ወደ ሮማውያን ፲፮

ከውክፔዲያ
ወደ ሮማውያን ፲፮
በ፫ኛው ክፍለ ዘመን የተጻፈ ወደ ሮማውያን ፲፮:፩፤፬-፯ ፲፮:፲፩-፲፪ በኮዴክስ ካሮሊነስ

ቅዱስ ጳውሎስ
ቅዱስ ጳውሎስ በዕሥር ቤት መልዕክቶቹን ሲጽፍ
አጭር መግለጫ
ፀሐፊ ጳውሎስ
የመጽሐፍ ዐርስት ወደ ሮማውያን
የሚገኘው በአዲስ ኪዳን ፮ኛው መጽሐፍ
መደብ የጳውሎስ መልዕክት


ወደ ሮማውያን በአዲስ ኪዳን የመጀመሪያው መልዕክት ሲሆን ቅዱስ ጳውሎስ በቆሮንጦስ እያለ በ፶ ዎቹ ዓ.ም. የጻፈው መልዕክት ነው። ይህ ምዕራፍ ፲፮ ሲሆን በ፳፯ ንዑስ ክፍሎች ይከፈላል። ጳውሎስ በዚህ መልዕክቱ በመንፈሳዊው ሥራው የተባበሩትን ቅዱሳን ሁሉ ያመሰግናል፣ ምዕመንን ይባርካል ፣ ያበረታታል ...።


ቅዱስ ጳውሎስ ለሮማውያን መልዕክቱን የጻፈበት ምክንያት አይሁዳውያንና ሮማውያን በሰላም አንድላይ በሮም ለብዙ ዘመናት ሲኖሩ ቆይተው ክርስትና በተመሠረተበት ወቅት፣ አይሁዳውያን ክርስቶስ እኛን ነው የመረጠን ለመንግሥቱ እናንተን አይደለም... ሲሊ ሮማውያን ደግሞ እናንተ ሰቀላችሁት እንጂ ምን አደረጋቹህለት... እየተባባሉ እርስበእርሳቸው ጥል ስለፈጠሩ እነሱን ለማስታረቅ ጻፈው።

የጳውሎስ መልዕክት ወደ ሮማውያን ምዕራፍ ፲፮

ቁጥር ፩ - ፲[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

1፤በክንክራኦስ፡ባለች፡ቤተ፡ክርስቲያን፡አገልጋይ፡የምትኾን፡እኅታችንን፡ፌቤንን፡ዐደራ፡ብያችዃለኹ፤ 2፤ለቅዱሳን፡እንደሚገ፟ባ፟፡በጌታ፡ተቀበሏት፥ርሷ፡ለብዙዎች፡ለኔም፡ለራሴ፡ደጋፊ፡ነበረችና፥ከእናንተም፡ በምትፈልገው፡በማናቸውም፡ነገር፡ርዷት። 3፤በክርስቶስ፡ኢየሱስ፡ዐብረውኝ፡ለሚሠሩ፡ለጵርስቅላና፡ለአቂላ፡ሰላምታ፡አቅርቡልኝ፤ 4፤እነርሱም፡ስለ፡ነፍሴ፡ነፍሳቸውን፡ለሞት፡አቀረቡ፥የአሕዛብም፡አብያተ፡ክርስቲያናት፡ዅሉ፡ የሚያመሰግኗቸው፡ናቸው፡እንጂ፡እኔ፡ብቻ፡አይደለኹም፤ 5፤በቤታቸውም፡ላለች፡ቤተ፡ክርስቲያን፡ሰላምታ፡አቅርቡልኝ። ከእስያ፡ለክርስቶስ፡በኵራት፡ለኾነው፡ ለምወደ፟ው፡ለአጤኔጦን፡ሰላምታ፡አቅርቡልኝ። 6፤ስለ፡እናንተ፡ብዙ፡ለደከመች፡ለማርያ፡ሰላምታ፡አቅርቡልኝ። 7፤በሐዋርያት፡መካከል፡ስመ፡ጥሩዎች፡ለኾኑ፥ደግሞም፡ክርስቶስን፡በማመን፡ለቀደሙኝ፥ዐብረውኝም፡ ለታሰሩ፡ለዘመዶቼ፡ለአንዲራኒቆንና፡ለዩልያን፡ሰላምታ፡አቅርቡልኝ። 8፤በጌታ፡ለምወደ፟ው፡ለጵልያጦን፡ሰላምታ፡አቅርቡልኝ። 9፤በክርስቶስ፡ዐብሮን፡ለሚሠራ፡ለኢሩባኖን፡ለምወደ፟ውም፡ለስንጣክን፡ሰላምታ፡አቅርቡልኝ። 10፤በክርስቶስ፡መኾኑ፡ተፈትኖ፡ለተመሰገነው፡ለኤጤሌን፡ሰላምታ፡አቅርቡልኝ። ከአርስጣባሉ፡ቤተ፡ሰዎች፡ ላሉት፡ሰላምታ፡አቅርቡልኝ።

ቁጥር ፲፩ - ፳[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

11፤ለዘመዴ፡ለሄሮድዮና፡ሰላምታ፡አቅርቡልኝ። ከንርቀሱ፡ቤተ፡ሰዎች፡በጌታ፡ላሉት፡ሰላምታ፡አቅርቡልኝ። 12፤በጌታ፡ኾነው፡ለሚደክሙ፡ለፕሮፊሞናና፡ለጢሮፊሞሳ፡ሰላምታ፡አቅርቡልኝ።በጌታ፡እጅግ፡ለደከመች፡
ለተወደደች፡ለጠርሲዳ፡ሰላምታ፡አቅርቡልኝ። 13፤በጌታ፡ኾኖ፡ለታወቀ፡ለሩፎን፡ለኔና፡ለርሱም፡እናት፡ሰላምታ፡አቅርቡልኝ። 14፤ለአስቀሪጦንና፡ለአፍለሶንጳ፡ለሄሮሜንም፡ለጳጥሮባም፡ለሄርማንም፡ከነርሱም፡ጋራ፡ላሉ፡ወንድሞች፡ ሰላምታ፡አቅርቡልኝ። 15፤ለፍሌጎንና፡ለዩልያ፡ለኔርያና፡ለእኅቱም፡ለአልንጦንም፡ከነርሱ፡ጋራ፡ላሉ፡ቅዱሳን፡ዅሉ፡ሰላምታ፡ አቅርቡልኝ። 16፤በተቀደሰ፡አሳሳም፡ርስ፡በርሳችኹ፡ሰላምታ፡ተሰጣጡ። የክርስቶስ፡አብያተ፡ክርስቲያናት፡ዅሉ፡ሰላምታ፡ ያቀርቡላችዃል። 17፤ነገር፡ግን፥ወንድሞች፡ሆይ፥እናንተ፡የተማራችኹትን፡ትምህርት፡የሚቃወሙትን፡መለያየትንና፡ ማሰናከያን፡የሚያደርጉትን፡ሰዎች፡እንድትመለከቱ፡እለምናችዃለኹ፥ከነርሱ፡ዘንድ፡ፈቀቅ፡በሉ፤ 18፤እንዲህ፡ያሉት፡ለገዛ፡ሆዳቸው፡እንጂ፡ለጌታችን፡ለኢየሱስ፡ክርስቶስ፡አይገዙምና፥በመልካምና፡በሚያቈላምጥ፡ንግግርም፡ተንኰል፡የሌለባቸውን፡ሰዎች፡ልብ፡ያታልላሉ። 19፤መታዘዛችኹ፡ለዅሉ፡ተወርቷልና፤እንግዲህ፡በእናንተ፡ደስ፡ይለኛል፤ነገር፡ግን፥ለበጎ፡ነገር፡ ጥበበኛዎች፡ለክፉም፡የዋሆች፡እንድትኾኑ፡እወዳለኹ። 20፤የሰላምም፡አምላክ፡ሰይጣንን፡ከእግራችኹ፡በታች፡ፈጥኖ፡ይቀጠቅጠዋል።የጌታችን፡የኢየሱስ፡ክርስቶስ፡ ጸጋ፡ከእናንተ፡ጋራ፡ይኹን።

ቁጥር ፳ - ፳፯[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

21፤ዐብሮኝ፡የሚሠራ፡ጢሞቴዎስ፡ዘመዶቼም፡ሉቂዮስና፡ኢያሶን፡ሱሲጴጥሮስም፡ሰላምታ፡ያቀርቡላችዃል። 22፤ይህን፡መልእክት፡የጻፍኹ፡እኔ፡ጤርጥዮስ፡በጌታ፡ሰላምታ፡አቀርብላችዃለኹ። 23፤የእኔና፡የቤተ፡ክርስቲያን፡ዅሉ፡አስተናጋጅ፡ጋይዮስ፡ሰላምታ፡ያቀርብላችዃል። የከተማው፡መጋቢ፡ ኤርስጦስ፡ወንድማችንም፡ቁአስጥሮስ፡ሰላምታ፡ያቀርቡላችዃል። 24፤የጌታችን፡የኢየሱስ፡ክርስቶስ፡ጸጋ፡ከኹላችኹ፡ጋራ፡ይኹን፤አሜን። 25-26፤እንግዲህ፡እንደ፡ወንጌሌ፡ስለ፡ኢየሱስ፡ክርስቶስም፡እንደ፡ተሰበከ፥ከዘለዓለም፡ዘመንም፡የተሰወረው፡ አኹን፡ግን፡የታየው፡በነቢያትም፡መጻሕፍት፡የዘለዓለም፡እግዚአብሔር፡እንደ፡አዘዘ፡ለእምነት፡መታዘዝ፡ ይኾን፡ዘንድ፡ለአሕዛብ፡ዅሉ፡የታወቀው፡ምስጢር፡እንደ፡ተገለጠ፡መጠን፡ሊያበረታችኹ፡ለሚችለው፥ 27፤ብቻውን፡ጥበብ፡ላለው፡ለእግዚአብሔር፡በኢየሱስ፡ክርስቶስ፡እስከ፡ዘለዓለም፡ድረስ፡ክብር፡ ይኹን፤አሜን፨

የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ፀጋው፤ ሀብተ ወልድ፤ ሕይወተ ልቦና፣ ገቢረ ተአምራት፣ ወመንክራተ ተስፋ መንግሥተ ሰማያት፣ ስርየተ ኃጢአት ይደረግላቹህ።

በቆሮንጦስ የተጻፈች በከንክርኤስ ያሉ ምዕመናን የምትረዳ በፌቤን እጅ ለሮም ሰዎች ከጳውሎስ የተላከች ክታብ ደረሰች ተፈፀመች።

ወስብሐት ለእግዚአብሔር።