አሉላ ዮሐንስ

ከውክፔዲያ

አሉላ ዮሐንስ ታዋቂ ኢትዮጵያዊ ድምፃዊ ከመሆኑም በተጨማሪ፣ ጊታርኪቦርድአርሞኒካከበሮ (ድረም)ፒያኖን በደንብ የሚጫወት ሁለገብና ዘመናዊ አርቲስት ነው።[1]

የህይወት ታሪክ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ድሬዳዋ ተወልዶ ያደገው አሉላ ዮሐንስ ዕድገቱ በአዳሪ ት/ቤት ውስጥ ነበር። በዚህ አዳሪ ት/ቤት ውስጥ እያለ የሙዚቃ ስሜት አድሮበት መጫወት ጀመረ።[1]

ከሙዚቃ መሳሪያዎች ጊታር በደንብ መጫወት የጀመረው ወደ አዲስ አበባ በመምጣት ትንሽ እንደቆየ ነበር። በ፲፱፻፶ ዓ.ም. መጨረሻዎች ለትምህርት ወደ ጀርመን ሀገር ሄደ። ከዚያም ለሦስት ዓመት ተኩል የሕክምና ትምህርቱን ከተማረ በኋላ በማቋረጥ ወደ ኮንሰርቫቶሪ የሙዚቃ ት/ቤት ገባ። እዚህ የሙዚቃ ት/ቤት እያለም «Mr. President» /ሚስተር ፕሬዝዳንት/ የተባለውን የመጀመሪያውን ሸክላ አሳተመ።[1]

አሉላ ወደ አሜሪካ በመሄድ ከሁለት አልበሞች በተጨማሪ አራት ሸክላዎች አሳትሟል። አሉላ በአሥራ አንድ ቋንቋዎች ይጫወታል። አማርኛትግርኛእንግሊዝኛስፓንኛጣሊያንኛፈረንሳይኛጀርመንኛዕብራይስጥኛ ወዘተ... አቀላጥፎ ይናገራል። ድሬዳዋ እያለ ስንታየሁ ይባል ነበር። «ስንታየሁ» የምትባለውም ሙዚቃ ከሕዝብ ጋር አስተዋወቀችው። አሉላ ከ፴ ዓመታት በላይ ረጅም የሙዚቃ ሕይወት ያለው አርቲስት ነው።[1]

ማጣቀሻ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

  1. ^ "ናሽናል ቢብሊዮግራፊ ቡድን፣ የአንጋፋ አርቲስቶች መዝገበ የሕይወት ታሪክ፣ መጋቢት ፳፻፣ ገጽ 29". Archived from the original on 2011-09-29. በ2010-12-18 የተወሰደ.