Jump to content

ኢኩኑም

ከውክፔዲያ

ኢኩኑምአሹር ንጉሥ ነበር። ምናልባት 1842-1828 አካባቢ ገዛ። የኢሉሹማ ልጅና የወንድሙ የ 1 ኤሪሹም ተከታይ ይባላል።

ሃቲ የነበሩት ካሩም (የንግድ ጣቢያዎች) አስቀጠለ፤ እንዲሁም አንዳንድ ቤተ መቅደስ ወይም አምባ እንዳሠራ ከጽላቶቹ ይታወቃል።

የዓመት ስሞች

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

የያንዳንዱ አሦራዊ ዓመት ስም ለዚያ ዓመት የተሾመው የሊሙ ስም ነበረ። ከዚህ በታች የዓመቱ ሊሙ እና ብዙ ጊዜ የሊሙ አባት ስም እንደ ኡልትራ አጭር አቆጣጠር ይዘርዝራሉ።

1842 ዓክልበ. - ቡዙ፤ አዳድ-ራቢ ልጅ
1841 ዓክልበ. - ሹሊ፤ ሻሊማሁ ልጅ / ኢዲን-ሲን፤ የሹሊ ወንድም
1840 ዓክልበ. - ኢኩኑም፤ ሹዳያ ልጅ
1839 ዓክልበ. - ዳን-ወር፤ አሁ-አሂ ልጅ
1838 ዓክልበ. - ሹ-አኑም ከነራብቲም
1837 ዓክልበ. - ኢል-ማሡ፤ አሹር-ጣብ ልጅ
1836 ዓክልበ. - ሹ-ሑቡር፤ ሹሊ ልጅ
1835 ዓክልበ. - ኢዱዋ፤ ጹሊሊ ልጅ
1834 ዓክልበ. - ላቀፕ፤ ፑዙር-ላባ ልጅ
1833 ዓክልበ. - ሹ-አኑም፤ የሃቢሩ ሰው
1832 ዓክልበ. - ኡኩ፤ ቢላ ልጅ
1831 ዓክልበ. - አሹር-ማሊክ፤ ፓናካ ልጅ
1830 ዓክልበ. - ዳን-አሹር፤ ፑዙር-ወር ልጅ
1829 ዓክልበ. - ሹ-ኩቡም፤ አሁ-አሂ ልጅ
1828 ዓክልበ. - ኢሪሹም፤ ኢዲን-አሹር ልጅ

ለ1841 ዓክልበ.፣ አንዱ የሊሙ ዝርዝር በ«ኢዲን-ሲን፤ የሹሊ ወንድም» ፈንታ «ሹሊ፤ የሻሊማሁ ልጅ» ይጻፋል። መግለጫው አንድ ሊሙ በዓመቱ ውስጥ አርፎ በወንድሙ ተተካ ሳይሆን አይቀርም።[1]

ቀዳሚው
1 ኤሪሹም
አሹር ገዥ
1842-1828 ዓክልበ. ግድም
ተከታይ
1 ሳርጎን
  1. ^ የመስጴጦምያ ነገሥታት (ፈረንሳይኛ)