Jump to content
ውክፔዲያ:ታሪካዊ ማስታወሻዎች/መጋቢት 2
መጋቢት ፪
- ፲፰፻፷፰ ዓ/ም - አሌክሳንደር ግራሃም ቤል ለመጀመሪያ ጊዜ በስልክ ረዳቱን አነጋገረ።
- ፲፱፻፵፯ ዓ/ም - ፔኒሲሊንን ያገኘው የብሪታኒያ ተወላጁ አሌክሳንደር ፍሌሚንግ (Sir Alexander Fleming )በልብ ምታት አረፈ።
- ፲፱፻፷፭ ዓ/ም - ኢትዮጵያ እና ሱዳን ድንበራቸውን የሚወስን የጋራ ጉባዔ ለመመሥረት መወሰናቸውን አስታወቁ።
- ፲፱፻፷፭ ዓ/ም - በኢትዮጵያ ርዕሰ ከተማ፣ አራት ኪሎ ላይ በሰላማዊ ሰልፍ የወጡ ተማሪዎችን ፖሊሶች በጢስ ቦምብ እና በዱላ በታተኑ። ተማሪዎቹ የጠቅላይ ሚኒስትር አክሊሉ ሀብተ-ወልድን የአሻንጉልት ምስል አቃጠሉ።
- ፲፱፻፷፮ ዓ/ም - በኢትዮጵያ አብዮት ሽብር የአየር በረራ አስተዳደር (Civil Aviation Administration) ሠራተኞች አድማ ተጀመረ። አድማው እስከ መጋቢት ፳፫ ቀን ድረስ ተካሂዷል።