በር:ሒሳብ/መግቢያ

ከውክፔዲያ
Jump to navigation Jump to search


የሒሳብ ስራና ግንዛቤ እሚከወነው በአእምሮ እንደመሆኑ የዕውቀቱ መሰረቶች ለቂቅ ሃሳቦችና በነርሳቸውም መካከል ያለ መመሳሰል እና ልዩነት ነው። ቁጥር የሒሳብ ዕውቀት መሰረታዊ ገንዘብ ነው ፤ አመጣጡም ለምሳሌ በአራት ድንጋዮችና በአራት ወፎች መካከል አንድ የጋር ነገር እንዳለ፣ ያም ብዛታቸው እንደሆነ ከመረዳት ነው። አራትነት ለቂቅ ነው ይተባለበት ምክንያት በተጨባጭ ያለ ነገር ሳይሆን፣ አዕምሮ ከተሰጡት የማይመሳሰሉ ሁለት ዓይነት ነገሮች አላቆ ያወጣው የጋራቸው ሃሳብ መሆኑ ነው። ከቁጥር ተጨማሪ ቅርጽአደረጃጀት፣ እና ለውጥ በሒሳብ የሚጠኑ ሌሎቹ ለቂቅ ሃሳቦች ናቸው።

አንድ የሒሳብ ጽንስ ዕውነት መሆኑ የሚረጋገጠው ከሒሳብ ውስጣዊ ስነ አመክንዮ እና ከመሪ ሃሳቦቹ አንጻር ብቻና ብቻ ነው። ስለዚህም በሒሳብ ስራ ውስጥ ለመሳተፍ አንድ ሰው ማዕረግም ሆነ ስልጣን በምንም መልኩ አያስፈልገውም። ሐቀኝነት፣ ግልጽነት፣ አዲስ የመፍጠር ፍላጎት፣ እርሳስና ወረቀት ለሒሳብ ስራ አስፈላጊና በቂ ጥሬ ዕቃዎች ናቸው።

አዳዲስ የሒሳብ ቅርንጫፎች በፍጥነት እየበቀሉ እና እየተስፋፉ ባለበት በአሁኑ ወቅት በዚያው ልክ ከዛሬ ሶስትና አራት ሺህ ዓመታት በፊት በግብጽና በባቢሎን ይሰራባቸው የነበሩ የሒሳብ ስሌቶች ያለምንም ለውጥ አሁን ድረስ ያገለግላሉ። ይሄ የሚያሳየው የዕውቀቱን አስተማማኘትና የዘዴውን ብቃት ነው።:መደብ:ሥነ ቁጥር