ሷይቩስ

ከውክፔዲያ

ሷይቩስ (ወይም ሿብ) የጀርመን መምኅር ዮሐንስ አቬንቲኑስ ባሳተመው ዜና መዋዕል ዘንድ፣ በጥንት የጀርመን አገር ፰ኛው ንጉሥ ነበረ። በሮማይስጥ እንደ ጻፈው፣ ከአባቱ ጋምብሪቪዩስ ቀጥሎ ለ52 ዓመታት (ምናልባት 1975-1923 ዓክልበ. ግድም) ነገሠ። (በጀርመንኛ በጻፈው ዕትም ግን ለ46 ዓመታት እንደ ነገሠ ይላል።) በዮሐንስና ሌሎች ምንጮች ዘንድ ይህ ሷይቩስ በጌርማኒያ የኖረውን ስዌቪ ብሔር መሠረተ፤ ከርሱም ብዙ ሕዝቦች ወጡ ወይም ተከፈሉ፦ አንግሊላንጎባርዲማርኮማኒኳዲሩግያውያን፣ የስዊድን ሰዎች፣ የስካኒያ ሰዎች፣ ሲቶናውያንሲሌስያውያንሊቮንያውያን ይዘርዝራል። በታወቀው ታሪክ፣ እነዚህ ስዌቪ በ፭ኛው ክፍለ ዘመን በሮሜ መንግሥት ውድቀት ጊዜ ከጌርማኒያ ወጥተው እስከ ዛሬው ፖርቱጋልስፔን ድረስ ፈለሱ።

ብሔራቸው በተለይ ከኤልበ ወንዝኦደር ወንዝ መካከልና ከዚያ ወደ ደቡባዊ ስዊድን አገር ሲሆን፣ ማርኮማኒ የተባሉት ግን ከኤልበ ምዕራብ እስከ ዳኑብ ወንዝ ድረስ፤ ሲቶናውያንም ከኦደር ምሥራቅ እስከ ቪስቱላ ወንዝ ድረስ እንደሠፈሩ ይላል። በምሥራቃቸው ደግሞ ጌታያውያንዳክያውያን ብሔሮችና የካርፓትያ ተራሮች ወሰናቸው። አንዳንዴም ሷይቩስ የዙሪክ መሥራች ተብሏል።[1]

በሷይቩስ ዘመን ሄርኩሌስ ሊቢኩስእስፓንያ ነግሦ ካረፈ በኋላ (1929 ዓክልበ.) እናቱ ኢሲስ (የኦሲሪስ አፒስ ንግሥት) ወደ ጀርመን ወደ ሷይቩስ መጣች፤ እህሉን መዝራትና መፍጫት፣ ዳቦን መጋገር፣ ሱፍን መፈተል፣ የዘይትና የወይን ጥቅም እንዳስተማረች ይባላል። ስለዚህ ነው ሕዝቡ እንደ አምላክ የቆጠራት። ምልክቷንና አረመኔ ሥርዓቷን በጀርመን ከሊቡርኒያ ኢንዳስገባች ይለናል። ከዚያ ጀርመንን ትታ ወደ ጣልያን ሄደች። ሷይቩስ በርሱ በኩል ደግሞ እንደ አምላክ ይቆጠር ጀመር ይላል አቨንቲኑስ። ከዚያ ልጁ ቫንዳሉስ ተከተለው።

ቀዳሚው
ጋምብሪቪዩስ
የቱዊስኮኔስ (ጀርመን) ንጉሥ
1975-1923 ዓክልበ. ግድም
ተከታይ
ቫንዳሉስ
  1. ^ የስዊስ ዜና መዋዕል 1596 ዓ.ም. (ጀርመንኛ)