ኮሽም
Appearance
ኮሽም (Dovyalis abyssinica) ኢትዮጵያ፣ ኬንያና ኡጋንዳ የሚበቅል የተክል አይነት ሲሆን ፍሬው ሳይበስል አረንጓዴ ሆኖ ይኮማጠጣል።
ስሩ ተፈልቶ ሲጠጣ የኩላሊትና የሽንት ዑደት ብልቶችን ጤንነት ያሻሽላል።
በአንድ ጥናት ዘንድ፣ ነቀርሳን ወይም ሆድ ቁርጠትን ለማከም፣ ፮ እስከ ፲ ከፍሬዎቹ ይበላሉ።[1]
ከ3000 እስክ 6000 ጫማ ከፍታ ያለ አየር ጸባይ። ስለዚህም ኮሽም ብዙ ጊዜ የሚገኘው በ ዩጋንዳ፣ ኢትዮጵያ እና ኬንያ ነው ።
አመቱን ሙሉ ፍሬ ይሰጣል፤ 9ጫማ ድረስ ቁመቱ ያድጋል። Dovyalis hebecarpa የሚባል ከኮሽም ጋር ተዛማጅ አትክልት በሴይሎን ይበቅላል። ሁለቱ ተክሎች ሲዳቀሉ ከፍተኛ ጥቅም ይገኛል። ለምሳሌ የኮሽም ፍሬውም መኮምጠጡን ያቆማል። የሚፈጠረው አዲስ አትክልት ፍሬው በጣም የተንዠረገገ ይሆናል። [2]
- ^ የፍቼ፣ ኦሮሚያ ባህላዊ መድሃኒት ጥናት 2006 ዓም ከዓቢዩ እኒየው እና ሌሎች፣ ጎንደርና አዲስ አበባ ኡኒቨርሲቲዎች ሥነ ፍጥረት ኮሌጆች
- ^ http://www.hort.purdue.edu/newcrop/morton/ketembilla_ars.html