ኢስታይዎን
ኢስታይዎን (ወይም ኢስትዋዮን፣ ኢስቴዎን) በጥንታዊ ጀርመናውያን ነገዶች መካከል አንዱ ዋና ክፍል ነበር። ስሙ በሮማውያን ታሪክ ጸሐፍት እንደ ታኪቱስና ፕሊኒ ዘንድ ይታወቃል።
ታኪቱስ (90 ዓ.ም.) እንደሚለን፣ በጀርመናውያን «ጥንታዊ ዘፈኖች» መሠረት በጥንት ማኑስ ሶስት ልጆች ነበሩት። እነኚህም 3 ልጆች ሦስት ንዑስ-ብሔሮች ወለዱ፦
ፕሊኒ (70 ዓ.ም. ግድም) እንደ ጻፈው፣ ጀመናውያን በ5 ንዑስ-ብሔሮች ተከፋፈሉ፤ እነርሱም ዋንዲሊ፣ ኢንግዋዮን፣ ኢስትዋዮን፣ ሄርሚዮን፣ እና ባስተርናይ ናቸው። ኪምብሪ የተባለው ጎሣ በኢንግዋዮን ነገዶች መካከል መገኘቱን ቢለንም፣ የኢስትዋዮን ነገድ ደግሞ ይላቸዋል።
በ820 ዓ.ም. ግድም ሂስቶሪያ ብሪቶኑም (የብሪታንያውያን ታሪክ) የሚባል መጽሐፍ ተጽፎ፣ የ«አላኑስ» ልጅ «ኢሳኮን» ይባላል፤ አራት ልጆቹም «ፍራንኩስ»፣ «ሮማኑስ»፣ «አለማኑስ»ና «ብሩቱስ» ሲሆኑ ከነዚህ ፍራንኮች፣ ላቲናውያን፣ ጀርመናውያንና ብሪቶናውያን እንደ ተወለዱ ይላል።
በ1513 ግድም ጀርመናዊው መምህር ዮሐንስ አቬንቲኑስ የጀርመን አገር ዜና መዋዕል አሳተመ፤ በዚህም ውስጥ እንደሚዘግበው፣ ኢስቴዎን የኢንጌዎን ልጅና ተከታይ ነው። በኢስቴዎን ዘመን የሊብያ አማዞኖች ንግሥት ሚሪና ሶርያንና ትንሹን እስያ ይዛ በአውሮጳ ገባችና እስከ ዳኑብ ወንዝ ድረስ ዘመተች። ጀርመንን ከሠራዊቷ ጋር ለመውረር ስትል ግን፣ ኢስቴዎን 2ቱን አለቆች ሞፕሱስንና ሲፒሉስን ልኮ በሳቫ ወንዝ ላይ በትልቅ ውጊያ አሸነፉአትና ተገደለች። ተመሳሳይ አፈ ታሪክ በግሪኩ ዲዮዶሮስ ሲኩሉስ መጽሐፍ (III. 55) ይገኛል።
ኢስቴዎን ለ52 ዓመት (2144-2092 ዓክልበ. ግድም) ከነገሠ በኋላ ሞተና ልጁ (ወይም እንደ ታኪቱስ፣ ወንድሙ) ሄርሚኖን በጀርመን ዙፋን ላይ ተከተለው ይላል።
ቀዳሚው ኢንጋይዎን |
የቱዊስኮኔስ (ጀርመን) ንጉሥ | ተከታይ ሄርሚኖን |