Jump to content

ነሐሴ ፬

ከውክፔዲያ

ነሐሴ ፬ኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፫፻፴፬ ኛው ዕለት ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በዘመነ ዮሐንስ ፴፪ ዕለታት ሲቀሩ፤ በዘመነ ማቴዎስማርቆስ እና ሉቃስ ደግሞ ፴፩ ዕለታት ይቀራሉ።

፲፭፻፲፩ ዓ/ም ፈርዲናንድ ማጄላን ከአምስት የእስፓኝ መርከቦች ጋር ዓለምን በባሕር ለመዞር ሴቪል ከሚባል ሥፍራ ጉዟቸውን ጀመሩ። ማጄላን በመሃል ላይ ፊሊፒን ደሴቶች ላይ ሲሞት ጉዞውን ምክትሉ ሴባስቲያን እልካኖ ጨረሰ።

፲፯፻፹፬ ዓ/ም በፈረንሳይ አብዮት ቱይሌሪ ቤተ መንግሥት ሲወሰድ ንጉሡ ሉዊ ፲፬ኛ በእስር ላይ ዋለ።