ሰናንኩያ

ከውክፔዲያ
Jump to navigation Jump to search

ሰናንኩያ (ወይም ሰናንኩኛስናንኩንሰነንኩን[1][2]) በማሊ፣ በጊኔና በጋምቢያ የሚገኝ ኅብረተሠባዊ ባሕርይ ነው፤ ባጠቃላይ በብዙ የምዕራብ አፍሪካ ኅብረተሠቦች ይገኛል። ትርጉሙ እንደ «መቀላለድ ዝምድና» ይመስላል።

በተወሰኑ የጎሳ ወይም የሙያ ቡድኖች ውስጥ ካለው ልምድ በላይ፣ «በረዶውን የሰበሩት» ማናቸውም ፈቃደኛ ተሳታፊዎች የሰናንኩያ ግንኙነት ሊመሠረቱ ይችላሉ። በሰናንኩያ ዝምድና ያሉት እርስ በርስ እንደ ቅርብ ዘመድ ሊቀላለዱ ይችላሉ። ቀልዶችም እስከ ቀላል ወይም አስቂኝ ስድቦች ሊደርሱ ይችላሉ። ይሄ የማንዴ እና የምዕራብ አፍሪካ ኅብረተሠብ ወሳኝ አላባ ይቆጠራል፤ በሱንዲያታ ከይታ1228 ዓም በማሊ መንግሥት አፈ ቃል ሕገ መንግሥትኩሩካን ፉጋም ዘንድ ሰናንኩያ እንደ ብሔራዊ አገባብ እንደ ተደነገገ ይባላል።

ይህም ውስብስብና ለረጅም ዘመን የቆየ ልማድ ተጽእኖች በምዕራብ አፍሪካ ሲታዩ እንዲሁም በአፍሪካዊ-አሜሪካዊ ባሕል ሊታዩ ይቻላል። ይህ በባህላዊ ሥርዓቶች ላይ ለምሳሌ «ዘ ደዘንዝ» በተባለው ይታያል፣ እንዲሁም በቅርብ ያልተዘመዱት ሰዎች በጨዋታ እንደ ቅርብ ዘመድ እንደ አክስት ምናምንት የሚለውን ማዕረግ እርሱ በርስ የሚፈቀዱበት ልማድ ከዚህ ታሪካዊ ድንጋጌ እንደ ወጣ ይመስላል።

ለአንድ ምሳሌ፣ ትራኦሬ እና ኮኔ የተባሉት ጎሦች መሃል እርስ በርስ ከሌላውም አባላት ጋር የ«ሰናንኩያ» ግንኙነት ሲኖር፣ ከቆዩት ሯጭ ቀልዶች መካከል ትልቅ የሆነው፣ እያንዳንዱ ጎሣ ሌላውን በይበልጥ ባቄላን መብላይ የሚወድድ መሆኑን እርስ በርስ ይከሠሳሉ።[3]

2014 እ.ኤ.አ. (2006 አም.) በኒጄር ያሉት ሐውዛፉላኒ ብሔሮች «መቃለድ ተግባር» በዩኔስኮ ድርጅት ብያኔ «የሰው ልጅ የማይጨበት ባሕላዊ ቅርስ» ተብሎ ተሰየመ።[4]

ዋቢ መጻሕፍት[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

  1. ^ McNaughton, Patrick: A Bird Dance near Saturday City: Sidi Ballo and the art of West African masquerade, 2008, p. 88ff.
  2. ^ Bamana: The Art of Existence in Mali, p. 246.
  3. ^ McNaughton, p. 90.
  4. ^ ዩኔስኮ (እንግሊዝኛ) የ2009 እ.ኤ.አ. አጭር ፈረንሳይኛ ፊልም ይያዝማል።