Jump to content

መጽሐፈ ኩፋሌ

ከውክፔዲያ
(ከኩፋሌ የተዛወረ)

መጽሐፈ ኩፋሌኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን መጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ በዲዩትሮካኖኒካል መጻሕፍት አንዱ ነው። በሌሎቹ አብያታ ክርስትያናት ግን ዛሬ የማይቀበል መጽሐፍ ወይም ሲውዴፒግራፋ ይባላል። ነገር ግን ለቀድሞው የቤተ ክርስቲያን አበው ታውቆ የጥቅስ ምንጭ ሆነላቸው። የመጽሐፉ ግሪክ ትርጉም የሚታወቀው ከቅዱስ ኤፒፋንዮስ ጥቅሶች ባቻ ሳይሆን እንዲሁም በዩስቲን ሰማዕት፣ በኦሪጄን፣ በዲዮዶሮስ ዘአንጥያክያ፣ በኢሲዶር ዘሰቪላ፣ በአሲዶር ዘእስክንድርያ፣ በዩቲክዮስ (አቡነ እስክንድርያ)፣ በዮሐንስ ማላላስ፣ በጊዮርጊስ ሱንኬሎስና በቄድሬኖስ ጥቅሶች በከፊል ይታወቃል።

ሆኖም መጽሐፉ በአይሁድ ሊቃውንቶች ወይምሳንሄድሪን1ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ እንደ ቅዱሳን መጻሕፍት መታየቱ ቆመ። የመፅሀፉ አንዳንድ ክፍል በቁምራን ዋሻ በ1939 ዓ.ም. እስከተገኘበት ዕለት ድረስ፣ የዕብራይስጥ ትርጉም ሙሉ በሙሉ ጠፍቶ ነበር።በኋላ ዘመንም በሮማ ቤተ ክርስቲያን አለቆች ተቀባይነት ሳይኖረው ቀርቷል። ሆኖም በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ዘንድ እንዲሁም በቤተ እስራኤል አይሁዶች ዘንድ፣ መጽሐፉ በግዕዝ ስለ ተገኘ እስከ ዛሬ ድረስ ቅዱስ ተብሎ ተከብሯል።

መጽሐፉ እንደሚለው መላእክት የዓለሙን ታሪክ ከፍጥረት ጀምሮ እስከ ኦሪት ዘጸአት ድረስ (2,410 ዓመታት ሲቆጠሩ) ለሙሴደብረ ሲና ይተርካሉ። ዘመናት በኢዮቤልዩ ወይም በ49 ዓመታት ይከፋፈላሉ። ኢያንዳንዱ ኦዮቤልዩ 7 ሱባዔ ወይም የዓመት ሳምንት (7 አመት) ነው። ከማየ አይህ አስቀድሞ ደቂቃ ሴት ከእግዚአብሔር አምጸው ወደ ቃየን ልጆች እንደ ሔዱና እንደ ከለሱ ይላል። ክልስ ልጆቻቸውም ክፉ ረጃጅሞች (ናፊሊም) ሆነው በማየ አይህ ጠፉ። ከዚህ በኋላ የኖህን ልጆች አሳቱ። ጣኦት ሠሩ፣ መንግሥት አጸኑ፣ የኖህ ልጆች ምድርን ሁሉ ያካፈላሉ፣ የባቢሎን ግንብ ከወደቀ ቀጥሎ ወደ ርስቶቻቸው ተበተኑ። መላእክትም ለአብርሃም ቅዱስ ቋንቋን አሳውቁት።

ከተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ውጭ እንደ «ሲውደፒግራፋ» በመቆጠሩ አንዳንድ ሊቃውንት በ150 ዓክልበ. ገደማ እንደ ተሠራ ይገምታሉ። ለዚሁ አስተሳሰብ ግን ምንም ማስረጃ አልተገኘም።

መጽሕፉን ለማንበብ

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]
የሚያዩት ገጽ ላይ ወይም እዚህ ላይ [1] በመጫን የመጽሐፉን ገጾች ማንበብ ይችላላሉ

የውጭ መያያዣዎች

[ለማስተካከል | ኮድ አርም]