ኦሜቴፔ ደሴት

ከውክፔዲያ
Jump to navigation Jump to search

ግራናዳ ከተማ በስተ ደቡብ ወደ 50 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ኦሜቴፔ ደሴት ይገኛል። በደሴቱ ላይ የሚታየው የተፈጥሮ ውበትና ለም የሆነው አፈሩ ለመኖሪያነት ተፈላጊ እንዲሆን አድርጎታል። እንዲያውም የኒካራጓግብርና ታሪክ የሚጀምረው በዚህ አካባቢ ነው። በዛሬው ጊዜ ኦሜቴፔ ወደ 42,000 የሚጠጉ ነዋሪዎች ያሏት ሲሆን የሚተዳደሩትም ዓሣ በማጥመድ እንዲሁም እንደ በቆሎሙዝቡና እና ሌሎች የእህል ዓይነቶችን በማልማት ነው። እዚህም ቢሆን እጅግ አስደናቂ የሆኑ የዱር እንስሳት ይገኛሉ። ኃይለኛ ድምፅ የሚያወጡ በጣም ብዙ በቀቀኖችን፣ ነጭና ሰማያዊ ላባ ያላቸውን የሚያማምሩ ወፎች እንዲሁም ብዙ ሰው የሚወዳቸውን ነጭ ፊት ያላቸው ጦጣዎች ማግኘት ይቻላል።