ቫንዳሉስ

ከውክፔዲያ

ቫንዳሉስ (በጀርመንኛ ቫንድለር) በጀርመን አፈ ታሪክ ዘንድ በጥንት የጀርመን ፱ኛው ንጉሥ ነበረ። ከአባቱ ሷይቩስ ቀጥሎ ለ41 ዓመታት (ምናልባት 1923-1882 ዓክልበ. ግድም) ነገሠ።

በተለያዩ ምንጮች ዘንድ ይህ ቫንዳሉስ በጌርማኒያ የኖረውን ቫንዳላውያን ብሔር መሠረተ፤ ከነርሱም አንዳንድ ሕዝቦች፦ ቡርጉንዳውያንአላኖችዌንዳውያን ይጠቀሳሉ። በታወቀው ታሪክ፣ ቫንዳሎቹ በ፭ኛው ክፍለ ዘመን በሮሜ መንግሥት ውድቀት ጊዜ ከጌርማኒያ ወጥተው እስከ ዛሬው ቱኒዚያ ድረስ ፈለሱ።

አቬንቲኑስ እንደ ጻፈው በዚህ ጊዜ አትላስ ኪቲምእስፓንያ ገዛ። ስለ ቫንዳሉስ መንግሥት ብዙ ሌላ ዝርዝር አይሰጠም። ከ፵፩ ዓመታት በኋላ በልጁ ቴውታኔስ እንደ ተከተለ ይባላል።

ቀዳሚው
ሷይቩስ
የቱዊስኮኔስ (ጀርመን) ንጉሥ
1923-1882 ዓክልበ. ግድም
ተከታይ
ቴውታኔስ