ቅዱስ ገብርኤል
ቅዱስ ገብርኤል | |
---|---|
ብሥራተ ገብርኤል | |
መዐረግ | ሊቀመላዕክት |
፩ኛ በዓለ ንግሥ | ታኅሣሥ ፳፪ ብሥራተ ገብርኤል |
፪ኛ በዓለ ንግሥ | ሐምሌ ፲፱ ቅዱስ ቂርቆስንና እናቱ ቅድስት እያሉጣን ከእሳት ያወጣበት |
፫ኛ በዓለ ንግሥ | ታኅሣሥ ፲፱ ሦሥቱን ደቂቃት ከእሳት ያዳነበት |
ገብርኤል (ቅዱስ ገብርኤል) በአብርሃማዊ ሀይማኖቶች (ክርስትና ፤ አይሁድ ፤ እስልምና) ከሶስቱ ዋና የእግዚአብሔር መላዕክት (ቅዱስ ሚካኤል፡ ቅዱስ ገብርኤል፡ቅዱስ ሩፋኤል) አንዱ ነው። በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ የተጠቀሰው በመጽሐፈ ዳንኤል ነው። የስሙም ትርጉም «ከእግዚአብሔር የሆነ አለቃ» ማለት ነው። በእግዚአብሔር ፊት መቆም ከሚችሉ ስባት መላዕክት ውስጥም አንዱ ተደርጎ ይቆጠራል። የአምላካችን፣ የጌታችንና የመድሐኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስን ልደት ለቅድስት ድንግል ማርያም አብስሯል።
በተጨማሪም ስለ መላእክት ከመጽሐፍ ቅዱስ ለመረዳት ፡
ዘፍ.16፡7/ ዘፍ.18፡15/ ዘጸ.23፡20/ መሳ6፡11/ 1ኛነገ.19፡5/ 2ኛነገ 6፡15/ ዳን.8፡15-19/ ዳን.3፡17/ ት.ዘካ.1፡12/ ማቴ.18፡10/ሉቃ. 1፡26/ ሉቃ.13፡6/ ዩሐ.20፡11/ ሐዋ.12፡6/ ራዕይ 12፡7/
ዘፍ.19፡1-2/ ዘኁ.22፡31/ ኢያሱ 5፡12-14/ መሳ.13፡2-22/ 1ኛ ዜና 21፡1-16/ ዳን.8፡15-17
እግዚአብሔርን የሚያመለኩና የሚገዙ እንዲሁም ለእርሱ ከብርን በመስጠት ያሉ ሁሉ ከነገር እንኳን አንዳች እንደማይጎድላቸው በዘመናት መካከል ተመልክተናል፡፡ ይህም ደግሞ እውነት ነው፡፡ ደግሞም እግዚአብሔር ለሚወዱት የሚሆን ጠባቂ በዙሪያቸው ያቆማል ።
እስራኤልላውያን በምርኮ ወደ ባቢሎን ምድር ወረዱ በዚያም በግዞት ኑሮዋቸውን ሲገፉ ኖሩ ፡፡
ከዕለታት አንድ ቀን የባቢሎን ምድር ንጉስ የነበረው ናቡከደነጾር ቁመቱ ስድሳ ክንድ ወርዱም ስድሳ ክንደ የሆነ ጣዖትን አሰርቶ ዱራ በሚባል ሜዳ ላይ አስቆመው በዚያም አንድ ትህዛዝን አዘዘ በእርሱ ግዛት ስር የሚተዳደሩትን በሙሉ እንደዚህ አላቸው የመለከት ድምጽ በሰማችሁ ጊዜ ለዚህ እኔ ላቆምኩት ምስል ስገዱ የማይሰግድ ግን በዚህ በሚነደው እቶን እሳት ስር ይጣላል አለ፡፡
እንደተባለውም የመለከቱ ድምጽ በተሰማ ጊዜ ሁሉም በግባሩ ተደፍቶ ለቆመው ምስል ሰገደ፡፡ ነገር ግን ከሕዝቡ ምካከል ሦስት ሰዎች ሳይሰግዱ ዝም ብለው ቆሙ፡፡ አስተናባሪዎቹ ግን እንዲሰግዱ ለመኑዋቸው ልጆቹ ግን እንቢ አሏዋቸው፡፡ ይህን ባለማድረጋቸው ወደ ሚነደውና ድምጽም ወደሚያስፈራ እሳት አመላከቷዋቸው ነገር ግን ጸንተው ቆሙ ልጆቹ ‹‹አምላኩን የሚያውቅ ሕዝብ ይቃወሙታል›› ይላል መጽሐፍ ቅዱስ፡፡
በመሆኑም ልጆቹ ይህን በጽናት ተቃወሙት፡፡ አንሰግድም ብለውም በጽናት ቆሙ፡፡ ‹‹የምናመልክው አምላክ ከዚህ ከሚነደው እሳት ያድነናል ባያድነን እንኳን አንተ ላቆምከው ምስል አንሰግድም›› አሉት ፡፡
ይህ ዓይነት ነገር ታላቅ እምነት ነው በዚህም ደግሞ ወንጌልን በኦሪት ያስተምሩናል፡፡ ይህም ማለት ‹‹ሳያዩ የሚያምኑ ብጹአን ናቸው›› እነዚህም ልጆች ሳያዩ አመኑ ድግሞም ቁርጥ ያለ መለስ መለሱ፡፡ በቅዱሱ አምላክ መታመን ማለት የእርሱን ጥበቃ የሚሆነውን ታላቅ ድህነት እናገኛለን ማለት ነው፡፡ ቅዱስ ዳዊት እንዲህ ይላል ‹‹የእግዚአብሔር መልአክ በሚፈሩት ሰዎች ዙሪያ ይሰፍራል ያድናቸውማል›› መዝ.33፡7፡፡ ይህም በመሆኑ ታዳጊው አምላክ እነርሱን ለመታደግ ሲል መላእክትን ይልካል፡፡
በዚህም ሁኔታ ንጉሱ ናቡ ከደነጾር በቁጣ እንዲህ አለ ወደ እሳቱ ጨምሩዋቸው አለ፡፡ ወስደውም ወደ እሳቱ ጨመሩዋቸው ነገር ግን በዚህ መሀል አንድ ትልቅ ነገር ተከሰተ ከሚጣሉት ሶስቱ ልጆች ጋራ ቀድሞ የተገኘው አራተኛው የእግዚአብሔር መልአክ ነበር፡፡ በእሳቱም መካከል በዝማሬ ተሞሉ፡፡ በዚያም የነበሩት ሁሉ በሆነው ነገር ተገረሙ፡፡ ንጉሱም እንዲህ አለ ‹‹እኔ የተፈቱ በእሳቱ ውስጥ የሚመላለሱ አራት ሰዎች አያለው ›› አለ አራተኛውንም ሲገልጸው ‹‹የአምላክን መልክ ይመስላል›› አለ፡፡
ከሊቃነ መላእክት መካከል አንዱ የሆነው ቅዱስ ገብረኤል በገነት አበቦች መካከል የተሾመው የአምላክ ባለሙዋል ነበር መ.ሔኖክ 10፡14፡፡ ከእሳቱ ውስጥ የነበርው፡፡ ለአምላካቸው የሚታመኑትን የሚረዱና የሚያገለግሉ የአምላካችን የእግዚአብሔር አገልጋዮች ቅዱሳን መላእክት ሁሌም ቢሆን እኛን ለመርዳት ይፈጥናሉ፡፡ በመሆኑም መላእክት ፈጣንና ሰውን ለመታደግ የሚተጉ ናቸው፡፡ ‹‹ቅዱሳን መላእክት አፈጣጠራቸው እም ኀበ አልቦ ኀበ ቦ (ካለመኖር ወደ መኖር) አምጥቶ ነው፡ ነገር ግን በግበራቸው በእሳትና በነፋስ ተመስለዋል፡፡ ይህውም እሳት ረቂቅ ነው መላእክትም እንደዚሁ ረቂቃን ናቸው፡ ነፋስ ፈጣን ነው እንደዚሁ መላእክት ፈጣን ናቸው ለተልእኮና እኛን ለመርዳት ፈጣን ናቸው›› (አክሲማሮስ) መዝ. ‹‹መላእክቱን መንፈስ የሚያደርግ አገልጋዮቹን እሳት ነበልባል›› ይላል በመጽሐፍ ቅዱስ ስለ መላእክት ተፈጥሮ ሲነግረን እንዲሁም በአዲስ ኪዳን ሐዋሪያው ቅዱስ ጳውሎስ ደግሞ እንዲህ ይለናል፡-‹‹ሁሉ መዳንን ይወረሱ ዘንድ ስላላቸው ለማገዝ የሚላኩ የሚያገለግሉም መናፍስት አይደሉምን ›› ዕብራውያን 1፡14፡፡ አምላካችን ሁላችንንም ከዚህ ረድኤት በረከት ይክፈለን፡፡ ቅዱስ ገብርኤል ሁላችንንም ይጠብቀን፡፡
ክርስትያኖች የአምላክን መልዕክተኛ «ገብርኤል» ሲሉት በእስልምና ደግሞ በአረብኛ ስሙ «ጂብሪል» ይባላል።