ቴውታኔስ

ከውክፔዲያ

ቴውታኔስ (በጀርመንኛ Deuto ዶይቶ) በጀርመን አፈ ታሪክ ዘንድ በጥንት የጀርመን ፲ኛው ንጉሥ ነበረ። ከአባቱ ቫንዳሉስ ቀጥሎ ለ27 ዓመታት (ምናልባት 1882-1855 ዓክልበ. ግድም) ነገሠ።

አቬንቲኑስ እንደ ጻፈው በእርሱ ምክንያት የብሔሩ ስም ከ«ቱዊስኮኔስ» ወደ «ቴውቶኔስ» ተቀየረ። ቴውቶኔስ የተባለው ነገድ በታሪክ የሮሜ መንግሥትን ወርረው በ109 ዓክልበ. ተሸነፉ። እስካሁን ድረስ ግን የጀርመናዊ ቋንቋዎች ቤትሠብ በሙሉ «ቴውቶኒክ» ሊባል ይችላል። ኢንዲሁም በዘመናዊ ጀርመንኛ ለራሳቸው ያላቸው ስያሜ «ዶይች»፣ «ዶይችላንድ» ከዚህ መነሻ ነው። (/ዶይች/ < /ቴውቲስክ/።)

በተጨማሪ እንደ ጀርመናዊው ሜርኩሪዩስ መቆጠሩ ሆነ ሲለን ስሙ ከጀርመናዊው አረመኔ አምላክ «ቲው» ጋር ግንኙንት እንዳለው ማለት ነው። ይህ ስያሜ በጀርመናዊ ቋንቋዎች እስከ ዛሬ ድረስ በማክሰኞ ስም (ለምሳሌ «ቲውዝደይ» በእንግሊዝኛ) ቆይቷል።

አቬንቲኑስ እንዳለው ይህ ንጉሥ ቴውታኔስ በጎረቤቱ አገር በኬልቲካ ውስጥ (የአሁን ፈረንሳይ) ጦርነት አደረገ፤ ወርሮት ለግዛቱ ከተሞች በ«ቪንደን» (አሁን ቫን)፤ በ«ሰነን» (አሁን ሳንስ)፣ «ሳንትነር» (አሁን ሰንት) እና «ቴውቶሴክ» (አሁን ቱሉስ) ነበሩት።[1]

ቀዳሚው
ቫንዳሉስ
የቴውቶኔስ (ጀርመን) ንጉሥ
1882-1855 ዓክልበ. ግድም
ተከታይ
ሄርኩሌስ አለማኑስ
  1. ^ የአቨንቲኑስ ታሪክ (በጥንታዊ ጀርመንኛ)