ኛ ዓመቱ በግብጽና በሱዳን ላይ ረሃብ ስለ ጸና ከከነዓን ልጆች የሰማሪዎን (ሳምሪ) ተወላጅ ዋቶ እና ነገዱ (ወይጦ) ወደ ኩሽ መንግሥት ገቡ።