ከአትክልት ጋር የሚሠራ ገንፎ

ከውክፔዲያ

ከአትክልት ጋር የሚሠራ ገንፎ በኢትዮጵያ አበሳሰል አለ። ከ6 ወር እስከ 9 ወር ዕድሜ ላለው ሕጻን ይስማማል።

አስፈላጊ ጥሬ ዕቃዎች[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

አዘገጃጀት[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

  • ጎመን ወይም ረቆስጣሪ ማጠብ፣
  • ከድንቹ ጋር ደባልቆ ማብሰል፣
  • ድንቹንና አትክልቱን መፍጨት፣
  • የተቀቀለውን ባቄላ መፍጨትና ከድንቹና ከአትክልቱ ጋር መቀላቀል፣
  • ዱቄቱን ከወተት ጋር ካገነፉ በኋላ፣ ከአትክልቱ ጋር ቀላቅሎ ማማሰል፣
  • ቀዝቀዝ ሲል በማንኪያ መመገብ፡፡

ማሳሰቢያ፣ ከአንድ ዓመት በታች የሆኑ ሕጻናት ምግብ ውስጥ ጨውም ሆነ ማንኛውንም ቅመማ ቅመም መጨመር አያስፈልግም፡፡ ምክንያቱም በጣም ያልዳበረው የሕጻኑ ኩላሊት ከባድ በሆነ የማጣራት ሥራ ስለሚጠመድ ነው፡፡ ቅመሞችም ለጨጓራ ስለሚከብዱ መጨመሩ አይደገፍም፡፡