ውክፔዲያ:ታሪካዊ ማስታወሻዎች/መጋቢት 19
Appearance
- ፲፱፻፳፪ ዓ/ም - የንግድ እና ኢንዱስትሪ ማዕከል እንዲሁም የቱርክ ርዕሰ ከተማ የሆነችው ‘አንጎራ’ ስሟ ተለውጦ አንካራ ስትባል፤ የአገሪቱ አንደኛ ከተማ እና በሮማይስጡ ቄሳር ቁስጥንጢኖስ የተመሠረተችው ቁስጥንጢንያ ወይም ኮንስታንቲኖፕል (Constantinople) ስሟን ቀይራ ኢስታንቡል ተባለች።
- ፲፱፻፷፮ ዓ/ም - የኢትዮጵያ አብዮት ሲፈነዳ ከተሰነዘሩት ዐበያት ሕዝባዊ እሮሮዎች አንዱ በመሳፍንቱ፣ መኳንንቱ፣ ሚኒስትሮችና ባለሥልጣናት ግፈኝነት እና ሙስና ስለነበር ይሄንኑ ጉዳይ እንዲያጠና የተመሠረተው ኮሚሲዮን አባላት ተሠየሙ።
- ፲፱፻፸፮ ዓ/ም - ለ መብራት ኃይል የእግር ኳስ ክለብ፤ የኢትዮጵያ ቡና የእግር ኳስ ክለብ እና የድሬ ዳዋ ባቡር የእግር ኳስ ክለብ እንዲሁም በቅርቡ ደግሞ ለየመን የአል ሳቅር የእግር ኳስ ክለብ ተጫዋቹ ዮርዳኖስ አባይ በዚህ ዕለት ተወለደ