Jump to content

ትንቢተ ዘካሪያስ

ከውክፔዲያ
ዘካሪያስ ያያቸው አራቱ ሰረገሎች(ም.6) በሰአሊ ጉስታቭ

ትንቢተ ዘካርያስብሉይ ኪዳን ከአስራ ሁለቱ ታናናሽ ነቢያት መካከል የሚካተት ሲሆን ጸሃፊውም ነብዩ ዘካሪያስ ነው። የተጻፈውም ከባቢሎን ምርኮ ለተመለሱ አይሁድና ለወደፊት አንባቢያን ሁሉ ነው።

አይሁድ 587/586 ዐ.ዐ በናቡከደናጾር ወደ ባቢሎን ከተማረኩ በኋላ በኤርምያስ አስቀድሞ እንደተነገረው ትንቢት በቂሮስ ዘመን ወደ እየሩሳሌም ይመለሳሉ። ከቂሮስ በኋላ የመጣው ዳሪዮስዘሩባቤልን በይሁዳ ሾመው። ዘካሪያስ ከነቢዩ ሃጌ ጋር በተመሳሳይ ጊዜ ያገለገለ ነብይ ሲሆን ወቅቱም በዚህ በዳርዮስ ዘመነ መንግስት ነበር። ነብዩ ዘካሪያስ አገልግሎቱን የጀመረው ሃጌ ትንቢት መናገር ከጀመረ ከሁለት ወር በኋላ ሲሆን የመጨረሻው ትንቢትም ከሃጌ ትንቢት ሁለት አመት በኋላ ነበር። ዘካሪያስ ያገለገለበት ዘመን በትንቢተ ዘካሪያስ ምዕራፍ 1 ፡ 1 ላይ “በዳርዮስ በሁለተኛው ዓመት በስምንተኛው ወር የእግዚአብሔር ቃል ወደ አዶ ልጅ ወደ በራክዩ ልጅ ወደ ነቢዩ ወደ ዘካርያስ እንዲህ ሲል መጣ” በማለት በግልጽ ተቀምጧል። ዘመኑም 520 እስከ 518 ዐ.ዐ ነበር። ዘካሪያስ አይሁድ የጀመሩትን የቤተመቅደሱን ግንባታ እንዲያጠናቅቁ ያበረታታቸው ነበር።

ዋና መልዕክቱ እግዚአብሄር በስራ ላይ እንደሆነና ህዝቡን ከጠላቶቻቸው ለማዳንና ከሃጥያታቸው ለማንጻት ያለውን እቅድ ያሳያል። መጽሀፉ በምዕራፍ 1-6 ለህዝቡ ንስሀ እንዲገቡ ከእስራኤል ታሪክ በማስታወስ ሲጀምር እስከ ምዕራፍ 6 ዘካሪያስ ያያቸውን 8 ራዕዮች ያስከትላል።

  1. ባርሰነት ዛፎች መካከል የቆመ ሰው ራዕይ እግዚአብሄር ለእስራኤል ምድር የሚያደርገውን ጥበቃና እንከበካቤ ያሳያስል
  2. እስራኤልና ይሁዳን የበታተኑ ሁለት ቀንዶችና አራቱ ሙያተኞች
  3. የመለኪያ ገመድና ታላቂቱን እየሩሳሌም ፤ እየሩሳሌም ከሰፋቷ የተነሳ ቅጥር እንደሌላት ከተማ ትሆናለች
  4. ስለ ሃጥያት ይቅርታና ስለ ካህናት አገልግሎት ተሃድሶ የካህኑ እያሱ ያደፈ ልብስ መቀየር
  5. የወርቁ መቅረዝና ሁለቱ የወይራ ዛፎች እስራኤል በመንፈስ መሞላት ሁለቱ የወይራ ዛፎች ዘሩባቤልና እያሱ
  6. የበራሪው ጥቅል ራዕይ ፤ በፍጥነት እየመጣ ያለውን ፍርድ ያመለክታል በተለይም ለሌቦችና ለሃሰተኞች
  7. የቅርጫቱ ራዕይ ፤ ሃጥያትና እርኩሰትን ያመለክታል ፤ ወደ ባቢሎን መወሰዱም ባቢሎን በሃጥያት እንደምትቀጥል ያሳያል።
  8. የአራቱ ሰረገሎችህ ራዕይ ፤ የክርስቶስ መንግስት መምጣት

የብርና ወርቅ አክሊል በዘካሪያስ በኢያሱ ላይ መሆን የመሲሁን ንጉስና ካህን መሆን ያመለክታል

ከምርኮ ለተመለሰው ህዝብ ጾሙን እግዚአብሄር ይቀበለው እንደሆነ ለማወቅ ዘካሪያስን ይጠይቃሉ። ጾማቸው ተቀባይነት ሚኖረው ከተግባራቸው ጋር ልባቸው ሲመለስ መሆኑን ይነግራቸዋል።

የመጨረሻዎቹ ሁለት ትንቢቶች እስራኤል ሰለሚታየው ተሃድሶና ብልጽግና የሚናገሩ ናቸው።

ስለ አለም ገዥ ም.9-14

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ሁለት ሸክሞችን በመግለጽ ይጀምራል

  • ስለ ጨቋኝ ግሪኮችና ሮማዊያን በመሲሁ ላይ አይሁድ በሚያደርሱት ተቃውሞ ይጠናቀቃል
  • ጭቆናን የሚያመለክቱ የወደፊት ሁኔታዎችን ያመለክታል
  • የመጨረሻው ምዕራፍ በክርስቶስ የሚመራውን ድል አድራጊ ሰራዊትና የክርስቶስን ንጉስ መሆን ያመለክታል

መሲሃዊ ትንቢቶች

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

በዘካሪያስ ስለ ክርስቶስ በርካታ ትንቢቶች ተጽፈው ይገኛሉ። ክነዚህም መካከል

  • በክርስቶስ አህዛብ ስለሚደርሳቸው መዳንና የእግዚአብሄር ህዝብ መሆን 1፡11በዚያም ቀን ብዙ አሕዛብ ወደ እግዚአብሔር ይጠጋሉ፥ ሕዝብም ይሆኑኛል
  • ስለ ክርስቶስ የዳዊት ስር መውጣት 3፡8 እኔ ባሪያዬን ቍጥቋጥ አወጣለሁ
  • ስለ ክርስቶስ ንግስናና የአህዛብ ወደ እግዚአብሄር ቤተክርስቲያን መምጣት 6፡12 እንዲህም በለው፦ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እነሆ፥ ስሙ ቍጥቋጥ የሚባል ሰው በስፍራው ይበቅላል፥ የእግዚአብሔርንም መቅደስ ይሠራል። 13 እርሱ የእግዚአብሔርን መቅደስ ይሠራል፥ ክብርንም ይሸከማል፥ በዙፋኑም ላይ ተቀምጦ ይነግሣል፤ በዙፋኑም ላይ ካህን ይሆናል፥ የሰላምም ምክር በሁለቱ መካከል ይሆናል። 15 በሩቅም ያሉት መጥተው የእግዚአብሔርን መቅደስ ይሠራሉ። 8፡20 በብዙ ከተሞች የሚቀመጡ አሕዛብ ገና ይመጣሉ፤
  • ክርስቶስ ኢየሱስ በአህያ ውርጫ ተቀምጦ ወደ ኢየሩሳሌም መግባት 9፡9 አንቺ የጽዮን ልጅ ሆይ፥ እጅግ ደስ ይበልሽ፤ አንቺ የኢየሩሳሌም ልጅ ሆይ፥ እልል በዪ፤ እነሆ፥ ንጉሥሽ ጻድቅና አዳኝ ነው፤ ትሑትም ሆኖ በአህያም፥ በአህያይቱ ግልገል በውርጫይቱ ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል።
  • ክርስቶስ በሰላሳ ብር መሸጡ 11፡12 በዚያም ቀን ተሰበረች፤ እንዲሁም እኔን የተመለከቱ የመንጋው ችግረኞች የእግዚአብሔር ቃል እንደ ነበረ አወቁ።
  • በግምጃ ቤት የተቀመጠው ሰላሳ ብር 11፡13 እነርሱም ለዋጋዬ ሠላሳ ብር መዘኑ
  • በባልንጀሮቹ መገፋቱ 13፡6 ሰውም፦ ይህ በእጅህ መካከል ያለ ቍስል ምንድር ነው? ይለዋል። እርሱም፦ በወዳጆቼ ቤት የቈሰልሁት ቍስል ነው ይላል።
  • የደቀመዛሙርቱ መበተን 13፡7 እረኛውን ምታ፥ በጎቹም ይበተናሉ