ኻአንኽሬ ሶበክሆተፕ

ከውክፔዲያ
ኻአንኽሬ ሶበክሆተፕ
የ፪ ሶበክሆተፕ ኻአንኽሬ ስዕል ከአቢዶስ (አሁን በሉቭር ፓሪስ)
የ፪ ሶበክሆተፕ ኻአንኽሬ ስዕል ከአቢዶስ
(አሁን በሉቭር ፓሪስ)
የግብጽ ፈርዖን
ግዛት 1795-1791 ዓክልበ. ግ.
ቀዳሚ ነጀሚብሬ
ተከታይ ረንሰነብ
ሥርወ-መንግሥት 13ኛው ሥርወ መንግሥት

ኻአንኽሬ ሶበክሆተፕ ላይኛ ግብጽ2ኛው ጨለማ ዘመን (13ኛው ሥርወ መንግሥት) ከ1796 እስከ 1791 ዓክልበ. ግድም የገዛ ፈርዖን ነበረ። የነጀሚብሬ ተከታይ ነበረ።

ስሙ በቶሪኖ ቀኖና ነገሥታት ዝርዝር «ሶበክ... ..ሬ» ይታያል፤ አሁን እንደሚታሠብ ሰኸምሬ ኹታዊ 1 ሶበክሆተፕ ከእርሱ በፊት ስለ ነገሠ ይህ ኻአንኽሬ በዘመናዊ ጥናቶች «፪ ሶበክሆተፕ» ይባላል፤ በፊት ግን እንደ «፩ ሶበክሆተፕ» ተቆጠረ። ሙሉ ስማቸው «ሶበክሆተፕ ኻአንኽሬ» ከአንድ የአቢዶስ ቤተ መቅደስ ዓምድ ይታወቃል። ተከታዩ ረንሰነብ ነበር።

ቀዳሚው
ነጀሚብሬ
ግብፅ (ጤቤስ) ፈርዖን
1795-1791 ዓክልበ. ግድም
ተከታይ
ረንሰነብ

ዋቢ ምንጭ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

  • K.S.B. Ryholt: The Political Situation in Egypt during the Second Intermediate Period, c. 1800 – 1550 BC, Carsten Niebuhr Institute Publications, vol. 20. Copenhagen: Museum Tusculanum Press, 1997 (እንግሊዝኛ)