ውክፔዲያ:ታሪካዊ ማስታወሻዎች/ሚያዝያ 6
Appearance
- ፲፰፻፷ ዓ/ም - የፋሲካ ማግሥት ዕለት መቅደላ አምባ ላይ የዓፄ ቴዎድሮስ ሠራዊት እና በሎርድ ኔፒዬር የተመራው የእንግሊዝ ሠራዊት ጦርነት ገጥመው፣ ድሉ የእንግሊዞች ሆነ። ንጉሠ ነገሥቱ ዓፄ ቴዎድሮስ በእንግሊዞች እጅ ከመውደቅ እራሳቸውን ማጥፋትን መርጠው ሽጉጣቸውን ጠጥተው ሞቱ። ቀብራቸው በመቅደላ መድኀኔ ዓለም ቤተ ክርስቲያን ተከናወነ።
- ፲፱፻፷፮ ዓ/ም - የኢትዮጵያ አብዮት ከተጀመረ በኋላ ንጉሠ ነገሥቱ ቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴየልጅ ልጃቸው ልዑል ዘርዓ ያዕቆብ በወቅቱ በሕክምነ ላይ ለነበሩት መርዕድ አዝማች አስፋ ወሰን ተጠባባቂ አልጋ ወራሽ እንደሆኑ በይፋ አስታወቁ። ይሄም ማብራሪያ የንጉሠ ነገሥቱ የሁለተኛ ወንድ ልጅ የነበሩት የሟቹ የልዑል መኮንን ወንዶች ልጆች በዕድሜ የዘርዓ ያዕቆብ ታላላቆች ቢሆኑም ለዘውዱ ውርስ ቅደም ተከተል ግን ከአስፋ ወሰን ወንድ ልጅ ተከታይ እንደሆኑ አረጋግጧል።