ነጀሚብሬ
Appearance
==
ነጀሚብሬ | |
---|---|
የግብጽ ፈርዖን | |
ግዛት | 1796 ዓክልበ. ግ. |
ቀዳሚ | ሰዋጅካሬ |
ተከታይ | ኻአንኽሬ ሶበክሆተፕ |
ሥርወ-መንግሥት | 13ኛው ሥርወ መንግሥት |
==
ነጀሚብሬ ላይኛ ግብጽ በ2ኛው ጨለማ ዘመን (13ኛው ሥርወ መንግሥት) በ1796 ዓክልበ. ግድም የገዛ ፈርዖን ነበረ። የሰዋጅካሬ ተከታይ ነበረ።
ስሙ ከቶሪኖ ቀኖና ነገሥታት ዝርዝር ብቻ ይታወቃልና ሕልውናውን የሚያስረዳ ቅርስ ገና አልታወቀም። ሆኖም በአንዳንድ ምንጭ ዘንድ ሁለት የጢንዚዛ ዕንቁዎች፣ አንዱ ከሜምፎስ አንዱም ከኢየሩሳሌም ስሙን ያሳያሉ።[1] በዝርዝሩም «ነጀሚብሬ ለ፯ ወርና ለ<...> ቀን ነገሠ» ይላል። ተከታዩ ኻአንኽሬ ሶበክሆተፕ ነበር። በዚሁም ወቅት ባጭር ጊዜ ውስጥ አያሌ ፈርዖኖች እንደ ጠፉ ይመስላል።
ቀዳሚው ሰዋጅካሬ |
የግብፅ (ጤቤስ) ፈርዖን | ተከታይ ኻአንኽሬ ሶበክሆተፕ |
- ^ Revue d'égyptologie, Volumes 29-30፣ 1978, p. 163.
- K.S.B. Ryholt: The Political Situation in Egypt during the Second Intermediate Period, c. 1800 – 1550 BC, Carsten Niebuhr Institute Publications, vol. 20. Copenhagen: Museum Tusculanum Press, 1997 (እንግሊዝኛ)