ብሪጉስ

ከውክፔዲያ
የካስቲል ምልክት -በብሪጉስ እንደ ተፈጠረ ይሚል ትውፊት አለ

ብሪጉስእስፓንያ አፈ ታሪክ ዘንድ ከዩቤልዳ ቀጥሎ የኢቤሪያ 4ኛው ንጉሥ ነበረ። የዩቤልዳ ልጅ ሆኖ ለ52 ዓመታት እንደ ነገሠ ይባላል (ምናልባት 2162-2109 ዓክልበ. ግድም)። በአንዳንድ ምሁር ዘንድ እሱ መጀመርያ ወርቃማ አምባ በቀይ ጋሻ ላይ የነበረው በኋላ የካስቲል መንግሥት አርማ ፈጠረ።[1]

ዮሐንስ አቬንቲኑስጀርመንኛ ባሳተመው ዜና መዋዕል ዘንድ፣ ዩባልዳ ያለ ወራሽ ወንድ ልጅ አርፎ ነበር፣ የጀርመን ንጉሥ የኢንጋይዎን አለቃ ብሪጉስ ወይም ብሪጎ ግን ሴት ልጁን አግብቶ የኢቤሪያን ዙፋን ወሰደ። እርሱ የመሳይ (ሞሳሕ) ልጅ ፣ የብሪጋውያን አባትና በቱዊስኮን ዘመን የሞይስያ አገረ ገዥ ሆኖ ይለዋል። በኢንጋይዎን ዘመን ታላቅ ከተማ በአርጽቡርግ (አሁን ቬልተንቡርግ ገዳምኬልሃይም ጀርመን) ሠርቶ ነበር፣ እንዲሁም ብሪጋንቲዮን (ብሬገንጽ) በኮንስታንጽ ሃይቅኦስትሪያ ሠራ። በብሪጉስ ዘመን በኢቤሪያ ላይ፣ አማዞኖች የታባሉት ሴት ወታድሮች በንግሥታቸው ሚሪና ሥር ከሊብያ ዘምተው ዛቻ በኢቤሪያ ላይ እንዲሁም በመላው አውሮፓ ላይ ጣሉ ይለናል።

እስፓንያና በፖርቱጋል ብዙ ቦታዎች በጥንት -ብሪጋ የሚለው መድረሻ በስማቸው ላይ ስለ ነበር፣ በብሪጉስ ዘመን እንደ ተሠሩ የሚል ልማድ አለ። ከነዚህም ውስጥ፦

በ -ብሪጋ የሚጨረሱ ጥንታዊ ቦታዎች በዚህ ካርታ በምዕራቡ (አረንጓዴና ጥላ-ሐምራውዊ ክፍሎች) ይታያሉ

ፖርቱጋል

...ወዘተ. አሉ።

ቀዳሚው
ዩቤልዳ
ኢቤሪያ ንጉሥ
2162-2109 ዓክልበ. ግድም
ተከታይ
ታጉስ ኦርማ
  1. ^ A brief history of Spain (የእስፓንያ ታሪክ ባጭሩ) 1700 እ.ኤ.አ. (እንግሊዝኛ)