ማርያም

ከውክፔዲያ
(ከድንግል ማርያም የተዛወረ)
Jump to navigation Jump to search
ቅድስት ድንግል ማርያም
ንግሥተ ሰማይ ወምድር
እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ምስለ ፍቅርን ታቅፋ
እርግበ መንግሥተ ሰማያት
የተወለደችው ፲፮ኛው ዓ.ም. ከክርስቶስ ልደት በፊት
የትውልድ ሀገር  ሊባኖስ
የምትከበረው ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን
ካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን
ኦርቶዶክ ክርስቲያን ቤተክርስቲያኖችና
በአንዳንድ ክርስቲያን ዲኖሚኔሽን
የእናት ስም ሃናማርያም
የአባት ስም እያቄም
ያረፈችበት በ፷፬ ዓመቷ
በዐላት ፴፫ሲሆኑ ዋና ዋናዎቹ፣
- የተወለደችበት ቀን ልደታ ግንቦት ፩
- ለቤተክርስቲያን የተሰጠችበት ባአታ ማርያም ታህሣሥ ፫
- ቃል ኪዳን የተቀበለችበት ኪዳነ ምረት የካቲት ፲፮
- በጎሎጎታ እየተመላለሰች የጸለየችበት ሰኔ ጎሎጎታ ሰኔ ፳፩
- በድንግልና የፀነሰችበት ነሐሴ ፯
- ፍልሰቷ ፍልሰታ ነሐሴ ፲፮


ድንግል ማርያምክርስትና፣ በእስልምና እምነቶች መሠረት የከበረችው የኢየሱስ ክርስቶስ እናት ነች። በክርስትና እምነት የኢየሱስ ክርስቶስ እናት ማለትም የወልድ እናት ድንግል ማርያም በመንፈስ ቅዱስ ግብር ኃይል በድንግልና ፀንሳ በድንግልና እንደ ወለደችው ይታመናል ። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በጣም ከመወደዷ የተነሳ ከ፻ በላይ ስሞች አሉዋት ። የቅድስት ድንግል ማርያም ስሞች

ሙስሊሞች ደግሞ መሪማ የኢየሱስ (ኢሳ) እናት ይልዋታል። በአለም ላይ ፪ ታላላቅ እምነቶች ዘንድ እስዋም ልጅዋም ትልቅ ሰዎች ተብለዉ ከተመረጡ ሰዎች ናቸዉ።

ክርስትና[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

በክርስትና እምነት ድንግል ማርያም ሰውሁኖ የመጣዉ የጌታ የኢየሱስ ክርስቶስ እናት ነች። ኢየሱስ ክርስቶስ ደግሞ ከአብ ወልድ መንፈስ ቅዱስ የአባት (የአብ) ልጅ (ወልድ) መንፈስ ቅዱስ (ሰራጺ )ነዉ፤ ደግሞ ጌታ ወይም መሢሕ ይባላል። እናቱ ማርያም እግዚአብሔር የተባለውን ወልድ ለመውለድ ስለ ተመረጠች እና ብቁ ሆና ስለተገኘች ከሴቶች ሁሉ ይልቅ ብጹዕ ፣ ቅድስት ትባላለች።

+የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ+[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ከ 34 ዓ.ም ጀምራ ክርስትናን በኢትዮጵያ ምድር የሰበከች ጥንታዊት ቤተክርስቲያን ሥትሆን ምድቧም ከ ኦርዮንታል አብያተ ክርስቲያናት ነው:: እንደ ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አስተምህሮ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ከሥላሴ አካላት አንዱ ወልድ፣ አምላክ ነው::ይህ አምላክም ወይም እግዚአብሔር ወልድ ከቅድስት ድንግል ማርያም ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነሥቶ ተወለደ::በሌላ አገላለጽ አምላክ ሰው ሆነ::በዚህም ምክንያት ቅድስት ድንግል ማርያምን የጌታ እናት ወይም የእግዚአብሔር እናት(ወላዲተ አምላክ) ትባላለች:: ቤተክርስቲያኗ ልጇን ኢየሱስ ክርስቶስንም አምላክ ፣ ወልደ አምላክ ፣ ወልደ ማርያም ፣ ወልድ፣ ቃል ብላ ትጠራዋለች:: ድንግል ማርያምን ደግሞ እመቤት ፣ ቅድስተ ቅዱሳን ፣ እግዝእትነ ማርያም ፣ የጌታ እናት ፣ ወላዲተ አምላክ ፣ ቅድስት፣እመ ብርሃን ፣ እመ አምላክ፣ንጽሕተ ንጹሃን ቅድስተ ቅዱሳን፣ጽዮን ወዘተ በማለት ትጠራታለች::ቅድስት ድንግል ማርያምን አንዳንድ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ተከታዮች ከአዳም በደል ወይም ከጥንተ አብሶ ነጻ ሆና በአዳም ባህርይ እንደ እንቁ ስታበራ የኖረች አደፍ ጉድፍ የሌለባት ፣ ከመርገመ ሥጋ ከመርገመ ነፍስ የነጻች ፣ እንደሆነች ያምናሉ። ሌላው ወገን ጥንተ አብሶ ነበራት ለዚህም ማስረጅያ "ጸሎተ እግዝእትነ ማርያም" ተብሎ የሚጠራው በሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ 1 ቁጥር 47 እግዚአብሔርን "መድኃኒቴ" ብላ ማመስገነዋ ነው። ሁለቱም ወገን ግን እግዚአብሔር ወልድ ሥጋዋን ከተዋሃደ በፊት እንዳነጻት ማደሪያው እንድትሆን እንዳስጌጣት ከወለድችሁም በኋላ በድንግልኗና በንፅህኗ እንደኖረች፣ ለዘለዓለም በዚሁ ሁኔታ ጸንታ እንደምትኖር ያምናሉ። ከፍጡራን በላይ ከፈጣሪ በታች የሆነች፣ የሰማይ የምድር ንግስት ፣ እንደሆነች ቤተክርስቲያን ታስተምራለችና::

የቅድስት ድንግል ማርያም ትውልድ:- ቅድስት ድንግል ማርያም አባቷ ኢያቄም እናቷ ደግሞ ሃና ይባላሉ::የተፀነሰቸው በእለተ እሁድ ነሐሴ ፯ ቀን ሲሆን የተወለደቸውም ግንቦት ፩ ነው::እመቤታችን እግዝትእነ ማርያም የተወለደችበት እለት በአባት እናቷ ቤት ፍስሃ ደስታ ተደረገበት ፤ ቤቱንም ብርሃን መላው ፤ በ፰ኛውም ቀን ማርያም ብለው አወጡላት::ስለምን ማርያም ብለው አወጡላት ቢሉ:እነሆ በዚህ አለም ከሚመገቡት ሁሉ ምግብ ለአፍ የሚጥም ለልብ የሚመጥን ማር ነው:በገነትም በህይወት የተዘጋጁ ጻድቃን ቅዱሳን ያም የሚባል ምግብ አላቸው ::ከዚ ሁሉ የበለጥሽ የከበርሽ ነሽ ሲሉ ስለዚህ ማርያም ብለው አወጡላት:: እመቤታችን ማርያም ለእናት ለአባቷ አንዲት ስትሆን የተወለደቸው በጸሎት በመሆኑና የስለት ልጅ በመሆኗ እናትና አባቷ ለእግዚአብሔር በተሳሉት መሰረት ፫ ዓመት ሲሞላት ወደ ቤተመቅደስ ወሰደው ለካህኑ ለዘካርያስ አስረከቧት::እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በተወለደች በሦስት ዓመቷ እናቷ ሐና አባቷ ኢያቄምን፡- “ይህች ብላቴና ሆዷ ዘመድ ሳይወድ፣ አፏ እህል ሳይለምድ “ለእግዚአብሔር በገባነው ቃል መሠረት ወስደን ለቤተ መቅደስ አንሰጣትምን?” ‘የሰጠ ቢነሣ የለበት ወቀሳ’ እንዲሉ አንዳች ነገር ብትሆንብን ከልጃችንም ከእግዚአብሔርም ሳንሆን እንዳንቀር” አለችው፡፡ እርሱም፡- “ፍቅርሽ ይለቅልሽ ብዬ ነው እንጂ እኔማ ፈቃዴ አይደለምን?” አላት፡፡ወላጆቿ ይህን ተነጋግረው እንዳበቁ ሕጻን ልጃቸውን ማርያምን ወስደው ለቤተ መቅደስ ሰጧት፡፡ በዚያን ጊዜ የነበረው ሊቀ ካህናት ዘካርያስ ይባላል፤ እርሱም ስለ ምግቧ ነገር ሊያስወስን መጥቅዕ (ደወል) ደውሎ ሕዝቡን ሰብስቦ እየተወያዩ ሳለ የእግዚአብሔር መልአክ ሊቀ መላእክት ቅዱስ ፋኑኤል የሰማይ ኅብስትና የሰማይ ጽዋ ይዞ ከሰማይ ወርዶና ረብቦ ታየ፡፡ብላቴናይቱንም መልአኩ ፈጥኖ ወርዶ አንድ ክንፉን አንጥፎ አንድ ክንፉን ደግሞ ጋርዶ በሰው ቁመት ያህል ከምድር አስለቅቆ ከፍ አድርጓትና መግቧት ዐረገ፡፡ ከዚህ በኋላ ካህናቱና ሕዝቡ “የምግቧ ነገር ከተያዘልንማ ከሰው ጋር ምን ያጋፋታል” ብለው ሕጻን ማርያምን ከወላጆቿ ተቀብለው ወደ ቤተ መቅደስ አግብተዋት በዚያ ፲፪ ዓመት ኖራለች፡፡ይህም ሲደመር ጠቅላላ ፲፭ ዓመት ሆናት ማለት ነው::በዚህ ስዓት አይሁድ ከበተመቅደስ ትውጣልን ብለው አመለከቱ ፤ ለጻድቁ ለዮሰፍም እንዲጠብቃት ታጨች ፤ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል አበሰራት::በ ፲፭ አመቷ እግዚአብሔር ወልድን ፀነሰች::

የቅድስት ድንግል ማርያም ስሞች:- የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን «እስመ ስሙ ይመርህ ኀበ ግብሩ» በማለት ስም ግብርን ሁኔታን ማንነትን ይገልጻል ይላሉ፡፡በዚህም መሰረት ቤተክርስቲያኗ ለስመ ድንግል ማርያም ዘርፍ /ቅጽል/ አልያም ምትክ አድርጋ የምትጠቀምባቸው ምሥጢራዊና ረቂቅ ትርጉም ያላቸው ንጽሕናዋን፣ ቅድስናዋን፣ ድንግልናዋን፣ ብፅእናዋን ወዘተ የሚመሰክሩ በርካታ ስሞች ሰይማላታለች፡፡ከነዚህም መካከል ከብዙ በጥቂቱ:ምልዕተ ጸጋ ፣ እምነ /«ም» ጠብቆ ይነበብ/ ጽዮን ፣እመ ብርሃን ሰአሊተ ምሕረት ፣እመቤታችን ፣ቤዛዊተ ዓለም፣ ወላዲተ አምላክ ፣ኪዳነ ምሕረት ወዘተ..

ቅድስት ድንግል ማርያም በ 64 ዓመቷ ካረፈች በኋላ እንደ ልጇ በሦስተኛው ቀን ማረጓን ቤተክርስቲያኑ ታስተምራለች::

እስልምና[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

የማርያምን ድንግል ሁና እየሱስን ወይንም እነሱ እንደሚሉት ኢሳ (አ.ሰ)ን እንደወለደች ብሎም በነሱ እምነት አራት ተብለዉ ከተጠቀሱ ምርጥ ሴቶች ዉስጥ አንድዋ ነች። ነገር ግን ኢሳን የአላህ መልዕክተኛ ነዉ ሲሉት፣ አላህም ፈጣሪዉ እንጅ ልጁ አይደለም ባዮች ናቸው። በቁርአን ምክንያት አምላክ አይወልድም አይወለድም፤ ይህም ለአላህ የማይገባው ሥራ ነው ይላሉ።

አይሁድና[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

አይሁድና ስለሁለቱም ምንም ነገር አያምኑም ሀሰተኛ ናቸዉ ይላሉ። በመጻሕፍታቸው ስለ ማርያም ስድብ ብቻ ይጻፋል።


: