ሻይ ቅጠል

ከውክፔዲያ
የሻይ ቅጠል
Camellia sinensis

ሻይ ቅጠል ወይንም «ካሜሊያ ሲኔንሲስ» በመባል የሚጠራው ችግኝ ሻይ ለማዘጋጀት የሚጠቅም እና ዓመቱን ሙሉ የሚለመልም ሲሆን ለመጀመሪያ ጊዜ የተገኘውም በቻይና እና በህንድ ነው። የሻይ ቅጠል ወፍራም ሲሆን ቀለሙ ደግሞ የጥቁር አርንጓዴ ነው። የሻይ ችግኝ ነጭ እና ሮዝ አበባም አለው። ይህም አበባ ሽቶ ለመስራት ያገለግላል። በአለማችን ላይ ከ200 የበለጡ የሻይ ችግኝ ዘሮች ይገኛሉ።