ቡሩ

ከውክፔዲያ

ዳንጉን ቡሩ (부루) በኮርያ ልማዳዊ አፈ ታሪክ በጥንታዊ ኮርያ (ጎጆሰን) የነገሠ ንጉሥ ነበር። እርሱ ከአባቱ ዳንጉን ዋንገም መንግሥት ቀጥሎ ገዛ።

በጠቅላላ ለ፶፰ ዓመታት እንደ ነገሠ ይጻፋል። ከዚያ በኋላ ልጁ ካርግ ተከተለው።

ኋንዳን ጎጊ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

በ1903 ዓም. በኮሪይኛ የተዘጋጀው ዜና መዋዕል ኋንዳን ጎጊ ስለዚሁ አፈታሪካዊ ዘመን መረጃ ይሰጣል፤ ሆኖም በብዙ የኮርያ መምህሮች ዘንድ ይህ መጽሐፍ እንደ ትክክለኛ ታሪክ አይሆንም። ቡሩ ካደረጉት ሥራዎች መካከል ዋና ዋናዎቹ እንዲህ ናቸው፦

በ2042 ዓክልበ. ግድም ዳንጉን ዋንገም አልጋ ወራሹን ልዑል ቡሩ በተልእኮ ወደ ዩ ላከው፣ ይህ ምናልባት በኋላ ዳ ዩ የተባለው የኋሥያ (ቻይና) አለቃ ይሆናል።

በ2015 ዓክልበ. ግድም ዳንጉን ዋንገም አረፈ፣ ልጁም ዳንጉን ቡሩ ያንጊዜ የጆሰን ዳንጉን (ንጉሥ) ሆኖ ተከተለው። የእርሻ እና የመስኖ ሥራ ወዘተ. ያበረታ ነበር።

በ2013 ዓክልበ. ግድም ቡሩ ሕዝቡን ሁላቸው ሰማያዊ አለባበስ እንዲለብሱ፤ ጽጉራቸውንም በሹሩባዎች እንዲያደርጉት አዘዛቸው። የክብደት መላኪያዎች ወዘተ መደበኛ ተደረጉ፤ የጨርቃጨርቅም ዋጋ መደበኛ ተደረገ።

በ1964 ዓክልበ. የፀሐይ ግርዶሽ በኮርያ ታየ፤ በዚያም ቀን ቡሩ ዓረፈ፣ ካርግም ተከተለው።


ቀዳሚው
ዳንጉን ዋንገም
ጆሰን ዳንጉን
2015-1964 ዓክልበ. ግድም
ተከታይ
ካርግ

ዋቢ ምንጭ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]