ዋጊኖስ

ከውክፔዲያ
ዘልለው ለመሔድ፦ የማውጫ ቁልፎችፍለጋ
ዋጊኖስ

ዋጊኖስ ወይም የደጋ አባሎ ባለጠጕር፣ ሥሩና ፍሬው ለደም ተቅማጥ መድኀኒት ይኾናል። ቅጠሉም ቀጥቅጦ በውሃ ዘፍዝፎ ብልትንና ዐይንን ፡ እንዳይነካ ተጠንቅቆ ገላን ቢቀቡት ከዕከክ ያድናል ። ሌላ ስሙ ጉፋ ይባላል ። [ነገር ስም] ትንሽ ቍጥቋጦ ዕንጨት የይፋት አባሎ ፍሬው ለቍስል የሚኾን።

የተክሉ ሳይንሳዊ ጸባይ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

ቊጥቋጡ ወይም ዛፉ እስከ ፯ ሜትር ድረስ ይበቅላል።

አስተዳደግ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

በብዛት የሚገኝበት መልክዓ ምድር[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

በከፊል እርጥበት ባላቸው ጫካዎች ወይም በወይና ደጋ በተፈጁ መስኮች ላይ በጣም ተራ ቊጥቋጥ ነው።

የተክሉ ጥቅም[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

የቆዳ ችግሮችንና፣ ቁምጥናን፣ ቁስሎችንም ለማከም፣ የተደቀቁት ቅጠሎች ወይም ዘሮች ከቅቤ ጋር ይቀላቀላል።

የሥሮቹና የፍሬዎቹ የተፈላ ልጥ በተቅማጥወባ ላይ ያክማል።

ቢጫ-ቀይ ፍሬዎቹ በከብት በተለይም በበግ ቢበላ ገዳይ መርዝ እንደ ሆነ ተብሏል።

የተክሉ መረቅ የከብቶችን ማበጥ ለማከም እንደ ጠቀመ ተብሏል።[1]

ዕከክን ለማከም፣ የዋጊኖስና የሽነት ቅጠል እና የጌሾ ዘር ተደቅቆ በቅቤ ለጥፍ ይለጠፋል።

የአባለዘር በሽቶችን ለማከም፣ የዋጊኖስ ዘርና የጤፍ ዘር በውሃ ተጋግሮ በለጥፍ ይለጠፋል።[2]

ፍቼ ወረዳ እንደ ተዘገበ፣ ለእከክ ወይም ለችፌ፣ ቅጠሉ ተደቅቆ ለ፫ ቀን በውሃ ውስጥ ከቆየ በኋላ እንደ መታጠቢያ ይጠቀማል። ለውሻ በሽታ ቅጠሉ በቀጥታ ይበላል፤ ለማስታወክ፣ የደረቀው ቅጠል እንደ ጢስ በአፍንጫ ይናፈሳል።[3]

ዘጌ እንደ ተዘገበ፦ ለ«ቡላድ»፦ የፍሬ ዱቄት በማር ፩ ሳምንት ተቡኮ ይበላል። ለችፌ፦ የልጥና የቅቤ ለጥፍ ይቀባል። ለተቅማጥ፦ የቅጠል ጭማቂ በጧት ይጠጣል። ለ«አህያ ኪንታሮት»፦ የፍሬው ዱቄት በወተት ለ፫ ቀን ይጠጣል። ለ«ሙሽሮ»፦ የሥሩ ዱቄት በማር ይጠጣል።።[4]

ማጣቀሻ[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

  • "Brucea antidysentrica". Encyclopaedia of the History of Science, Technology, and Medicine in Non-Western Cultures፣ Helaine Selin፣ እ.ኤ.አ ፳፻፰ ዓ.ም፣ ገጽ ፰፻፴፯
  1. ^ አማረ ጌታሁን - SOME COMMON MEDICINAL AND POISONOUS PLANTS USED IN ETHIOPIAN FOLK MEDICINE March 1976 እ.ኤ.አ.
  2. ^ በደብረ ሊባኖስ ዙሪያ ያለው ሕዝብ መድሃኒታዊ እጾች እውቀናና ጥቅም 1998 ዓም ከጥላሁን ተክለሃይማኖት፣ ሚሩጸ ጊዳይ፣ ግርማይ መድኅን፣ ያለም መኮነን፣ አዲስ አበባ ዩኒቬርሲቴ፣ አክሊሉ ለማ ተቋም
  3. ^ የፍቼ፣ ኦሮሚያ ባህላዊ መድሃኒት ጥናት 2006 ዓም ከዓቢዩ እኒየው እና ሌሎች፣ ጎንደርና አዲስ አበባ ኡኒቨርሲቲዎች ሥነ ፍጥረት ኮሌጆች
  4. ^ የዘጌ ልሳነ ምድር ባህላዊ መድሃኒት ጥናት 1999 ዓም ከጥላሁን ተክለሃይማኖት፣ ሚሩጸ ጊዳይ፣ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ