Jump to content

ኮናይረ ሞር

ከውክፔዲያ
(ከኮናይሬ ሞር የተዛወረ)

ኮናይረ ሞር (ሞር ማለት «ታላቁ») በአይርላንድ አፈ ታሪክ22 እስከ 36 ዓም ድረስ የአየርላንድ ከፍተኛ ነጉሥ ነበር።

ፕሮፌሰር ዲ ፒ ማካርጢ እንዳስረዳው፣ ከ11ኛው ክፍለ ዘመን ዓም የተረፉት ቅድመኞቹ ምንጮች በአቆጣጠር ረገድ እርስ በርስ ይስማማሉ። [1] በዚያው አቆጣጠር፣ የክርስቶስ ልደት (1 እ.ኤ.አ. እንደ ታሠበ ወይም በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር 8 ዓክልበ.) በዮኩ ፈይድሌክ ዘመን (11 እስከ 1 ዓክልበ.) ፫ኛው ዓመት ደረሰ።

በኋላ የተጻፉት ዝርዝሮች ግን ኮናይረ ለ70 ዓመታት ሙሉ እንደ ገዛ ይላሉ። ማካርጢም እንዳስረዳው፣ ከ12ኛው ክፍለ ዘመን ዓም ጀምሮ ምንጮቹ በአይርላንድ ነገሥታት አቆጣጠር ስለ ክርስቶስ ልደት ዓመት ይለያዩ ጀመር። ሌቦር ጋባላ ኤረን እንደቆጠረው የክርስቶስ ልደት በኤቴርስኬል ዘመን ሆነ። ወይም በ17ኛው ክፍለ ዘመን የተጻፉት ታሪኮች እንዳሉት ደግሞ፣ ክርስቶስ በክሪምጣን ኒያ ናይር ዘመነ መንግሥት ተወለደ።

የቲገርናቅ ዜና መዋዕልየላውድ አቆጣጠሮች ስለ ኮናይረ ዘመን በመስማማታቸው፣ ፕሮፌሰር ማካርጢ እንዳስረዳው፣ እነዚህ ምንጮች የድሮ (ኦሪጂናል) አቆጣጠር በታማኝነት እንደ ጠበቁ ይመስላል።

  1. ^ የአይርላንድ ነገስታት ልማዶችን ስለ ማስማማት Archived ሜይ 26, 2014 at the Wayback Machine (እንግሊዝኛ)