ሚካኤል

ከውክፔዲያ
Jump to navigation Jump to search
ቅዱስ ሚካኤል
ኅዳር 12 - በአለ ሲመቱ ለቅዱስ ሚካኤል
ሊቀመላዕክት ቅዱስ ሚካኤል
መዐረግ የስድስቱ ሊቃነመላዕክት አለቃ
፩ኛ ቅዱስ ገብርኤል
፪ኛ ቅዱስ ሩፋኤል
፫ኛ ቅዱስ ራጉኤል
፬ኛ ቅዱስ ፋኑኤል
፭ኛ ቅዱስ ዑራኤል
፮ኛ ቅዱስ አፍኒን
እንዲሁም የ፺፱ ነገደ መላእክት
፩ኛ በዓለ ንግሥ ኅዳር ፲፪ እስራኤላውያንን ቀይ ባሕርን ያሻገረበት
፪ኛ በዓለ ንግሥ ሰኔ ፲፪ የባሕራምን የሞት ደብዳቤ ወደ ሕይወት የቀየረበት
ሚካኤል ማለት ዕፁብ ድንቅ ነገር


ሚካኤል (ዕብራይስጥ: מִיכָאֵל‎, ሲነበብ፡ ሚካኤል, ሲተረጎም፡ 'ማንነው እንደ እግዚአብሔር?'; በግሪክ: Μιχαήλ, ሲነበብ፡ Mikhaḗl; በላቲን: Michahel-ሲነበብ፡ ሚካኤል; በአረቢኛ: ميخائيل‎, ሲነበብ፡ ሚካኤል) በክርስትና በአይሁድ በእስልምና እንዲሁም በመላዕክት አማላጅነት በሚያምኑ ሃይማኖቶች የመላዕክት ሁሉ አለቃ ሊቀ መላዕክት ተብሎ ይጠራል

ቅዱስ ሚካኤል ሊቀ መላእክት


ቅዱስ ሚካኤል ሊቀ መላእክት - ኦርና አውድማ

መላእክት ቁጥራቸው እጅግ ብዙ ቢሆንም በ ፺፱ኙ ነገደ መላእክት የተከፈሉና አለቆችም ያሏቸው ናቸው፡፡ የእነዚህ ሁሉ መላእክት አለቃ የሆነው ቅዱስ ሚካኤል ነው፡፡ በትህትናው ልዕልናን ያገኘው ቅዱስ ሚካኤል በእግዚአብሔር ዘንድ የተሰጠው ክብር ከማንኛውም መልአክ የበለጠ መሆኑን መጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ አስቀምጦታል፡፡

በተጨማሪም ስለ መላእክት ከመጽሐፍ ቅዱስ ለመረዳት እነዚህን ጥቅሶች ይመለከቱ

ሰውን ይረዳሉ ዘፍ.16፡7/ ዘፍ.18፡15/ ዘጸ.23፡20/ መሳ6፡11/ 1ኛነገ.19፡5/ 2ኛነገ 6፡15/ ዳን.8፡15-19/ ዳን.3፡17/ ት.ዘካ.1፡12/ ማቴ.18፡10/ሉቃ. 1፡26/ ሉቃ.13፡6/ ዩሐ.20፡11/ ሐዋ.12፡6/ ራዕይ 12፡7/

ስግደት ይገባቸዋል ዘፍ.19፡1-2/ ዘኁ.22፡31/ ኢያሱ 5፡12/ መሳ.13፡2/ 1ኛ ዜና 21፡1-7/ ዳን.8፡15

የቅዱስ ሚካኤል ስሞች[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ሚካኤል ማለት << መኑ ከመ አምላክ (እግዚአብሔር) እንደ እግዚአብሔር ያለ ማነው>> ማለት ነው፡፡ ይህም የእግዚአብሔርን ገናንነትና እሱን የሚመስል አምላክ እንደሌለ የሚያመለክት ነው እንደ እግዚአብሔር ያለ ቅዱስ ንጹሕ ርህሩህ ኃይል ረቂቅ ማነው መልሱ የለም ነው፡፡ ቅዱስ ሚካኤል የስሙ ዘርፍ ሆነው የሚጨመሩ መጠሪያዎች አሉት እነዚህም ከእግዚአብሔር ዘንድ የተሰጠውን የባለሟልነት ክብር የሚገልጹ ናቸው፡፡ ይኸውም መልአከ ኃይል፣ መጋቤ ብሉይ፣ መልአከ ምክሩ፣…ናቸው፡፡ መልአከ ኃይል የተባለው እግዚአብሔር በሱ አማካይነት ታላላቅ ሥራዎችን በመሥራት ኃይሉን ስለገለጸ - ዲያብሎስን ከነሠራዊቱ ስላሸነፈ ነው፡፡ መጋቤ ብሉይ የተባለበት ምክንያት በብሉይ ኪዳን ውስጥ ከእግዚአብሔር እየተላከ ብዙ ታላላቅ ሥራዎችን የሠራ በመሆኑ ነው፡፡

መልአከ ምክር ወይም የእግዚአብሔር የምክሩ አበጋዝ የተባለበት ምክንያት እግዚአብሔርን በምክሩ ይረዳዋል ለማለት ሳይሆን እግዚአብሔር የሚሠራውን ሥራ ለወዳጁ ለቅዱስ ሚካኤል ይገልጽለታል በሱም አማካኝነት ይሠራል ለማለት ነው፡፡

ቅዱስ ሚካኤል በመጽሐፍ ቅዱስ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ቅዱስ ሚካኤል በዚህ ሁሉ ልዕልና ላይ ትሕትናን ደርቦ የያዘ በጸሎቱ ተማጽኖ በተራዳኢነት አምኖ ለሚለምነው ሁሉ ፈጥኖ በመድረስ ከሠራዊተ አጋንንት ተንኰል የሚያድን መልአክ ነው፡፡ ወደ ቅዱስ መጽሐፍ ስንገባ ለቅዱስ ሚካኤል የተሰጠውን ክብርና ባለሟልነት እንዲሁም የሠራቸውን ሥራዎች እንመለከታለን፡፡ በመጀመሪያ (ኢያሱ 5÷13-15) እንዲህ ይላል፡፡ ‹‹እንዲህም ሆነ ኢያሱ በኢያሪኮ አጠገብ ሳለ ዓይኑን አንሥቶ ተመለከተ፡፡ እነሆም የተመዘዘ ሰይፍ በእጁ የያዘ ሰው በፊቱ ቆሞ ነበር፡፡ ኢያሱም ወደ እርሱ ቀርቦ ከእኛ ወገን ወይስ ከጠላቶቻችን ወገን ነህን አለው፡፡ እርሱም አይደለሁም እኔ የእግዚአብሔር ሠራዊት አለቃ ሆኜ አሁን መጥቻለሁ አለ፡፡ ኢያሱም ወደ ምድር በግምባሩ ተደፍቶ ሰገደ፡፡ ጌታዬ ለባሪያው የሚነግረው ምንድን ነው አለው፡፡ የእግዚአብሔርም ሠራዊት አለቃ ኢያሱን አንተ የቆምህበት ሥፍራ የተቀደሰ ነውና ጫማህን በፊቱ አውልቅ አለው፡፡ ኢያሱም እንዲሁ አደረገ ይላል፡፡ ይህን ጥቅስ ልብ ብለን ብናጤነው ለሌላው ሁሉ መርህ ይሆናልና ጥቂት ለማብራራት እንሞክራለን፡፡

እንዲሁም እግዚአብሔር ራሱ ለኢያሱ ‹‹…በሕይወትህ ዕድሜ ሁሉ ማንም አይቋቋምህም ከሙሴ ጋር እንደሆነው እንዲሁ ካንተ ጋር እሆናለሁ አልጥልህም አልተውህም፡፡…›› (ኢያሱ 1÷1-9) በማለት ምን ያህል እንዳከበረው ያስረዳል፡፡ እስራኤላውያን አሞራውያንን በወጉ ጊዜ ቀኑ ስለመሸባቸው ከመደበኛው የተፈጥሮ ሕግ ውጭ ቀኑ እንደማይጨልምና መዓልቱ እንዲረዝም ኢያሱ በጸሎት ፈጣሪውን ስለጠየቀ እግዚአብሔርም ጸሎቱን ሰምቶ ቀኑን አስረዝሞ ከሰማይ በረድ አዝንሞ ጠላቶቻቸውን በማጥፋት የፈጸመውን አስደናቂ ተአምር እንዲህ ብሎ ጸፏል፡፡

‹‹...ፀሐይም በሰማይ መካከል ዘገየ አንድ ቀንም ሙሉ ያህል ለመግባት አልቸኰለም፤ እግዚአብሔር ለእስራኤል ይዋጋ ነበርና እግዚአብሔር የሰውን ቃል (ልመና) የሰማበት እንደዚያ ያለ ቀን ከዚያም በፊት ከዚያም በኋላ አልነበረም›› (ኢያ 10÷12-14) በማለት ተገልጿል፡፡ በጠቅላላው ከኢያሪኮ ጀምሮ ታላላቅ የአሕዛብ ምሽጐችን አፍርሶ አሕዛብን አጥፍቶ እግዚአብሔር ለአብርሃም ለይስሐቅ ለያዕቆብ የማለላቸውን የተስፋይቱን ምድር ለልጆቻቸው ያወረሰ ኢያሱ ነው፡፡

ይህ የእስራኤል መሪ በእጅ የተመዘዘ ሰይፍ ይዞ የተገለጸለት ቅዱስ ሚካኤል መሆኑን አላወቀም፡፡ ከቃሉ እንደምንረዳው ከራሱ ወገን ወይም ከጠላቶቹ ወገን የሆነ አንድ ወታደር መስሎት ነበር፡፡ መልአኩ በሰው አምሳል ስለተገለጸለት አላወቀውም ነበር፡፡ ያነጋገረውም ያለ ፍርሃት ያለ ጭንቀት ያለድንጋጤ ወታደሮቹን እንደሚያነጋግር ዘና ብሎ ነው፡፡ ሆኖም ከመልአኩ የተሰጠው መልስ ታላቅ መሪና ነቢይ የሆነውን የኢያሱን አስተሳሰብ ለወጠው፡፡ ይኸውም <<ከወገኖችህ ወይም ከጠላቶችህ አይደለሁም እኔ የእግዚአብሔር ሠራዊት አለቃ ሆኜ አሁን መጥቻለሁ>> የሚለውን ቃል ሲሰማ ኢያሱ በፊቱ የቆመው ተራ ወታደር ሳይሆን የመላእክት ሠራዊት አለቃ ከሙሴ ሳይለይ የእስራኤልን ሕዝብ የሚጠብቅ የእግዚአብሔር መልአክ ቅዱስ ሚካኤል መሆኑን ሲረዳ ለመልአኩ ክብር መስጠት ስለሚገባ የአክብሮት ስግደት ሰገደለት፤ <<ጌታዬ ለባሪያው የሚነግረው ምንድነው>> በማለት በትህትና ጠየቀ፡፡ ጌታዬ አንተ ቅዱስ ሚካኤል ለኔ ለባሪያህ ለኢያሱ የምትነግረኝ ምንድነው; በማለቱ የእግዚአብሔርን ክብር ለፍጡር መስጠቱ አይደለም መላእክት ጌቶች ይባላሉ፡፡ ጌትነታቸውም የጸጋ ጌትነት ነው፡፡

ኢያሱ መልአኩን ጌታዬ ብሎ ከጠራው እኛማ ኃጢአተኞች ጌታዬ፤ ቀዱስ ሚካኤል ለኔ ለባሪያህ ጸልይልኝ መጥተህ አድነኝ…በማለት የአክብሮት (የጸጋ) ስግደት በመስገድ ብንለምነው ከመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ውጭ አልወጣንም፡፡ የፈጣሪን ክብር ለፍጡር አልሰጠንም፡፡ ተሳስታችኋል የሚለን ሰው ቢኖር እኛ አብነት ያደረግነው የእግዚአብሔር ወዳጅ ኢያሱን ስለሆነ ኢያሱም ተሳስተሃል ይባል፡፡ መልአኩም ኢያሱ ያቀረበለትን የአክብሮት ስግደትና ጥያቄ በመቀበል ከእግዚአብሔር የተሰጠውን መልእክት ነገረው፡፡ ኢያሱም ትእዛዙን ፈጸመ፡፡

እግዚአብሔር የሠራዊት ጌታ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ይህም ማለት መላእክትን ፈጥሮ የሚገዛ፣ የሚያዛቸው፣ የሚቀድሳቸው ማለት ነው፡፡ የእግዚአብሔር ሠራዊት አለቃ የሚለው ከፈጣሪ በታች በመላእክት ላይ በፈጣሪ የተሾመ ማለት ነው፡፡ መላእክት አለቆቻቸውን ያከብራሉ፤ ለእነሱም ይታዘዛሉ፡፡ ቅዱስ ሚካኤል የመላእክት ሁሉ አለቃ ስለሆነ ከትእዛዙ አይወጡም፤ ሠራዊተ መላእክት የሚያከብሩትንና የሚታዘዙለትን የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤልን እኛም እንደ ኢያሱ እናከብረዋለን እንታዘዘዋለን፡፡ መላእክትን ማክበርና መታዘዝ እንደሚገባ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፡፡ <<በመንገድህ ይጠብቅህ ዘንድ ወዳዘጋጀሁትም ሥፍራ ያገባህ ዘንድ እነሆ እኔ መልአክህን በፊትህ እሰዳለሁ፤ በፊቱ ተጠንቀቁ፤ ቃሉንም አድምጡ፤ ስሜም በእርሱ ስለሆነ ኃጢአት ብትሠሩ ይቅር አይልምና አታስመርሩት፤ አንተ ግን ቃሉን ብትሰማ፣ ያልሁህንም ሁሉ ብታደርግ፣ ጠላቶችህን እጣላቸዋለሁ፣ የሚያስጨንቁህንም አስጨንቃቸዋለሁ፣ መልአኬ በፊትህ ይሄዳልና…>>(ዘጸ.23÷20-22) በማለት ለሙሴ ተናግሯል፡፡ ይህ ቃል ለአንድ ጊዜ ብቻ ለሙሴና ለሕዝቡ ተነግሮ ያበቃ ሳይሆን እስከዛሬና ወደፊትም የሚቀጥል ነው፡፡ መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል ✞✞✞ በስመ ሥላሴ ✞✞✞

† ♥ † እስጢፋኖስም ጌታ ሆይ፥ ይህን ኃጢአት አትቍጠርባቸው ብሎ በታላቅ ድምፅ ጮኸ። ይህንም ብሎ አንቀላፋ።† ♥ †(የሐዋ.ሥራ ፯፡፶፱-፷)

እንኳን ለሰማዕቱ ቅዱስ እስጢፋኖ ወርሃዊ መታሰቢያ ክብረ በዓል በሰላም በጤና አደረሳችሁ አደረሰን!!! † ♥ † ሰው ግን ዓለምን ቢያተርፍ ነፍሱን ግን ቢጎዳ ምን ይረባዋል/ምን ይጠቅመዋል?† ♥ † ማቴ.፲፮፡፳፮ የቅዱሳኑ ሞት በእግዚአብሔር ፊት የከበረ ነው። መዝ. 115/116፡15 † ♥ †እኔን የሚወድ ቢኖር እራሱን ይካድ መስቀሌንም ተሸክሞ /መከራዬን ሳይሰለች/ ዕለት ዕለት ይከተለኝ † ♥ †፡፡ ማቴ ፲፡፴፰-፵፪ † ♥ † ስለ ጽድቅ የሚራቡና የሚጠሙ፣ እንዲሁም የሚሰደዱ ብጹዓን ይጠግባሉና፣ መጽናናትንም ያገኛሉና…† ♥ † ጌታ በተራራ ስብከቱ ከተናገራቸው፣ ካስተማራቸው የሕይወት ምግብ የሆነ ቃሉ ማቴ.፭፡፩-ፍጻሜ ቅዱስ እስጢፋኖስ በፍርድ አደባባይ ሲቆምና ሲከሠስ እውነቱን መናገሩ ሕይወቱን እንደሚያስከፍለው እያውቀ፡፡ እውነቱን መናገር አልፈራም፡፡ አያችሁ ቅዱስ እስጢፋኖስ የእግዚአብሔርን ፈቃድ ነበር ያስተዋለው፡፡ ውጤቱ ምንም ይሁን፡፡ እግዚአብሔር በእውነት የተሞላን እንድንሆን ይፈልጋል፡፡ የክርስቶስ ምስክር ሆነው የተሰዉት ቅዱሳን የክብር አክሊል የተቀዳጁት ለእውነት ስለሞቱ ነው፡፡ ነገር ግን በመንፈስ ሕያዋን ናቸው፡፡ በዘላለማዊ ደስታም ከእግዚአብሔር ጋር ኖረዋል፡፡ እስጢፋኖስም ጸጋንና ኃይልን ተሞልቶ በሕዝቡ መካከል ድንቅንና ታላቅ ምልክትን ያደርግ ነበር። የነፃ ወጪዎች ከተባለችው ምኵራብም ከቀሬናና ከእስክንድርያም ሰዎች ከኪልቅያና ከእስያም ከነበሩት አንዳንዶቹ ተነሥተው እስጢፋኖስን ይከራከሩት ነበር፤ ይናገርበት የነበረውንም ጥበብና መንፈስ ይቃወሙ ዘንድ አልቻሉም። በዚያን ጊዜ። በሙሴ ላይ በእግዚአብሔርም ላይ የስድብን ነገር ሲናገር ሰምተነዋል የሚሉ ሰዎችን አስነሡ። ሕዝቡንና ሽማግሌዎችንም ጻፎችንም አናደዱ፥ ቀርበውም ያዙት ወደ ሸንጎም አመጡትና። ይህ ሰው በዚህ በተቀደሰው ስፍራ በሕግም ላይ የስድብን ነገር ለመናገር አይተውም፤ ይህ የናዝሬቱ ኢየሱስ ይህን ስፍራ ያፈርሰዋል ሙሴም ያስተላለፈልንን ሥርዓት ይለውጣል ሲል ሰምተነዋልና የሚሉ የሐሰት ምስክሮችን አቆሙ። በሸንጎም የተቀመጡት ሁሉ ትኵር ብለው ሲመለከቱት እንደ መልአክ ፊት ሆኖ ፊቱን አዩት። ፮፡፰-፲፭) “ይህ እንዴት ያለ ይቅርታ ነው? ልክ ጌታ በዚያ በመከራ ሰዓት ብዙ መከራ ሲያጸኑበት አባት ሆይ የሚያደርጉት አያቁምና የቅር በላቸው ብሎ የፍቅር አምላክ ይቅርታ እንዳደረገላቸው ሁላ የጌታው ተከታይ የሆነው፤ እስጢፋኖስም።” “ጌታ ኢየሱስ ሆይ፥ ነፍሴን ተቀበል ብሎ ሲጠራ ይወግሩት ነበር። ተንበርክኮም። ጌታ ሆይ፥ ይህን ኃጢአት አትቍጠርባቸው ብሎ በታላቅ ድምፅ ጮኸ። ይህንም ብሎ አንቀላፋ። ሳውልም በእርሱ መገደል ተስማምቶ ነበር።” (የሐዋ.ሥራ ፯፡፶፱-፷) የሰማዕቱ በረከት ይደርብን እስከ ሞት ድረስ ለአምላካችን እንድንታመን እርሱ ይርዳን፡፡ እስከ መጨረሻ ድረስ የታመንህ ሁን የህይወት አክሊል እሰጣሃለሁ ራዕይ 2፡10 ለዚህ ነው እኮ ቅ/ጳውሎስ “እሩጫዬን ጨርሻለሁ ሃይማኖቴን ጠብቄያለሁ ከእንግዲህ የሕይወት አክሊል ይጠብቀኛል” ያለው ፪ጢሞ.፬፡፮-፯ የእግዚአብሔር፣ቸርነት የድንግል ማርያም አማላጅነት፣ የቅዱሳን መላእክት ተራዳኢነት፣ የጻድቃን፣ የሰማዕታት፣ የቅዱሳን ሐዋርያት፣ የቅዱሳን አበው መነኮሳት፣ የቅዱሳት አንስት፣ የደናግላንና የቅዱሳን ሁሉ ምልጃና ቃል-ኪዳናቸው ባለንበት ከሁላችን ጋር ይሁን ይቆየን፡፡

ወስብሐት ለእግዚአብሔር ወለወላዲቱ ድንግል ለመስቀሉ ክቡር አሜን ። ይቆየን ጊዜ ሕዝበ እስራኤልን ፊት ፊት እየመራ ጠላቶቻቸው አሕዛብን አጥፍቶ ምድረ ርስትን ምድራዊት ኢየሩሳሌምን እንዳወረሳቸው ዛሬም ይኸው መልአክ ቅዱስ ማካኤል እስራኤል ዘነፍስ የተባልን ህዝበ ክርስቲያንን ፊት ፊት እየመራ ጠላቶቻችን ሠራዋተ አጋንንትን እያጠፋ ምድረ ርስት ወደተባለች ሰማየ ሰማያት ያገባናል፡፡ የእስራኤል ሕዝብ ታሪክ ለአዲስ ኪዳን ሕዝብ ምሳሌ ስለሆነ በታሪክነቱ ብቻ ተነግሮ የሚታለፍ አይደለም፡፡ ኦሪት ሰም ሲሆን ሐዲስ ኪዳን ደግሞ ወርቅ ነውና፡፡

ይህ የእግዚአብሔር ሠራዊት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ሕዝበ እስራኤልን ከግብጽ ባርነት ያወጣ፣ በበረሃ 4ዐ ዓመት የመራቸው፣ ምድር ርስትን ያወረሳቸው መሆኑን በሌላ ስፍራ እንዲህ ይላል፡፡ ‹‹…በእስራኤል ሠራዊት ፊት ይሄድ የነበረው የእግዚአብሔር መልአክ ፈቀቅ ብሎ በኋላቸው ሄደ፤ የደመናውም ዓምድ ከፊታቸው ፊቀቅ ብሎ በኋላቸው ቆመ፡፡›› (ዘጸ.14÷15-20) በዚህ መሠረት እስራኤልን ይመራ የነበረው የእዚአብሔር መልአክ ቅዱስ ሚካኤል ነው፡፡ እንዲሁም በኮሬብ ተራራ እግዚአብሔር ለሙሴ ሐመልማል ከነበልባል ተዋሕዶ በተገለጸለት ጊዜ መልአኩ ቅዱስ ሚካኤል አልተለየም ነበር፡፡ (ዘጸ.3÷1-6፣ የሐዋ. 7÷30-34) በኦሪት የእግዚአብሔር መልአክ እየተባለ የሚጠራው አብዛኛውን ጊዜ ቅዱስ ሚካኤል እንደሆነ ሊቃውንተ ቤተ ክርስቲያን ያስተምራሉ በድርሳነ ሚካኤልም ተጽፎ ይገኛል፡፡ (መዝ.33÷7) ‹‹የእግዚአብሔር መልአክ (ቅዱስ ሚካኤል) እግዚአብሔርን በሚፈሩት ሰዎች ዙሪያ ይሰፍራል ያድናቸዋል (በኢሳ.37÷36) ›› የእግዚአብሔር መልአክ(ቅዱስ ሚካኤል) መጣ፡፡ ከአሞራውያንም ሰፈር መቶ ሰማንያ አምስት ሺህ ገደለ…›› በማለት ቅዱስ ሚካኤል ሕዝቅያስን እንዴት እንዳዳነው ተገልጿል፡፡ በአጠቃላይ ቅዱስ ሚካኤል ያልረዳው ቅዱስ የለም ቢባል ማጋነን አይሆንም፡፡

በዳን.10÷13 ‹‹የፋርስ መንግሥት አለቃ ግን ሃያ አንድ ቀን ተቋቋመኝ፤ እነሆም ከዋነኞቹ አለቆች አንዱ ሚካኤል ሊረዳኝ መጣ›› በማለት የቅዱስ ሚካኤል ተራዳኢነት ተገልጿል /ዳን.10÷21/፡፡

በዚሁ በትንቢተ ዳንኤል ም.12÷1 ላይ ‹‹በዚያም ዘመን ስለ ሕዝብህ ልጆች የሚቆመው ታላቁ አለቃ ሚካኤል ይነሳል በማለት ታላቅነቱን፤ለሰው ልጆች ሁሉ በአማላጅነቱና በተራዳኢነት የሚቆም እንደሆነ በማያሻማ ቃል ተገልጿል፡፡

ከዚህም ሌላ ዲያብሎስ ከነሠራዊቱ በእግዚአብሔር ላይ ባመፀ ጊዜ ከክብሩ ያዋረደው ወደምድር የጣለው ቅዱስ ሚካኤል ቅዱሳን መላእክትን በመምራት ከዲያብሎስና ከሠራዊቱ ጋር ስላደረገው ጦርነትና ስለተቀዳጀው ድል ቅዱስ ዮሐንስ እንዲሀ በማለት ገልጾታል፡፡ ‹‹በሰማይም ሰልፍ ሆነ፤ ሚካኤልና መላእክቱ ዘንዶውን ተዋጉ፤ዘንዶውም ከመላእክቱ ጋር ተዋጋ፡፡ አልቻላቸውምም፤ ከዚያም ወዲያ በሰማይ ሥፍራ አልተገኘላቸውም፡፡ ዓለሙንም ሁሉ የሚያስተው ዲያብሎስና ሰይጣን የሚባለው፡፡ ታላቁ ዘንዶ እርሱም የቀድሞው እባብ ወደ ምድር ተጣለ፡፡ መላእክቱም ከእርሱ ጋር ተጣሉ…›› (ራእ.12÷7-9) ዛሬም ቅዱስ ሚካኤል ሰዳዴ አጋንት አጋንንትን የሚያሳድድ በመሆኑ ከሰይጣንና ከሠራዊቱ መከራ እንዲያድናቸው በጸሎት ለሚለምኑት በቃል ኪዳኑ ለሚማፀኑት ሁሉ ፈጥኖ እየደረሰ ይታደጋቸዋል፡፡ በዙሪያቸው እየከተመ አጥር ቅጥር ሆኖ ይጠብቃቸዋል፡፡ ከክፉ ነገር ሁሉ ያድናቸዋል (መዝ.33÷7)፡፡

በመልእክተ ይሁዳ ቁ.9 ‹‹የመላእክት አለቃ ሚካኤል ግን ከዲያብሎስ ጋር በተከራከረ ጊዜ ስለ ሙሴ ሥጋ ሲነጋገር ጌታ ይገስጽህ አለው እንጂ የስድብን ፍርድ ሊናገረው አልደፈረም›› በማለት ቅዱስ ሚካአል ዲያበሎስን እንኳ እግዚአብሔር ይፍረድብህ ከማለት በቀር ሌላ ቃል አለመናገሩ ታጋሽነቱን ያሳያል፡፡

የቅዱስ ሚካኤል ክብር[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ቅዱስ ሚካኤል ለማንም ያልተሰጠ እጅግ ታላቅ የሆነ ክብር እንደተሰጠው ተጽፎ እናገኛለን፡፡ ይኸውም በዕለተ ምጽአት ጌታችን ቅዱሳን መላእክትን አስከትሎ በክበበ ትስብአት በግርማ መለኮት በሚመጣበት ጊዜ ከእግዚአብሔር ዘንድ በሙታን ላይ ሥልጣን የተሰጠው ለዚሁ ለኃያሉ መልአክ ለቅዱስ ሚካኤል ነው፡፡ ይህንንም ቅዱስ ጳውሎስ በሚገባ ገልጾታል፡፡ ‹‹እነሆ አንድ ምሥጢር እነግራችኋለሁ ሁላችን አናንቀላፋም፡፡ ነገር ግን የኋለኛው መለከት ሲነፋ ሁላችን በድንገት በቅጽበተ ዓይን እንለወጣለን፤ መለከት ይነፋል፤ ሙታንም የማይበሰብሱ ሆነው ይነሣሉ፤ እኛም እንለወጣለን ይላል›› (1ቆሮ.15÷51-52) ከዚሁ ጋር በተጨማሪ ‹‹በጌታ ቃል የምንላችሁ ይህ ነውና እኛ ሕያዋን ሆነን ጌታ እስኪመጣ ድረስ የምንቀር ያንቀላፉትን አንቀድምም ጌታ ራሱ በትእዛዝ በመላእክትም አለቃ ድምፅ በእግዚአብሔርም መለከት ከሰማይ ይወርዳልና በክርስቶስ የሞቱ አስቀድመው ይነሣሉ…›› (1ተሰ..4÷15-16) በማለት በዕለተ ምጽአት ምን ያህል ክብርና ጌትነት እንደሚሰጠው ይገልጽልናል፡፡

የቅዱስ ሚካኤል በዓል[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

የቤተ ክርስቲያን አባቶች በየወሩ በ12 መታሰቢያውን እንድናደርግ አዘውናል፡፡ ይህንንም ያልቻለ በዓመት አራት ዐበይት በዓላትን ከቀዝቃዛ ጽዋ ውኃ ጀምሮ እንደተቻለ ማዝከር ይገባል፡፡ እነዚህም ኅዳር 12 ቀን ቀጥሎ ሰኔ 12 ቀን ከዚያም ነሐሴ 12 ቀንና ታኅሳስ 12 ቀን ናቸው፡፡ ከሁሉም የሚበልጠው ታላቁ በዓሉ ኅዳር 12 ቀን ነው፡፡ በዚህም ዕለት እግዚአብሔር በሰማይ ካሉ ሁሉ በላይ አድርጐ ሾመው፡፡ ስለትሕትናውና ስለ መታዘዙ ጌታውን ፈጣሪውን የከዳና የበጐ ሥራ ሁሉ ጠላት የሆነውን ሰይጣንን ድል ይነሣ ዘንድ ሥልጣን ሰጠው፡፡ በዚህ ዕለት እንዲሁ ከላይ እንደተገለጸው ቅዱስ ሚካኤል በታላቅ ክብር ሆኖ በንጉሥ ጭፍራ አምሳል ለነዌ ልጅ ለኢያሱ የታየበት ዕለት ነው፡፡

በቅዳሴያችን ‹‹ተውህቦ ምሕረት ለሚካኤል፤ ለሚካኤል ምሕረት (ይቅርታ ርኀራኄ) ተሰጠው ይላል፡፡ ነቢዩ ሄኖክም ምሕረት ለሚካኤል መሰጠቱን ገልጿል፡፡ ትሕትናውን ታዛዥነቱን አስረድቷል (ሄኖክ. 6 ቁ.5 ምዕ.10 ቁ.12) ፡፡

የሰማያውያን ሠራዊት አለቃ ለሰው ሁሉ የሚራራና ስለ ሰው ልጆች ሳያቋርጥ ወደ ፈጣሪው የሚለምን ርኀሩኀ ትሑት የሆነው ኃያሉ ቅዱስ ሚካኤል የሠራውን ሥራ የክብሩን ገናንነት ጽፈን ለመጨረስ ስለማይቻለን በዚሁ እናበቃለን፡፡ ጸሎቱ እና በረከቱ፣ ተራዳኢነቱም ሀገራችንና ሕዝባችንን ይጠብቅልን አሜን፡፡

ድርሳነ ሚካኤል ጥር[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም የማይለይ ሦስት የማይከፈል አንድ የማይለይ አኗኗር ያለው።

የኃይል መልአክ የመላእክት አለቃ የቅዱስ ሚካኤልን ድርሳን እናገር ዘንድ ርዳኝ።


የሰማያውያን ሠራዊት መላእክት ሁሉ መሪ። እነዚህም የብዙ ብዙ ናቸው።


በጥር በዐሥራ ሁለት ቀን በመላእክት አለቃ በቅዱስ ሚካኤል በዓል የሚነበብ። ልመናው በረከቱ ከኛ ጋር ይኑር ለዘለዓለሙ አሜን።

ከዚህ የተሰበሰባችሁ ልብ በማድረግ ትሰሙት ዘንድ ይገባል።ከሌሎች ወገኖች ከመላእክት አለቆች ይልቅ የከበረ የመላእክት አለቃ የቅዱስ ሚካኤልን ክብር ታወቁ ዘንድ።


በተፈጥሮ ለሚመሳሰል ሁሉ አለቃ አለውና። መላእክት ሁሉ ፍጡራን ናቸው። ተፈጥሯቸውም ከእሳትና ከነፋስ ነው ይኸውም ሁለት ጠባይ ነው። መሬታውያን ግን ጠባያቸው አራት ነው። እነዚህም ነፋስና አሳት ውሃና መሬት ናቸው። መላእክት ግን ሥጋ የሌላቸው ረቂቃን ናቸው።


በእነሱ ላይ ሞትና ድካም እንደሰው በጋብቻ መቀላቀል የለባቸውም እንዲባዙ የሚያደርግ የሰው ጠባይ የለባቸውም። የሴትና የወንድ ምልክት የለባቸውም። ነገር ግን ዓለም ከተፈጠረ ጀምሮ ዓለም እሰኪያልፍ ድረስ የወረደው እጅግ ብዙ የሆነ ዝናም እያንዳንዱ ነጠብጣብ ቢቆጠር እንኳን ያስበው የማይቀርበት ጌትነቱ የማይጎልበት የአምላክ ቅዱሳን መላእክት እጅግ ከዚያ ይበዘላሉ።


ለሰዎችም ለከዋክብትም እያንዳንዳቸው ሊጠብቋቸው የተመደቡ መላእክት አሏቸው።ወደየክፍላቸውም ይመሯቸዋል ለአራዊትም ለእንስሳም ለአዕዋፍም ለባሕር ዓሣዎች ለሌላውም ለሚነቀሳቀሰው የህይወቱ እስትነፋስ ላለው ለፍጥረቱም ሁሉ ለእያንዳንዱ በልዑል እግዚአብሔር ትእዛዝ ጠባቂ አለው።


ነገር ግን የከበሩ የብርሃን መላእክት የብርሃንን ልጆች ይጠብቃሉ።


እነዚሁም ክርስቲያን ናቸው እሊህ የእግዚአብሔር ወገኖች ናቸው። እሊህ የእግዚአብሔር እስራኤል ናቸው የእውነት ማኅተም ያላቸውን እነዚህም ሁሉንም ለዘለዓለም ሕይወት ይጠብቋቸዋል።


ይሁን እንጂ ጻድቃንንም ኃጥአንንም ቢሆን በልዑል እግዚአብሔር ትእዛዝ ይጠብቋቸዋል።ያለጊዜያቸው እንዳይሞቱ። ለእውነተኛ ሰው ፍርድ እስኪመለስ ድረስ በዚህ ዓለም እግዚአብሔር ወገኖቹን አይጥላቸውምና ብሎ በነቢይ እንደተናገረ።


በወንጌልም ለደጎችም ለክፉዎችም እሱ ቸር ነው እሱ በዚህ ዓለም ለሁሉም በእኩልነት ፀሐይን ያወጣላቸዋል ዝናምን ያዘንምላቸዋል ተብሎ ተጽፏል። በሚመጣውም ዓለም ለሁሉ እንደሥራው ይከፍለዋል ለዘለዓለሙ ክብር ጌትነት ገነዘቡ ነው። እናንተ የክርስቲያን ልጆች መንፈሳውያን የሰውን ልጆች ከሰይጣንና ከሠራዊቱ ተንኮል እንደሚጠብቋቸው እንደ ሚከራከሩላቸው እንደሚዋጉላቸው የቅዱሳን መላእክትን ነገር ስሙ።


ለነቢዩ ለዳንኤል የተገለጠለት መልአክ እንደነገረው እንዲህ ብሎ የፋርስ ንጉሥ አለቃ ሐያ አንድ ቀን ሙሉ በፊቴ ቆሞ ነበር።

እነሆ ከቀደሙት መላእክት አንዱ ሚካኤል ሊረዳኝ መጣ። ከፋርስ ንጉሥ አለቃ ጋር ሊዋጋ እሱን ከዚያ ትቼ በኋላ ዘመን ሕዝብህን የሚያገኛቸውን እነግርህ ዘንድ ወደ አንተ መጣሁ ዳግመኛም ቅዱስ ሚካኤል ስለሰው ሕይወት መላእክትም ስንኳ ለመርዳት ሥልጣን እንዳለው ሲያስረዳው።


በጽድቅ መጽሐፍ የታዘዘውን ልንገርህ በዚህ ነገር ከኔ ጋራ የሚረዳ አለቃቸሁ ነው። አንጂ ሌላ ማንም የለም ብሎታል። መጽሐፍ አለቃችሁ ማለቱ የሚገባ ነው ቅዱስ ሚካኤል ቅዱሳንን ለመርዳት ሰይጣንን ለመውጋት ከኃያላን ፈጣሪ ከእግዚአብሔር የተሾመ ነውና።


ሰይጣንን ከነሠራዊቱ የመታው ከሰማይም ወደምድር አውርዶ የጣለው ኃያል መልአክ ሚካኤል ነው። ምሥጢር የተገለጠለት ዮሐንስ እንዳለ ሚካኤልና ሠራዊቱ በሰማይ አውሬውን ወጉት። አውሬውም ከነሠራዊቱ ተዋጋቸው። ድል ሆነ ከእነግዲህ ወዲህም በሰማይ ቦታ አላገኘም።ያ ታላቅ አውሬ ወደምድር ወደቀ። ታላቁ አውሬም ቀድሞ ዓለሙን ሁሉ ያሳተው ሰይጣን የሚባለው ነው።


እሱ ወደ ምድር ወደቀ ሠራዊቱም ከእሱ ጋር ወደ ምድር ወደቁ። የሰይጣን ሠራዊቶቹም ሥጋ ያልለበሱ መናፍስት ናቸው። ከደመና በላይ የሚኖረ ሰውን የሚያስቱ ርጉማን ወደሰው ልቡና እየገቡ ኃጢአትን የሚያስተምሩ የሳጥናኤል ወገኖች እነዚህ ናቸው።


መፈጠራቸውም እንደመላእክተ ብርሃን ከአላቃቸው ከዲያብሎስ ጋር ከእሳት ከነፋስ ነው። ሳይበድሉ ከበደሉም በኋላ ወራዶች ሆኑ። በቅዱሳን መላእክት ላይ ከአደረ ከጌትነቱ ብርሃን የተራቆቱ ሁነዋልና።ዳግመኛም ቅድስናን ከተቀበሉ በኋላ ርኩሳን ሆነዋልና።


ሦስተኛም ዕውቀቱን ከተቀበሉ በኋላ አላዋቂዎች ሆነዋልና። ስለዚህም ነገር በንስሐ ወደፈጣሪአቸው ይመለሱ ዘንድ አይቻላቸውም ። ነገር ግን ንስሐ በማይጠቅምበት በፍርድ ቀን እንዲጸጸቱ አእምሮ ይሰጣቸዋል። ለሰይጣንና ለመልእክተኞቹ ሁሉ በተዘጋጀ ስቃይ እንዲኖሩ ለእነሱም ከማሳት በቀር ምንም ምን ሥልጣን የላቸውም ።


እነሱንስ እግዚአብሔር ሰውንም እንስሳንም ማንንም ይጠብቁ ዘንድ አይልካቸውም። እነሱ የሚያስቱ የሚጎዱ የተረገሙ እግዚአብሔር የጠላቸው እግዚአብሔርን የሚጠሉ ናቸውና። በውሃ ውስጥና በየብስ የሚኖሩ ሥጋ ያላቸው አጋንንትም አሉ። እነሱ ግን ይጋባሉ ይዋለዳሉ ዳግመኛም ይሞታሉ መልካቸውም ልዩ ልዩ ነው እነሱ ግን ያማሉ እንጂ ማንንም አያስቱም አይገድሉም።


ከእነሱም ተስቦ የሚሆን አለ። ከእነሱም የሆድ በሽታ (ዝማ ተቅማጥ) የሚሆን አለ። ደዌያቸውም ልዩ ልዩ የሆነም አሉ። በዚህ ዓለም ያለነሱ ደዌ የለም። ነገር ግን ያለ እግዚአብሔር ፈቃድ ማንንም መግደል አይቻላቸውም።


ነፍስና ሥጋን የሚዋጉትን እነዚህን አጋንንትና ሰይጣናትን ሁሉ የእግዚአብሔርን ሕዝብ የሚጠብቅ ታላቁ መልአክ ቅዱስ ሚካኤል ያሳድዳቸዋል።


ሚካኤልና ሠራዊቱ ግን የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለመፈጸም የሚፋጠኑ እሳታውያን መንፈሳውያን ናቸው። እሊህ መንፈሳውያን የዘለዓለም ሕይወትን ይወርሱ ዘንድ የታደሉ ቅዱሳንን ለመርዳት ይላካሉ። እነዚህ እሳታውያን ዓመፀኞችን ለማጥፋት ይላካሉ። ዓመፀኞች ሰይጣንና መልእክተኞቹ ግን በእግዚአብሔር መላእክት ፊት በነፋስ ፊት ለፊት እንዳለ ትቢያና ጢስ ናቸው።


የኃያላን ፈጣሪ ረቂቃን መላእክትንም የፈጠረ እግዚአብሔር ኃይሉን የሚገልጥበትን መቅሰፍት ለማምጣት በፈቀደ ጊዜ ታግሦ ታግሦ ለማጥፋት የተዘጋጁትን ቁጣውን የሚገልጥባቸውን መላእክት አመጣል። ዳግመኛም የቸርነቱን ስፋት ለመግለጥ በወደደ ጊዜ ለይቅርታ የተዘጋጁ መላእክትን ያመጣል።

ስለዚህ ቅዱሳን መላእክት ጻድቃንን ይረዳሉ ኃጥአንን ይቀጣሉ እግዚአብሔር ወደ ወደደው የሚልካቸው እሊህ ናቸው። የያፌትን ልጆች ሲቀጡ ሰማንያውን ዕልፍ በአንዲት ቀን የጨረሱ እሊህ ናቸው። ዝሙትን ዋዛ ፈዛዛን ስለአበዙ። እስክንድር ንጉሥ የዘጋባቸው ጎግ ማጎግ አገራቸውን ወረሱ።


በኋላ ዘመን ዓለምን ለማጥፋት የሚመጡት በዚያን ወራት መዓት ጭንቅ መከራ ሕማም ይበዛል። ሰው ሁሉ ሞትን ይሻል አያገኝም። ወደገደልም ቢወርድ ወደጥልቅኢ ባህርም ቢገባ አምስቱ ወሮች እስኪፈጸሙ ድረስ መሞት አይቻለውም።


ስለእነዚያ ዘመኖችም እግዚአብሔር በነዚያ ወራቶች የሌሉ ሰዎች የተመሰገኑ ናቸው አለ ከጭንቁ ከመከራው ጽናት የተነሳ ከዚህ በኋላ ጌታችን በእሑድ ቀን ለመፍረድ ይመጣል። በመጋቢት ወር በሐያ ዘጠኝ ቀን ለማዳን እንደመጣ። ይህችውም ጌታችን ሰው የሆነባት ድኅነት የተደረገባት ወር ናት።


ወደ ቀደመ ነገራችን እንመለስ ለፈጣሪአቸው የሚቀኑ የኃጥአንን ነፍስ እያጣደፉ እያጣደፉ የሚወስዷቸው እሊህ ናቸው። ግርማቸውም ሞት ነው። ከዳዊት ሕዝብ ከነግህ እስከ ሦስት ሰዓት ሰብዓ ዕልፍ የገደሉ አነዚህ ናቸው። ከሰናክሬም ሠራዊት ዐሥራ ስምንት እልፍ የገደሉ እሊህ ናቸው። እንዲሁ እግዚአብሔር ወደ ወደደው ሁሉ ይልካቸዋል።


የወደደውን የሚያደርጉ ቃሉን የሚሰሙ ጽኑዓን ኃያላን ቅዱሳን መላእክተ ብርሃን በየጊዜው በየሥፍራው በከሀሊነቱ ለሚሰጠው ቃል ይታዘዛሉ። ስለዚህም የዘለዓለምን ሕይወት ይወርሱ ዘንድ የታደሉትን ለማገልገል የሚላኩበት ጊዜ አለ። ኢሳያስ እንዳለ።


ከሱራፌል አንዱ ወደኔ ተላከ በእጁም ከመሠዊያው በጉጠት የያዘው እሳት ነበር። ከንፈሬን አስነካኝ እነሆ ከንፈርህን ከዚህ አስነካሁህ ኃጢአትህንም አራቅሁልህ ከበደልህም ያነጻሃል አለኝ። በካህናት አምሳል የሚሠየሙበት ጊዜም አለ ለሱም በየሰዓት የምስጋና መሥዋዕት ይሠዋሉ እንዲህ እያሉ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ አሸናፊ እግዚአብሔር ጌትነትህ በሰማይ በምድር ምሉ ነው።


ከነቢያት ይልቅ ቃሉ የተሰማለት ኢሳይያስ የመለኮትን ምሥጢር ያስተማረ ዮሐንስ እንደተናገረ ዳግመኛም መንበሩን ያጥናሉ ከዕጣናቸውም ጋራ የቅዱሳንን ጸሎት ከምድር ወደ እግዚአብሔር ፊት ያሳርጋሉ።


ስለዚሀም ባለራዕዩ እንዲህ ይላል ከምሥራቅ ሌላ መልአክ መጣ በመሠዊያው ፊት ለፊትም ቆመ በእጁም የወርቅ ጽና ይዟል በመንበሩ ፊት ባለው በመሠዊያው ላይ ለቅዱሳን ጸሎት ማሳረጊያ አድርጎ እንዲያቀርበው ብዙ ዕጣን ሰጡት። የዕጣኑም ጢስ ከቅዱሳን ጸሎት ጋራ ከመልአኩ እጅ ወደ እግዚአብሔር ፊት ቀረበ።


ኃጢአተኞችን በደለኞችን እግዚአብሔርን የካዱትን ለመቅጣት የሚላኩበት ጊዜ አለ። በቅዱስ ወንጌል እንደተባለ። መከሩ የዓለም ፍጻሜ ነው አጫጆቹም መላእክት ናቸው። እንክርዳዱን እንዲለቅሙት በእሳትም አንዲያቃጥሉት። በዓለም ፍጻሜ እንዲሁ ይሆናል የሰው ልጅ መላእክትን ይልካቸዋል ከሕዝብ መሐከልም ከሐዲዎችን ይለቅሙዋቸዋል ወደ እሳት ምድጃም ይጥሏቸዋል በዚያም ልቅሶና ጥርስ ማፏጨትም ይሆናል። ዳግመኛም በዮሐንስ ራእይ መጽሐፍ አንዲህ የሚል ተጽፏል።


ከዚህም በኋላ በሰማይ ያለው የምስክሩ ድንኳን መቅደስ ተከፈተ ሰባት መቅሰፍት የያዙ ሰባት መላእክት ከመቅደስ ወጡ ንጹሕና

ብሩህ ልብስ ለብሰዋል በወገባቸውም የወርቅ ዝናር ታጥቀዋል። ከአራቱ እንስሳትም አንዱ ለሰብአቱ መላእክት ለዘለዓለም ሕያው የሚሆን የእግዚአብሔር ቁጣ የተሞላባቸው ሰባት የወርቅ ጽዋ ሰጣቸው።


ከዚህ በኋላ ከጌትነቱ ከኃይሉ የተነሳ የእግዚአብሔር የቁጣው ጢስ መቅደሱን መላው። ሰባቱ መላእክት ያታዘዙበት ሰብዓቱ መቅሰፍት እስከ ተፈጸም ድረስ ወደ መቅደሱ ሊገባ የሚችል የለም። እሳታውያን ብርሃናውያን የሚሆኑ የቅዱሳን መላእክት የአገልግሎታቸው ሥራ አንዲህ ነው። እሱ ልዑል ተናገረ ተገኙ እሱ አዘዘ ተፈጠሩ ትእዛዝ ሰጣቸው አልተላለፉም።


እሱ ልዑል የወደደውን ይምራል የወደደውን ይቀጣል። መላእክቱ ግን ፈቃዱን የሚፈጽሙ አገልጋዮቹ ናቸው። ልዑል እሱ ይገድላል ያድናል። መላእክቱም ወደ ላካቸው ይላካሉ ትእዛዙንም አይተላለፉም ወደ ላካቸው ይላካሉ ትእዛዙንመ አይተላለፉም። ልዑል እሱ ይገድላል ያደናል። መላእክቱም ወደ ላካቸው ይላካሉ ትእዛዙንም አይተላለፉም።


መላእክትን እንዲያዩት የሚያስመኛቸው የክብር ባለቤት እሱ ነው ከሚያስደንቀው ከገናንነቱ ግርማና ከማይነገረው ከክብሩ ብርሃን የተነሳ ሊያዩት አይችሉምና። ስለዚህም በሁለት ክንፋቸው እግራቸውን ይሸፍናሉ በሁለት ክንፋቸው ፊታቸውን ይጋርዳሉ በሁለት ክንፋቸውም በአንድነት ወደፊት እየበረሩ ቅዱስ ቅዱስ ቅዱስ አሸናፊ እግዚአብሔር ምስጋናህ በሰማይ በምድር ሙሉ ነው ይላሉ።


በሰማያውያን ሠራዊት ሁሉ ላይ አለቃ አድርጎ ቅዱስ ሚካኤልን የሾመው የክብር ባለቤት እሱ ነው። መንፈሳውያን ለሚሆኑ ለብርሃን መላእክት አለቃቸው ሚካኤል ነው። አብ ኪዳኑን ያጸናለት መልአክ እሱ ነው። ልዑል ምክሩን የሚፈጽምበት መልአክ እሱ ነው። እግዚአብሔር ኃይሉን የሚገልጽበት ከፍ ያለ ማዕረግ የተሰጠው መልአክ እሱ ነው። የተመረጡ ሊቃነ መላእክትም እነዚህ ናቸው። እነዚህም ቅዱሳን ሚካኤል ገብርኤል ሩፋኤል ፋኑኤል አፍኒን ራጉኤል ሳቁኤል የኃይላት የመላእክት አለቆች እነዚህ ናቸው።


ነገር ግን አለቃቸው መሪያቸው ቅዱስ ሚካኤል ነው። ስለክብሩ ከፍተኛነትም ለቅዱስ ሚካኤል በቤተ ክርስቲያን በዓል ተሰርቶለታል። በመላእክት አለቃ በቅዱስ ሚካኤል ስም በምስጋና በጸሎት በመመጽወት በጎ ለሚያደርግ ሰው ሁሉ ቅዱስ ሚካኤል ረዳት ጣባቂ ይሆነዋል።


በዚህም ዓለም በሚመጣውም ዓለም ከክፉ ነገር ሀሉ ይጠብቀዋል ያድነዋል።


በሞተ ጊዜም ነፍሱን ተሸክሞ ወደ ደስታ ቦታ ያገባታል ለተላፊኖስ እንደ አደረገለት። ተላፊኖስ የድሃ ልጅ ነበር። አናቱ ግን የመላእክት አለቃ የቅዱስ ሚካኤልን በዓል መታሰቢያ ታደርግ ነበር።እጅግ ባለጠጋ የሆነ እንድ አገረ ገዥ ነበር። በአንዲት ቀንም እርሻውን ሲያሳጭድ የተላፊኖስ እናት አንድ ዓመት የሆነውን ልጅዋን ተሸክማ መጣች።


በአገረገዥው እርሻ ውስጥ ቃርሚያ ትለቅም ጀመር በመሸ ጊዜም ክፉ አገረ ገዥ ከለቀምሽው ፈንታዬን ስጭኝ አላት። ጌታዬ እዘንልኝ አትውሰድብኝ ባል የሌለኝ ድሃ ነኝና ገንዘብም የለኝምና።የሚከኤልም በዓል ደርሶብኛል ከልጅነት ጀምሬ እስከ ዛሬ ድረስ የከበረ የመላእክትን አለቃ የቅዱስ ሚካኤልን በዓል መታሰቢያ አላስታጎልኩምና አለቸው።


ድሃ ሆነሽ ቢሆን የመላእክት አለቃ የቅዱስ ሚካኤልን በዓል መታሰቢያ ባላደረግሽ ነበር።አሁን ድርሻዬን ስጭኝ ድርሻሽን ውሰጂ አላት። ድርሻውን ሰጥታው ሔደች። በነጋው ቃርሚያ ልትለቀም መጣች ብዙ ሰዎች በግራና በቀኙ ያጭዱ ነበር።


አገረ ገዥው ከተላፊኖስ ጋር በእርሻው መካከል ተቀምጦ ሳለ ሚካኤልና ገብርኤል በሰው አምሳል ታይተው አገረ ገዥውን ሰላምታ ሰጡትና ይህ ብላቴና የማነው አሉት። የዚች የድሃ ሴት ልጅ ነው አላቸው ይህ ብላቴና ስለእናቱ በደል በእግዚአብሔር ትእዛዝ ይወርስሃል አሉት።በሱ ዘንድ ማድላት የለበትምና ይህን ብለው ከሱ ተሰወሩ። እሱ ግን አእምሮውን ያጣ ሆነ። እናም ይህን ብላቴና ስጭኝ ላሳድገው አላት።


ከሚካኤልና ከገብርኤል ጋር አደራ ብዬ ሰጥቼሃለሁ አለችው ተቀብሎ ወስዶ በሣጥን አድርጎ ከባሕር ባለው። ዓሣ የሚያጠምድ ሰው ከባሕር ውስጥ አግኝቶ ወደቤቱ ወሰደው በዚያም አገር አደገ። አሥራ ሁለት ዓመት በሆነውም ጊዜ ይህ አገረ ገዥ ወደዚያ አገር ሔደ። ስሙን ተላፊኖስ ብለው ሲጠሩት ሰማ ይህም አገረ ገዥ ይህ ምንድን ነው ምን ማለት ነው አለ። ከውሃ የአገኘነው ማለት ነው አሉት።

በምን ጊዜ በየትስ ወንዝ አገኛችሁት አላቸው። በሣጥን ሆኖ በአንድ ወንዝ ውስጥ አገኘነው ዘመኑም አሥራ ሁለት ዓመት ነው አሉት። እስኪ ሣጥኑን አሳዩኝ አላቸው። ያን ሣጥን አሳዩት። አገረ ገዥውም አይቶ አወቀውና ስለ አልሞተና ስለአመለጠው ጥርሱን አፏጨ። ይህን ባሪያ በዋጋ ስጡኝ አላቸው። በሚስቶቻችን ጡት አድጓልና አንሰጥህም አሉት።


ብዙ ገንዘብ ወርቅና ብር የአሥር ግመል ጭነት ያህል ልብስ እሰጣችኋለሁ አላቸው ሰጣቸው። ዋጋቸውን ተቀብለው እነሱም ተላፊኖስን ሰጡት። ከዚህ በኋላ አገረ ገዥው ይህንን ደብዳቤ ያመጣውን ሰው ራሱን በሰይፍ ቁረጡት ፈጥናችሁ ግደሉት ብሎ ጽፎ ድብዳቤውን ለተላፊኖስ ሰጠው።


ይህን ድብዳቤ ወስደህ ለሚስቴ ስጥ በጉባኤ ያንብቧት አለው። መንገድ የሚመሩት ሁለት ሰዎች ጨመረለት እንደ ይሁዳ በሽንገላ ራሱን ሳመው። ተላፊኖስም ጎዳናውን ሔደ። የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል በጎዳና ተገናኘው። እግዚአብሔር ወደ አንተ

ልኮኛልና ይህን ድብዳቤ አሳየኝ አለው። ጌታዬ አላዘዘኝም ያመነኝን እክዳለሁን አላሳይህም አለው።


የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤልም መግለጡንስ አትግለጥ እንደተጠቀለለ አሳየኝ አለው። ተላፊኖስም ለቅዱስ ሚካኤል አሳየው። ቅዱስ ሚካኤልም ሦስት ጊዜ እፍ እፍ እፍ አለና። የሞቱንም ደብዳቤ ወደ ሕይወት ደብዳቤ ለውጦ ሰጠው። ከዚህ በኋላ ወደ ሰማይ ወጣ። ተላፊኖስም ይህችን ደብዳቤ ወስዶ ለአገረ ገዥው ሚስት ሰጣት።


ሕዝቡ በተሰበሰበበት አደባባይ ተነበበ። መጽሐፉም እንዲህ የሚል ነበር። እኔ መኮንን እገሌ ይህን ዓለም ትቼው ሔጃለሁና ሹመቴንና ገነዘቤን ሁሉ ለልጄ አጋብታችሁ በቦታዬ ላይ አስቀምጡት ። በራሱ ላይም የራስ ወርቅ አቀዳጁት የወርቅ ማርዳ( ኒሻን) ሸልሙት። ይህን ትእዛዝ ያልተቀበለ ሰይፍ ይቅጣው ብላችሁ አዋጅ ንገሩ የሚል ነው።


በውስጡም ከሚስቱ ጋርና ከሌሎችም ጋር የሚተዋወቅበት ምልክት ተገኘች። ደብዳቤይቱም በተነበበች ጊዜ ተላፊኖስን መርተው ያመጡትን ሁለቱን የባሏን አገልጋዮች በእውነት ጌታዬ ይህን ነገር ልኳልን አለቻቸው። ደብዳቤውን ሲሰጠው አይተናል ራሱን ሲስመው ተመልከተናል ለአገሩም ሰው ሁሉ ገንዘቡን ሲበትን አይተናል አሏት።


ሚስቱም ይህን ነገር በሰማች ጊዜ የራስ ጸጉሯን ቆርጣ በራሷ ላይ ትቢያ ነስንሳ ማቅ ለብሳ ታለቅስ ጀመር። ፈት ሁና ተቀመጠች። ያገሩ ሰዎች ግን አገረ ገዥውን ልጅ አጋብተው ዓዋጅ ነግረው ተላፊኖስን ሾሙት። ቅዱስ ሚካኤል ውሃውን ወይን በአደረገው በፈጣሪው ኃይል የሞቱን መልእክት ወደ ሕይወት ለውጦታልና ተላፊኖስ ግን ደግ ቸር ዐዋቂ ሰው ሆነ።


ሁሉን ደስ አሰኘ። የተማረኩትን የተገዙትንም ሁሉ ነጻ አወጣቸው። የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤልም ተላፊኖስን በሕልም ታየው (ተነጋገረው)። እንዲህም አለው ከልጅነትህ እሰከ ዛሬ ድረስ የጠበቅሁህ ስለእናትሀም መገፋት ከብዙ መከራና ከሞት ያዳንኩህ በእሳታውያን ሠራዊት ላይ የተሾምኩ የጌታ የኃይሉ መልእክተኛ እኔ ሚካኤል ነኝ።


ቀጥሎ ያገኘውን መከራ ሁሉ ነገረው። አሁንም ለአንተ በተናገርኩ ጊዜ ለአገረ ገዥው በታየሁበት አርሻ መካከል በኔ ስም ቤተ ክርስቲያን ሥራ። ከጥቂት ዘመን በኋላ ይህ ጎስቋላ አገረ ገዥ ወደ አንተ ይመጣልና የቤተ ክርስቲያን ጠባቂ አድርገው።


ወደዚች ቤተ ክርስቲያን ለሚገባውና ለሚወጣው ሁሉ ኃጢአቱን ይናገር ዘንድ። የሌላውን ገንዘብ በዐመፅ የሚወስዱ ድሆችንም የሚቀሟቸው ባለጾጎች ሁሉ ይገሠጹ (ይመከሩ) ዘንድ። ባለጸጋው ጣታቸውን ነክረው ይሰጡት ዘንድ ውሃ እስከመለመን ደርሶ በሲኦል መከራ እንደ ተቀበለ።


እንደዚሁ ባለጸጎችም ምጽዋት በመስጠት ከአልተባበራቸው በቀር ከድሆች ውሃ እስኪለምኑ ድረስ በሲኦል ይጮሃሉ(መከራ ይቀበላሉ)። ይህችንም እርሻ ለቤተ ክርስቲያኔ መባ ስጠኝ። ይህን ብሎት ከሱ ተሰወረ። ከዚህ በኋላ ተላፊኖስ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል እንደአዘዘው አደረገ። በቅዱስ ሚካኤል ስም ቤተ ክትስቲያን ሰራ። ይህችንም ቤተ ክርስቲያን አከበራት ከፍ ከፍ አደረጋት ያችንም እርሻ ለቤተ ክርስቲያን መባ ሰጠ።


ያ መኮንን ከብዙ ዘመን በኋላ መጣ። እግዚአብሔር እንደ ወደደው ሊቃነ መላእክት ሚካኤልና ገብኤልም እንደ ነገሩት ሆኖ አገኘ። ተላፊኖስም የቤተ ክርስቲያን የእርሻ ጠባቂ አደረገው። ያ መኮንንም የተላፊኖስን ቃል ተቀብሎ የመላእክት አለቃ የቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን አገልጋይ ሆነ።


ኃጢአቱንም ሁሉ ለሰው ነገረ መላ ዘመኑንም በንሰሐ ኖረ። ተላፊኖስ ግን በጸሎትና በምጽዋት መልካም እየሰራ ብዙ ዘመን ኖሮ በሰላም አረፈ። የቅዱስ ሚካኤል ጸሎቱ በረከቱ አማላጅነቱ ከኛ ጋር ይኑር ለዘለዓለሙ አሜን። ይህን ድንቅ ተአምራት ለተላፊኖስ ያደረገለት የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ነው። በደግነቱ ላይ ለሰው ታዛዥ ነውና። ዲያብሎስ ከወደቀ በኋላ ሚካኤል ተሾመ የሚሉ አሉ።


ግን እንደዚህ አይደለም። ዲያብሎስም ሳይወድቅ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል የተሾመ ነውና። እንደዚሁ ሰብዓቱ ሊቃነ መላእክት ከነሠራዊታቸው ነበሩ። መሪያቸው ፈጣሪያቸው ሿሚያቸው እግዚአብሔር ዓለም ከመፈጠሩ አስቀድሞ ከዚያም በኋላ ለዘለዓለም ብቻውን ንጉሥ ነውና።


ከሳኦል በፊት ለእስራኤል እንደነገሠላቸው ነጉሥ እንዲያነግስላቸው በፈለጉ ጊዜ ግን እግዚአብሔር ሳሙኤልን ሕዝቡ የሚሉህን ቃላቸውን ስማቸው እኔን ናቁ እንጂ አንተን የናቁ አይደለምና። የሚገዛቸውን ንጉሥ እንግሥላቸው የንጉሡን አገዛዝ ንገራቸው። ስለዚህም ለክብር ፍላጎት የሚሆን እንዲህ ዓይነት ነገር ሰዎች ሊለምኑ አይገባቸውም።


ይህን አድርግልን ብለው የሚገባውንና የማይገባውን አያውቁምና። አንተ እግዚአብሔር የሚሻለንን የሚበጀንን አድርግልን እያሉ ቸርነቱን ጌትነቱን ይለምኑ እንጂ አሁንም ሰባቱ አለቆች ከሠራዊቶቻቸው ጋር አሉ። ዘጠኙ መዓርጋት ናቸው። ጌታው ጴጥሮስን የአንዱ ነገድ ርቀት የሰማይና የምድር ያህል ነው ብሎታልና።


መልካቸውንም ሊያዩ ቢወዱ የሚያበራ የብርሌ ባሕርን ይመለከታሉ። መልካቸውን አይተው የሁሉም መገኛ የመላእክትን ፈጣሪ ያመሰግናሉ። አንዱ አለቃ ግን ከሠራዊቱ ጋር ወደቀ። ዲያብሎስ ለአዳም መስገድን እምቢ ስለአለ። ወደቀ የሚሉ አሉ።


በቅዱስ ጊዮርጊስ ገድል መጽሐፍ ተጽፎ አለና ጊዮርጊስ ግን እንዲህ አላለም እሱ ርኩስ መንፈስ ለአዳም መስገድን እምቢ ብል ጣለኝ አለ አንጂ ይኸው ሐሰት ነው። ሐሰተኛ ነውና የሐሰትም አባት ነውና። ፈጣሪያችንስ ሰው ከመሆኑ አስቀድሞ ለፍጥረቱ ይሰግዱ ዘንድ መላእክትን አላዘዛቸውም።


ሰው ከሆነ በኋላ ግን ኃይል ባለው ክብር በተቀመጠ ጊዜ ፍጥረቱ ሁሉ ለዚህ ሥጋ ሰገዱለት ያውም ቢሆን አዳም ከዕለተ ዓርብ አስቀድሞ አልተፈጠረም ነበር። ዲያብሎስም የወደቀ አዳም ሳይፈጠር አስቀድሞ በዕለተ ረቡዕ ነው።


እግዚአብሔር በመጀመሪያ ቀን እሑድ ሰማይንና ምድርን ውሃንና መሬትን ነፋስንና እሳትን መላእክትን ጨለማን ብርሃንን ፈጥሯልና። በሁለተኛው ቀን ውሃውን ከፈለ ጠፈርንም ፈጠረ ያንንም ጠፈር ሰማይ አለው። በሦስተኛው ቀን ሣርን ቅጠልን ፈጠረ። በአራተኛው ቀን ፀሐይን ጨረቃን ከዋክብትን ፈጠረ።


በሰማይ ጠፈር ሁነው በምድር ላይ ያበሩ ዘንድ። ሰይጣን የብርሃናትን መልክ በአየ ጊዜ ዙፋኔን በነሱ ላይ አስቀምጣለሁ ጌታንም እመስለዋለሁ አለ። ያን ጊዜም ወደቀ። በአምስተኛው ቀንም በባሕር ውስጥ የሚላወሰውን የሚንቀሳቀሰውን ፈጠረ።


በዕለተ ዓርብም እንስሳትን አራዊትን አዕዋፍን የሕይወት እስተንፋስ ያለውንም ሁሉ ከምድር ፈጠረ ከነሱም በኋላ የመጀመሪያውን ሰው አዳምን በመልኩ በአምሳሉ ፈጠረ። በሰባተኛው ቀንም ከሥራው ሁሉ አረፈ። ክብር ምስጋና ለሱ ይሁን ለዘለዓለሙ አሜን።


የክርስቲያን ወገኖች ምእመናን የመላእክት አለቃ የቅዱስ ሚካኤልን በዓል በየወሩ አድርጉ በዚህ ዓለም በረከት ይሰጣችሁ ዘንድ። በሚመጣውም ዓለም በክንፉ ባሕረ እሳትን ያሻግራችሁ ዘንድ። እኛንም ያሻግረን ለዘለዓለሙ አሜን።ከእሳት ከነበልባል የተፈጠረ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል የአደረገው ተአምር ይህ ነው። ልመናው በረከቱ አማላጅነቱ ከአገልጋዩ ከሁላችንም ከሕዝበ ክርስቲያን ጋር ይኑር

አዲሶቹ የወንጌል አታክልት ከሆነው የኢየሱስን ደም ከተቀባነው ጋር ይሁን። ከክፉ ዘመን መከራም ያድነን ለዘለዓለሙ

አሜን።


በአንዲት አገር ለበጎ ሥራ እጅግ የሚተጋ እግዚአብሔርን የሚፈራ ትእዛዙን የሚሰራ የክርስቲያን ወገን የሆነ አንድ ሰው እንነበረ ተነገረ። የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤልን ይወደው ነበር። ደስ እያለው መታሰቢያውን እያደረገ ኖረ።


እረሱም በእርሻ ሥራ ይኖር ነበር። የራሱን ነፍስ የሚያድንበት ምግብ ይሆነው ዘንድ። ቀድሞ ደስ እያለው የቅዱስ ሚካኤልን በዓል መታሰቢያ ያደርግ ነበር። ብዙ ገንዘብ አግኝቶ ነበር። እጅግ ከበረ። በአንዲት ዓመትም በእርሻው ውስጥ የዘራው አዝመራ በጅቶለት ነበር። ስንዴው እህሉም ሁሉ በየዓይነቱ ብዙ ነበር።


ግን እንደቀድሞው ሥራው አላደረገም። የመላእክትን አለቃ የቅዱስ ሚካኤልን በዓልም አላሰብም። በእርሻው ሁሉ ክፉ ወጥቶ የምድሩን አዝመራ ሁሉ በላው እጅግ ያማረውን እርሻ ሁሉ አጠፋው። ትልቅ መከራ በመጣበት ጊዜም ፅኑ ድንጋጤ ደነገጠ።


የመላእክትን አለቃ የቅዱስ ሚካኤልን በዓል ስለአስታጎለ የምድሩ ፍሬ ሁሉ ጠፍቷልና። ከዚህ በኋላ የመላእክትን አለቃ የቅዱስ ሚካኤልን በዓል መታሰቢያ ሥራን በትጋት አሰበ። በፍጹም ትጋት ንሥሐ ገባ የቅዱስ ሚካኤልን በዓል መታሰቢያም እንደ ቀድሞው ያደርግ ጀመር ባለ ዘመኑ ሁሉ በጎ መሥራትን ቸል አላለም። እግዚአብሔርም ፍጹም በረከቱን አላሳጣውም።


መሐሪ ይቅር ባይ ነውና። የምህረትና የይቅርታ መልእክተኛ በሚሆን በቅዱስ ሚካኤል ጸሎት ንስሐውን ተቀበለው። ቅዱስ ሚካኤልም የቀድሞ ቸርነቱን አልዘነጋበትም። ዳግመኛም የምድሩን ፍሬ አበዛለት ተመልሶ እንደ ቀድሞው ሆነ። ምንም ምን ትል አልነካውም። በላዩ የእግዚአብሔር ጸጋ አደረበት በቤቱም የመላእክት አለቃ የቅዱስ ሚካኤል በረከት ሞላበት። በእርሻውም በገዛውም ሁሉ። ሀብቱም ከቀድሞው ይልቅ በዛ። በመላእክት አለቃ በቅዱስ ሚካኤል አማላጅነት።


ያም ሰው በጎ አድራጎትን አበዛ።ለድኆች ለችግረኞች ምጽዋት ለመስጠት እጁን ዘረጋ። በመላእክት አለቃ በቅዱስ ሚካኤል ስም በመታሰቢያው ቀን ምጽዋትን ያደርግ ነበር። ይህን ሲያደርግ ኖሮ በጎ ዕረፍትን ዓረፈ። በመላእክት አለቃ በቅዱስ ሚካኤልም አማላጅነት መንግሥተ ሰማያት ገባ።


ልመናው በረከቱ ይደርብንና ለዘለዓለሙ አሜን።


አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም።


ጥር አሥራ ሁለት ቀን በዚች ዕለት የመላእክት አለቃ የቅዱስ ሚካኤል በዓል መታሰቢያ ነው። በዚች ቀን እግዚአብሔር የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤልን እስራኤል ወደ ተባለ ወደ ያዕቆብ ልኮታልና።


ወንድሙን ኤሳውን ሲፈራ ከእሱም አዳነው የዮርዳኖስንም ወንዝ አሻገረው ወደ እናቱ ወንድም ወደ ላባ ሔደ ሁለቱን ልጆቹን ልያንና ራኄልን አጋባው። ጎዳናውን እየጠረገ በፍቅር በደኅና አገሩ መለሰው። ከልጆቹ ከቤተሰቡ ከገንዘቡ ጋር። ወንድሙ ኤሳውም በፍቅር በሰላም ተቀበለው። ስለዚህ ነገር በየወሩ በአሥራ ሁለት ቀን የመላእክትን አለቃ የቅዱስ ሚካኤልን በዓል መታሰቢያ እናደርግ ዘንድ የቤተ ክርስቲያን መምህራን አዝዘውናል።


ፍጹም አማላጅነቱ ከኛ ጋር ይኑረ ለዘለዓለሙ አሜን።

ድ. ቅ. ሚ. ዘታህሣሥ [ለማስተካከል | ኮድ አርም]

በአንዲት አገር እግዚአብሔርን የሚፈራ አንድ ደግ ሰው ነበረ። ለድሆች ለችግረኞች ምጽዋት ያደርግ ነበር። የመላእክት አለቃ የቅዱስ ሚካኤልን ምልጃ ተስፋ አድርጎ በየወሩ በአሥራ ሁለት ቀን መታሰቢያውን ያደርግ ነበር። ይህም ሰው የእርሻ ሥራ ይሠራ ነበር። ከዚህ ነገር በኋላ በአንዲት ዘመን በአለበት አገር መከር ጠፋ። ይህም እግዚአብሔርን የሚፈራ ደግ ሰው አስቦ ለመላእክት አለቃ ለቅዱስ ሚካኤል መታሰቢያ ምን አደርጋለሁ አለ። ደሃና ጦም አዳሪ ሆኗልና በቤቱም ምንም አልነበረውም ችግር ጸናበት የሚበላው የሚጠጣው የሚለብሰውም አጣ የዕለት ምግብ አጣ።ጽምና ረኃብ ችግር ያዘው። ጽኑ ኃዘንም አገኘው። ኃይሉ ደከመ ብርታቱም ጠፋ። ከተቀመጠበትና ከተኛበት መነሳት ተሳነው። ከረኃቡም ጽናት የተነሳ አዝኖ ተኛ። በዚያች ቀን እንደሞተ ሰው ሆነ። በዚያች ሰዓት ስለሰው ሁሉ ይቅርታን የሚለምን የመላእክት አላቃ ቅዱስ ሚካኤል ፈጥኖ ወደሱ መጣ። በደግነቱ ላይ ለሰው ታዛዥ ነውና። ለደግነቱም መጠን የለውምና። ለዚያም ሰው ተገለጠለት አረጋጋው አጽናናው መታሰቢያዬን የምታደርግልኝ ወዳጄ ሆይ ለምን ታዝናለህ ለምንስ ትተክዛለህ በጧት ፈጥነህ ተነሥ። ልቡናህ ይጽና ኃይልህም አይድከም። ወደ ባሕር ዳርቻ ፈጥነህ ሒድ መረብህን በባሕር ላይ ጣል። ታላቅ ዓሣም ይገባልሃል እግዚአብሔርም ክብርን ብዕልን ከሱ ይሰጥሃል። በውስጡ ብዙ በረከት ታገኛለህ እኔም ከአንተ አልለይም አብሬህ አኖራለሁ። አልለይህም ቸል አልልህም ፈጽሞ በችግር ላይ አልጥልህም በእግዚአብሔር ኃይል ከአንተ ጋር ይኑር አለው። ይህን ከአለው በኋላ የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤል ከሱ ተሰወረ ወደሰማያትም ወጣ። ይህም ሰው ከእንቅልፉ በነቃ ጊዜ ይህ ነገር ከእግዚአብሔር ዘንድ አንደሆነ ዓወቀ። በነጋ ጊዜ ኃይል አግኝቶ ተነሳ የእግዚአብሔር መልእክተኛ ቅዱስ ሚካኤል እንደነገረው ወደ ባሕር ዳርቻ ፈጥኖ ሒዶ ከባሕር ላይ መረቡን ጣለ። የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤልም እንደ ነገረው ታላቅ ዓሣ ተያዘለት። አፉንም በከፈተ ጊዜ የጠራ የነጠረ ወርቅ አገኘ። ከዚህ በኋላ እጅግ ደስ አለው። እግዚአብሔርን አመሰገነው የመላእክት አለቃ ቅዱስ ሚካኤልንም አሰበው በጽኑ ችግሩ ጊዜ አልተለየውምና። ይህንንም ወርቅ ይዞ በታላቅ ደስታ ወደ ቤቱ ገባ። ከዚህ በኋላ ከዚሁ ወርቅ በአማረ ሽልማት አስጊጦ የመላእክትን አለቃ የቅዱስ ሚካኤልን ሥዕል አሠራ። በታላቅ ክብር በከበረች ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሰቅሎ አኖረው።እስከ ሚሞትበትም ጊዜ ድረስ በየወሩ በአሥራ ሁለት ቀን የመላእክት አለቃ የቅዱስ ሚካኤልን መታሰቢያ ማድረግ አላስታጎለም።

ፍጹም ልመናውና አማላጅነቱ ከእኛ ጋር ይኑር ለዘለዓለሙ አሜን።