ወደ ሮማውያን ፲፭

ከውክፔዲያ
ወደ ሮማውያን ፲፭
በ፫ኛው ክፍለ ዘመን የተጻፈ ወደ ሮማውያን ፲፭:፳፮-፳፯ ወደ ሮማውያን ፲፭:፴፪-፴፫ በኮዴክስ ካሮሊነስ
አጭር መግለጫ
ፀሐፊ ጳውሎስ
የመጽሐፍ ዐርስት ወደ ሮማውያን
የሚገኘው በአዲስ ኪዳን ፮ኛው መጽሐፍ
መደብ የጳውሎስ መልዕክት


ወደ ሮማውያን በአዲስ ኪዳን የመጀመሪያው መልዕክት ሲሆን ቅዱስ ጳውሎስ በቆሮንጦስ እያለ በ፶ ዎቹ ዓ.ም. የጻፈው መልዕክት ነው ። ይህ ምዕራፍ ፲፭ ሲሆን በ፴፫ ንዑስ ክፍሎች ይከፈላል ። ጳውሎስ በዚህ መልዕክቱ በምዕራፍ ፲፬ ያለውን መልክት በመቀጠል የእግዚአብሔርን ቃል እንደ ምግብ በየዕለቱ መቀለብ በመንፈስ ቅዱስ መሞላትንና በእምነት ጠንካራ እደሚያደርግ ያስተምራል።


ቅዱስ ጳውሎስ ለሮማውያን መልዕክቱን የጻፈበት ምክኒያት አይሁዳውያንና ሮማውያን በሰላም አንድላይ በሮም ለብዙ ዘመን ሲኖሩ ቆይተው ክርስትና በተመሠረተበት ወቅት ፣ አይሁዳውያን ክርስቶስ እኛን ነው የመረጠን ለመንግሥቱ እናንተን አይደለም... ሲሊ ሮማውያን ደግሞ እናንተ ሰቀላችሁት እንጂ ምን አረጋቹህለት... እየተባባሉ እርስበርሳቸው ጥል ስለፈጠሩ እነሱን ለማስታረቅ ጻፈው ።

የጳውሎስ መልዕክት ወደ ሮማውያን ምዕራፍ ፲፭

ቁጥር ፩ - ፲[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

1፤እኛም፡ኀይለኛዎች፡የኾን፟፡የደካማዎችን፡ድካም፡እንድንሸከም፡ራሳችንንም፡ደስ፡እንዳናሠኝ፡ይገ፟ባ፟ናል። 2፤እያንዳንዳችን፡እንድናንጸው፡ርሱን፡ለመጥቀም፡ባልንጀራችንን፡ደስ፡እናሠኝ። 3፤ክርስቶስ፡ራሱን፡ደስ፡አላሠኘምና፤ነገር፡ግን፦አንተን፡የነቀፉበት፡ነቀፋ፡ወደቀብኝ፡ተብሎ፡እንደ፡ ተጻፈ፡ኾነበት። 4፤በመጽናትና፡መጻሕፍት፡በሚሰጡት፡መጽናናት፡ተስፋ፡ይኾንልን፡ዘንድ፡አስቀድሞ፡የተጻፈው፡ዅሉ፡ለትምህርታችን፡ተጽፏልና። 5-6፤ባንድ፡ልብ፡ኾናችኹ፡ባንድ፡አፍ፡እግዚአብሔርን፥ርሱም፡የጌታችን፡የኢየሱስ፡ክርስቶስ፡ አባት፥ታከብሩ፡ዘንድ፥የትዕግሥትና፡የመጽናናት፡አምላክ፡እንደክርስቶስ፡ኢየሱስ፡ፈቃድ፡ርስ፡በርሳችኹ፡ ባንድ፡ዐሳብ፡መኾንን፡ይስጣችኹ። 7፤ስለዚህ፥ክርስቶስ፡ለእግዚአብሔር፡ክብር፡እንደ፡ተቀበላችኹ፡እንዲሁ፡ርስ፡በርሳችኹ፡ተቀባበሉ። 8-9፤ለአባቶች፡የተሰጠውን፡የተስፋ፡ቃል፡ያጸና፡ዘንድ፡ደግሞም፦ስለዚህ፡በአሕዛብ፡መካከል፡ አመሰግንኻለኹ፡ለስምኽም፡እዘምራለኹ፡ተብሎ፡እንደ፡ተጻፈ፥አሕዛብ፡ስለ፡ምሕረቱ፡እግዚአብሔርን፡ ያከብሩ፡ዘንድ፥ክርስቶስ፡ስለእግዚአብሔር፡እውነት፡የመገረዝ፡አገልጋይ፡ኾነ፡እላለኹ። 10፤ደግሞም፦አሕዛብ፡ሆይ፥ከሕዝቡ፡ጋራ፡ደስ፡ይበላችኹ፡ይላል።

ቁጥር ፲ - ፳[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

11፤ደግሞም፦እናንተ፡አሕዛብ፡ዅላችኹ፥ጌታን፡አመስግኑ፡ሕዝቦቹም፡ዅሉ፡ይወድሱት፡ይላል። 12፤ደግሞም፡ኢሳይያስ፦የእሴይ፡ሥር፡አሕዛብንም፡ሊገዛ፡የሚነሣው፡ይኾናል፤በርሱ፡አሕዛብ፡ተስፋ፡ ያደርጋሉ፡ይላል። 13፤የተስፋ፡አምላክም፡በመንፈስ፡ቅዱስ፡ኀይል፡በተስፋ፡እንድትበዙ፡በማመናችኹ፡ደስታንና፡ሰላምን፡ዅሉ፡ ይሙላባችኹ። 14፤እኔም፡ራሴ፡ደግሞ፥ወንድሞቼ፡ሆይ፥በበጎነት፡ራሳችኹ፡እንደ፡ተሞላችኹ፥ዕውቀትም፡ዅሉ፡እንደ፡ ሞላባችኹ፥ርስ፡በርሳችኹም፡ደግሞ፡ልትገሠጹ፡እንዲቻላችኹ፡ስለ፡እናንተ፡ተረድቻለኹ። 15-16፤ነገር፡ግን፥አሕዛብ፡በመንፈስ፡ቅዱስ፡ተቀድሰው፡የተወደደ፡መሥዋዕት፡ሊኾኑ፥ለእግዚአብሔር፡ ወንጌል፡እንደ፡ካህን፡እያገለገልኹ፥ለአሕዛብ፡የክርስቶስ፡ኢየሱስ፡አገልጋይ፡እኾን፡ዘንድ፡ከእግዚአብሔር፡በተሰጠኝ፡ጸጋ፡ምክንያት፡ተመልሼ፡ላሳስባችኹ፡ብዬ፡በአንዳንድ፡ቦታ፡በድፍረት፡ጻፍኹላችኹ። 17፤እንግዲህ፡ከእግዚአብሔር፡ዘንድ፡በሚኾን፡ነገር፡በክርስቶስ፡ኢየሱስ፡ትምክሕት፡አለኝ። 18-19፤አሕዛብ፡እንዲታዘዙ፡ክርስቶስ፡በቃልና፡በሥራ፥በምልክትና፡በድንቅ፡ነገር፡ኀይል፥በመንፈስ፡ ቅዱስም፡ኀይል፡በእኔ፡አድርጎ፡ከሠራው፡በቀር፡ምንም፡ልናገር፡አልደፍርም፤ስለዚህ፥ከኢየሩሳሌም፡ዠምሬ፡ እስከ፡እልዋሪቆን፡ድረስ፡እየዞርኹ፡የክርስቶስን፡ወንጌል፡ፈጽሜ፤ሰብኬያለኹ። 20፤እንዲሁም፡በሌላው፡ሰው፡መሠረት፡ላይ፡እንዳልሠራ፡የክርስቶስ፡ስም፡በተጠራበት፡ስፍራ፡ሳይኾን፡ ወንጌልን፡ለመስበክ፡ተጣጣርኹ፤

ቁጥር ፳፩ - ፴፫[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

21፤ነገር፡ግን፦ስለ፡ርሱ፡ያልተወራላቸው፡ያያሉ፥ያልሰሙም፡ያስተውላሉ፡ተብሎ፡እንደ፡ተጻፈ፡ነው። 22፤ስለዚህ፡ደግሞ፡ወደ፡እናንተ፡እንዳልመጣ፡ብዙ፡ጊዜ፡ተከለከልኹ። 23፤አኹን፡ግን፡በዚህ፡አገር፡ስፍራ፡ወደ፡ፊት፡ስለሌለኝ፥ከብዙ፡ዓመትም፡ዠምሬ፡ወደ፡እናንተ፡ልመጣ፡ ናፍቆት፡ስለ፡አለኝ፥ 24፤ወደ፡እስጳንያ፡በኼድኹ፡ጊዜ፡ሳልፍ፡እናንተን፡እንዳይ፥አስቀድሜም፡ጥቂት፡ብጠግባችኹ፡ወደዚያ፡ በጕዞዬ፡እንድትረዱኝ፡ተስፋ፡አደርጋለኹ። 25፤አኹን፡ግን፡ቅዱሳንን፡ለማገልገል፡ወደ፡ኢየሩሳሌም፡እኼዳለኹ። 26፤መቄዶንያና፡አካይያ፡በኢየሩሳሌም፡ቅዱሳን፡መካከል፡ያሉትን፡ድኻዎች፡ይረዱ፡ዘንድ፡ወደዋልና። 27፤ወደዋልና፥የእነርሱም፡ባለዕዳዎች፡ናቸው፤አሕዛብ፡በእነርሱ፡መንፈሳዊ፡ነገርን፡ተካፋዮች፡ከኾኑ፡ በሥጋዊ፡ነገር፡ደግሞ፡ያገለግሏቸው፡ዘንድ፡ይገ፟ባ፟ቸዋልና። 28፤እንግዲህ፡ይህን፡ፈጽሜ፡ይህን፡ፍሬ፡ካተምኹላቸው፡በዃላ፡በእናንተ፡በኩል፡ዐልፌ፡ወደ፡እስጳንያ፡ እኼዳለኹ፤ 29፤ወደ፡እናንተም፡ስመጣ፡በክርስቶስ፡በረከት፡ሙላት፡እንድመጣ፡ዐውቃለኹ። 30፤ወንድሞች፡ሆይ፥ስለ፡እኔ፡ወደ፡እግዚአብሔር፡እየጸለያችኹ፡ከእኔ፡ጋራ፡ትጋደሉ፡ዘንድ፡በጌታችን፡ በኢየሱስ፡ክርስቶስና፡በመንፈስ፡ፍቅር፡እለምናችዃለኹ፤ 31-32፤በእግዚአብሔር፡ፈቃድ፡በደስታ፡ወደ፡እናንተ፡መጥቼ፡ከእናንተ፡ጋራ፡እንዳርፍ፥በይሁዳ፡ካሉት፡ ከማይታዘዙ፡እድን፡ዘንድ፥ለኢየሩሳሌምም፡ያለኝ፡አገልግሎቴ፡ቅዱሳንን፡ደስ፡የሚያሠኝ፡ይኾን፡ዘንድ፡ ጸልዩ። 33፤የሰላምም፡አምላክ፡ከኹላችኹ፡ጋራ፡ይኹን፤አሜን።