አባል:Dawit143

ከውክፔዲያ

ወሎ Wollo (Bete Amhara [1][ለማስተካከል | ኮድ አርም]

'''ወሎ''' በሰሜን ምስራቅ የኢትዮጵያ ክፍል የሚገኝ ታሪካዊ አዉራጃ እና ክፍለ ሀገር ሲሆን ዋና ከተማዋ ደሴ ነው። ከ1842 በፊት የ ወሎ የቀድሞ ስሙ ቤተ አማራ ሲሆን 17ኛው ክፍለ ዘመን የኦሮሞ መስፋፋትን ተከትሎ በአከባቢዉ በሰፈረው በ ወሎ ኦሮሞ ነገድ ተሰየመ። ወሎ በዘር አማራ ወይም ቤተ አምሐራ ከመሆኑም በተጨማሪ የአማራ የዘር ግንድ መነሻም ጭምር ነዉ፡፡ ቤተ አምሀራ ማለት በቀድሞ ካርታዎች ላይ በሰሜን በሽሎ ወንዝ ፣በደቡብ ጃማወንዝ ፣በምእራብ አባይና በምስራቅ አፋር ያዋስኑታል ያዋስኑታል። የወሎ ድንበር በየዘመኑ የመስፋት እና የመጥበብ ሁኔታዎች የሚታይበት ሲሆን በአንዳንድ የታሪክ አጋጣሚዎች እስከ አሰብ ድረስ ይሰፋ ነበር፡፡ ከጣልያን ጦርነት ቀጥሎ በ1933 ዓ.ም. አዘቦራያዋግ እና የጁ ይፋዊ የወሎ ግዛቶች ሆኑ። ወሎ እጅግ ሰፊ የሚባል አዉራጃ የነበረ ሲሆን በስፋቱም ከሐረርጌ፣ከባሌ እና ከሲዳሞ በመቀጠል በአራተኛ ደረጃ ላይ የቀመጣል ስፋቱም 79,4002 ስኩየር ኪሎሜትር ነበር፡፡[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

በ1987 ዓ.ም ኢሀዴግደርግን ስረአት በሀይል በመጣል አገሪቱን ከተቆጣጠረ በኋላ ባወጣዉ ሕገ መንግሥት መሠረት፣ ወሎ የሚባል ራስገዝ የአዉራጃ አስተዳደር በማስቀረት ግዛቱን በአፋር (ክልል)ትግራይ ክልል ፣ እና አማራ (ክልል) እንዲከፈል ተደረገ።

በወሎ አባይተከዜ እና አዋሽ የመሳሰሉ ወንዞች አቋርጠው ያልፋሉ በሽሎ ቦርከና የመሳሰሉ ስመ ጥር ወንዞችም ይገኛሉ። ከአምስት በላይ ሐይቆች በወሎ ሲገኙ እነሱም ሐይቅአርዲቦአሸንጌማይባር እና ጎልቦ ናቸው።

ወሎ ላይ ብዛት ያለው የኦፓል መአድን የወርቅ ክምችት የነዳጅ ሀብት የድንጋይ ከሰል የእምነበረድ መአድናት ብረት ይገኛሉ። በተጨማሪም በመቅደላ፣ሀርቡ ፍልውሃ፣ላስታ ገና ብዙ ምርምር የሚጠይቁ ያልታወቁ መአድናት ይገኛሉ።

ወሎ ላይ ከስምንት በላይ ቋንቋዎች በስፋት ይነገራሉ አማርኛ፣ራይኛ፣አገውኛ፣አርጎብኛ፣አፋርኛ፣ኦሮምኛ፣ትግርኛ እና አረብኛ በከፊል ናቸው።ከዚህ በተጨማሪ ወሎ በኢትዮጵያ በስፋት የሚነገረው የአምሐርኛ ቋንቋ ምንጭ ነው።

የወሎ ህዝብ የግንባታ፣የሸማ፣የሸክላ፣የብረታብረት ጥበብን በኢትዮጵያ በማስተዋወቅ ጉልህ ድርሻ ሲኖረው መሰንቆ፣ባህላዊ ልብስ፣የአምባሰል፣አንቺሆዬ፣ትዝታና ባቲ የዘፈን ቅኝቶች ፈጣሪ ነው።

ወሎ በኢትዮጵያ የነገስታት መፍለቂያ ሲሆን የሰለሞን ስረወ መንግስት ፣ የዛጉዬ ስረወ መንግስት ፣ የመሀመዶ እና የወረሴህ የመሳሰሉት መንግስታት ምንጭ ነው። ዮዲት ጉዲት በወሎ አካባቢ እንደተወለደች የሚጠቁሙ አንድ አንድ መረጃዎች አሉ።

ዶ/ር ዶናልድ ሌቪን "የአሁኗን ኢትዮጵያ የሰሯት ወሎዎች (ቤተ አምሀራዎች) ናቸው ልታመሰግኗቸው ይገባል" ሲል እንዲህ ይላል፡፡

finally from irer read this "The echoes of the glorious days of the ancient Amhara province faintly preserved in some remote villages in Amhara-Saynt (still poignantly stuck to the name of its ancient mother province); in the “Zelalemawitwa” Ambassel (the fortress and prison court of Amhara Kings ); in the famous monastry of Abba Eyesus Moa of Hayq Estifanos(the Abbot and cofounder of the Solomonic dynasty); in the four musical notes of Ethiopian traditional musical notes of (Ambassel, Bati, Achihoye lene and Tizita); in the language of the Amharas( their folklore and traditions) and in the name of the founder King of the Solomonic dynasty, Yekuno Amlak, who was a native of ancient Amhara, in Segerat(now a Kebele in the town of Kuta-ber), just outside of Dessie."


References

https://en.m.wikipedia.org/wiki/Donald_N._Levine

https://en.m.wikipedia.org/wiki/Yekuno_Amlak

https://www.google.com/search?q=Bete+Amhara+Old+map&client=ms-android-samsung-gn-rev1&source=android-browser&prmd=inv&source=lnms&tbm=isch&sa=X&ved=2ahUKEwic-MCWj7_gAhUNwqYKHYGyDkEQ_AUoAXoECAwQAQ&biw=412&bih=670&dpr=2.63#imgrc=Q-r_0SlEmJMM7M&imgdii=etCjKHrXqhEIPM

  1. ^ https://en.m.wikipedia.org/wiki/Donald_N._Levine https://en.m.wikipedia.org/wiki/Yekuno_Amlak https://www.google.com/search?q=Bete+Amhara+Old+map&client=ms-android-samsung-gn-rev1&source=android-browser&prmd=inv&source=lnms&tbm=isch&sa=X&ved=2ahUKEwic-MCWj7_gAhUNwqYKHYGyDkEQ_AUoAXoECAwQAQ&biw=412&bih=670&dpr=2.63#imgrc=Q-r_0SlEmJMM7M&imgdii=etCjKHrXqhEIPM