ውክፔዲያ:ታሪካዊ ማስታወሻዎች/መስከረም 30
Appearance
- ፮፻፸፫ ዓ/ም - የቀሊፋ ቀዳማዊ ያዚድ ወታደሮች በካርባላ ጦርነት ላይ የነቢዩ ሞሐመድን የልጅ ልጅ የአሊ ልጅ ሁሴንን አንገቱን በመቁረጥ ሰውት። ሺአቶች ዕለቱን በሐዘን ያስቡታል፡፡
- ፲፱፻፶ ዓ/ም - የጋናው የገንዘብ ሚኒስትር ኮምላ አግቤሊ ግብዴማ፣ በዘረኛነት ጥላቻ ምክንያት በዴላዌር ምግብ ቤት መስተንግዶ በመነፈጋቸው፣ የአሜሪካው ፕሬዚደንት ድዋይት አይዘንሃወር ይቅርታ ጠየቋቸው።
- ፲፱፻፶፯ ዓ/ም - ቶክዮ፣ ጃፓን ላይ የተካሄደው የበጋ ኦሊምፒክ ውድድር መክፈቻ ስርዓት ለመጀመሪያ ጊዜ በሳተላይት ተሰራጨ።
- ፲፱፻፸፫ ዓ/ም - ሁለት ትላልቅ የመሬት እንቅጥቅጥ ነውጦች ኤል አስናም በምትባለዋ የሰሜናዊ አልጄሪያ ከተማ ላይ የ፳ ሺህ ሰዎችን ነፍስ ጥፋትና የብዙ ሺህ ሰዎችን የአካል ጉዳት አስከተሉ።
- ፲፱፻፺፰ ዓ/ም - ዩጋንዳን መጀመሪያ ወደነጻነትና በጄኔራል ኢዲ አሚን መፈንቅለ መንግሥት እስከወደቁ ጊዜ ድረስ በቀዳማዊ ጠቅላይ ሚንስትርነት፤ ከአሚን ውድቀት በኋላ ለሁለተኛ ጊዜ በመፈንቅለ መንግሥት እስከተሰደዱ ድረስ ያገለገሉት አፖሎ ሚልተን ኦቦቴ ጆሃንስበርግ ላይ አረፉ::