ውክፔዲያ:ታሪካዊ ማስታወሻዎች/መስከረም 16
Appearance
መስከረም ፲፮፦ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ እምነት የመስቀል ዋዜማ
- ፲፱፻፳፱ ዓ/ም - የቀድሞው የደቡብ አፍሪቃ ፕሬዚደንት የኔልሰን ማንዴላ የመጀመሪያ ሚስት የነበሩት ዊኒ ማንዴላ ተወለዱ።
- ፲፱፻፵፫ ዓ/ም -የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ በሰጠው ውሳኔ መሠረት ፥ኤርትራ ከኢትዮጵያጋራ ተዋሃደች።
- ፲፱፻፶፫ ዓ/ም - በአሜሪካ የፕሬዚደንትነት ምርጫ ተወዳዳሪዎቹ ጆን ኤፍ ኬኔዲ እና ሪቻርድ ኒክሰን በመጀመሪያው የቴሌቪዥን ሙግት ላይ በሺካጎ ከተማ ተሳተፉ።
- ፲፱፻፶፭ ዓ/ም - የየመን አረባዊ ሪፑብሊክ ተመሠረተ።
- ፲፱፻፷፮ ዓ/ም - በፈረንሳይ እና ብሪታንያ በኅብረት የተሠራው ‘ኮንኮርድ’ የተባለው አየር ዠበብ ለመጀመሪያ ጊዜ የአትላንቲክ ውቅያኖስን በማቋረጥ የፍጥነት ክብረ ወሰን አስመዘገበ።
- ፲፱፻፺፭ ዓ/ም - ‘ጁላ’ (MV Joola) የተባለች የሴኔጋል የንግድ መርከብ ከተፈቀደላት የሰው ጭነት በላይ ሦስት እጥፍ ጭና ስትጓዝ ከጋምቢያ ጠረፍ አካባቢ ላይ ሰምጣ ወደ ፩ሺ ፰፻፷፫ መንገደኞች ሕይወታቸውን አጡ።