ኢንጋይዎን

ከውክፔዲያ
ጀርማኒክ ቋንቋዎች 1 ዓ.ም. ግድም፣ ቀይ፡- ስሜን ባሕር ጀርማኒክ ወይም «ኢንግቫዮኒክ»

ኢንጋይዎን (ወይም ኢንግዋዮንኢንጌዎን) በጥንታዊ ጀርመናውያን ነገዶች መካከል አንዱ ዋና ክፍል ነበር። ስሙ በሮማውያን ታሪክ ጸሐፍት እንደ ታኪቱስፕሊኒ ዘንድ ይታወቃል።

ታኪቱስ (90 ዓ.ም.) እንደሚለን፣ በጀርመናውያን «ጥንታዊ ዘፈኖች» መሠረት በጥንት ማኑስ ሶስት ልጆች ነበሩት። እነኚህም 3 ልጆች ሦስት ንዑስ-ብሔሮች ወለዱ፦

በአንድ አስተያየት በኢንጋይዎን የተነገረው የቅድመ-ጀርመንኛ ቀበሌኛ የ«ኢንግቫዮኒክ ቋንቋዎች» (እንግሊዝኛፍሪዝኛዝቅተኛ ሳክስኛ) አባት ሆነ።

ፕሊኒ (70 ዓ.ም. ግድም) እንደ ጻፈው፣ ጀመናውያን በ5 ንዑስ-ብሔሮች ተከፋፈሉ፤ እነርሱም ዋንዲሊ፣ ኢንግዋዮን፣ ኢስትዋዮን፣ ሄርሚዮን፣ እና ባስተርናይ ናቸው። በኢንግዋዮን ነገዶች መካከል ኪምብሪቻውኪቴውቶን የተባሉ ጎሣዎች እንደ ኖሩ ይለናል።[1]

በ820 ዓ.ም. ግድም ሂስቶሪያ ብሪቶኑም (የብሪታንያውያን ታሪክ) የሚባል መጽሐፍ ተጽፎ፣ የ«አላኑስ» ልጅ «ኔውጊዮ» ይባላል፤ ሦስት ልጆቹም «ዋንዳሉስ»፣ «ሳክሱስ»ና «ቦጋኑስ» ሲሆኑ ከነዚህ ባቫሪያውያን፣ ቫንዳሎች፣ ሳክሶኖችጡሪንጋውያን እንደ ተወለዱ ይላል።

አኒዩስ ዴ ቪቴርቦ በ1490 ዓ.ም. ባሳተመው ጽሑፍ ዘንድ፣ ቤሮሶስ ብዙ መዝገቦች አቅርቦ ነበር። በዚህ በኩል፣ የማኑስ ልጅ ኢንጋይዎን የሳርማትያ እና የጀርመን አገሮች ሦስተኛው ንጉሥ ነበር። ኢስታይዎን ባይጠቀስም ሄርሚኖን ከኢንጋይዎን በኋላ እንደ ነገሠ ይጨምራል።

በ1513 ዓ.ም. ግድም ጀርመናዊው መምህር ዮሐንስ አቬንቲኑስ የጀርመን አገር ዜና መዋዕል አሳተመ፤ በዚህም ውስጥ እንዳለው፣ በጥንት ጀርመኖች ፕሊኒ እንደ ጻፈው በ5 ብሔሮች ተከፋፈሉ። የኢንጌዎን ነገዶች ከማኑስ ልጅና ተከታይ ንጉሥ ኢንጌዎን ተወለዱ፤ እነዚህም በስሜን ባሕር ላይ የተገኙ ሕዝቦች ቻውኪ፣ ኪምብሪ፣ ቴውቶኖች፣ ፍሪዚ፣ ሳክሶኖችና ዳኖች ነበሩ።

ጀርመንኛ ባሳተመ ሌላ መጽሐፍ ዘንድ፣ በኢንጋይዎን ዘመን አለቃው ብሪጉስ ወይም ብሪጎ ታላቅ ከተማ በአርጽቡርግ (አሁን ቬልተንቡርግ ገዳምኬልሃይም ጀርመን) ሠርቶ ነበር፣ እንዲሁም ብሪጋንቲዮን (ብሬገንጽ) በኮንስታንጽ ሃይቅኦስትሪያ ሠራ። በኋላ ብሪጉስን ወደ ኢቤሪያዩቤልዳን ዙፋን ለመውረስ ላከው።

አቬንቲኑስ እንደሚዘግበው፣ በኢንጌዎን ዘመን፣ የጥራክያ ንጉሥ ሊኩርጉስ ሁለት አለቆች ሞፕሱስንና ሲፒሉስን ከሳቫ ወንዝ ዙሪያ ወደ ኢንጌዎን ግዛት አባረራቸው። ከዚህ በኋላ በኢንጌዎን ልጅ ኢስቴዎን ዘመን የሊብያ አማዞኖች ንግሥት ሚሪና በወረረችበት ወቅት 2ቱ አለቆች በሳቫ ወንዝ ላይ በትልቅ ውጊያ አሸነፉአትና ተገደለች።

ኢንጌዎን ለ45 ዓመት (2190-2145 ዓክልበ. ግድም) ከነገሠ በኋላ ሞተና ልጁ (ወይም እንደ ታኪቱስ፣ ወንድሙ) ኢስቴዎን በጀርመን ዙፋን ላይ ተከተለው ይላል።

  1. ^ Pliny the Elder Book IV. (እንግሊዝኛ)


ቀዳሚው
ማኑስ
የቱዊስኮኔስ (ጀርመን) ንጉሥ
2190-2145 ዓክልበ. ግድም
ተከታይ
ኢስታይዎን