Jump to content

ከበደ ሚካኤል

ከውክፔዲያ

ከበደ ሚካኤል (1909-1991) በደብረ ብርሃን ከተማ ኣካባቢ፣ ገርም ገብርኤል አጥቢያ ጥቅምት ፳፫ ቀን ፲፱፻፱ ዓ.ም.ተወለዱ። ወደ አዲስ አበባ እንደ መጡ መጀመሪያ በአሊአንስ ኢቲዮ-ፍራንሴዝ በኋላም በላዛሪስት ሚሲዮን ትምህርታቸውን ተከታተሉ። የሼክስፒርሮሜዎና ዡልየትማክቤዝን በመተርጎም እውቅናን ለማትረፍ ችለዋል።

ሌሎች ታዋቂ የትርጉም ሰራዎች መሃል፦

  • ይቅርታ በላይ በሚል አርእስት ከBeyond the Pardon በ M.Clay የተተረጎመው ሊጠቀስ የቻላል።

ከበደ ሚካኤል 30 ገደማ መፃሕፍትን ፅፈዋል። ከበደ ሚካእል ካበረከቷቸው የቴአትር ስራዎች

ይገኙባቸዋል።

ከበደ ሚካኤል በርካታ የስነ ጽሁፍ ስራዎች ባለቤት በመሆናቸው በተለይም ለልጆች ትምህርት አዘል ጽሁፎችን የግጥም የፈጠራ ስራዎችን ቅኔዎችን በስፋት በማበርክታቸው በኢትዮጵያ የስነጽሁፍ መድረክ ገናና ከሆኑት ደራሲዎች አንዱ ናቸው። ከነዚህም መሃል፦

ሊጠቀሱ ይችላሉ።

የሰዎች ስነ ምግባር ላይ የማተኮርና ምክር አዘል መልእክቶችን የማስተላለፍ ዝንባሌአቸው በአብዛኛው ስራቸው ላይ ይንጸባረቃል።

ዘመናዊት ኢትዮጵያን ለማደርጀት በተደረገው ትግል በግንባር ቀደምትነት የተሳተፉ እኒህ ፈላስማ፥ ባለቅኔ፥ ጸሐፌ-ተውኔት፥ ደራሲና አንጋፋ ጋዜጠኛ ፥ 'የቀለም ሰው' በሀገራችን የመጀመሪያ የነበረውን የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ሽልማት ድርጅት በቀዳሚነት የተቀበሉ ሲሆን፣ አዲስ ትውልድ ላፈራ ስብእናቸው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ጥቅምት ፳፮ ቀን ፲፱፻፺ ዓ.ም. በሥነ ጽሑፍ የክብር ዶክቶሬት ዲግሪ ሸልሟቸዋል። በተረፈም ከፈረንሳይጀርመንሶቭየት ህብረትሜክሲኮ ሽልማትን ተቀብለዋል።

በተረፈ የትምህርት ሚኒስትር ዳይረክተር፣ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ተከታይ ዳይሬክተር (፲፱፵፪)፣ የብሄራዊ መጻህፍት ቤት ዳይረክተር (፲፱፵፬)ና የካቢኔ ሚንስትር ሆነው አገልግለዋል።

ክቡር ዶክቶር ከበደ ሚካኤል፥ ኢትዮጵያዊ 'የቀለም ሰው' ኅዳር ፫ ቀን ፲፱፻፺፩ ዓ.ም. በሰማንያ ሁለት ዓመታቸው አረፉ።[1]

ናሙና ግጥሞች

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

የተማረ ሆኖ እውነቱን የማይገልጽ ፣
ባለ ጸጋ ሆኖ ገንዘቡን የማይሰጥ፣
ደሃ ሆኖ መስራት የማይሻ ልቡ፣
ሶስቱም ፍሬ ቢሶች፣
ለምንም አይረቡ።

አይነ የለውም አሉ የሰነፍ ልመና
ወደ አምላክ ሲጸልይ ማታ በልቦና
መንገዱ ሳይመታኝ ባቧራ በጭቃ
አድርገኝ ይለዋል ላገሬ እንድበቃ
እንጦጦ ተኝቼ ሃረር እንድነቃ

መርዝም መድሃኒት ነው ሲሆን በጠብታ
እንዲሁም ለተንኮል አለው ቦታ ቦታ
ምን ቢሰለጥኑ ቢራቀቁ በጣም
ሁልጊዜ ደጋግሞ ብልጠት አያዋጣም።
በጅ የተበተቡት ተንኮል ዞሮ ዞሮ
ማጋለጡ አይቀር እጅና እግር አስሮ ።
መጽሓፉም ይለናል ሲያስተምረን ጥበብ
ብልጥ ሁን እንደባብ የዋህ ሁን እንደርግብ
ስለዚህ በብልጠት ተንኮል ስትሰሩ
በዝቶ እንዳይገላችሁ ገርነት ጨምሩ ...
የዕውቀት ብልጭታ የተወሰደ
  1. ^ ብርሃነ መስቀል ደጀኔ እና ጌታሁን ሽብሩ፣ "ያሠርቱ ምእት ፥ የብርዕ ምርት"፣ (1999 ዓ.ም.) ገጽ 42

[1]