ውክፔዲያ:ታሪካዊ ማስታወሻዎች/ሰኔ 24
Appearance
- ፲፯፻፷፰ ዓ/ም - አባ ፍራንሲስኮ ፓላው የተባለ የካቶሊክ ሚሲዮናዊ እና መቶ-ዓለቃ ሆሴ ዮአኪን ሞራጋ የተባሉ የእስፓኝ አቅኚዎች የዛሬዋ ሳን ፍራንሲስኮ ከተማ በተቆረቆረችበት ሥፍራ ላይ የሚሲዮናዊ ቤት አቆሙ።
- ፲፱፻፴፮ ዓ/ም - አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ በተወለዱ በ፸፪ ዓመታቸው በዚህ ዕለት አርፈው ደብረ ሊባኖስ ተቀበሩ።
- ፲፱፻፶፪ ዓ/ም - ጋና በዚህ ዕለት ሪፑብሊክ ስትሆን ክዋሜ ንክሩማ ፕሬዚደንት ተብለው ንግሥት ኤልሣቤጥ (ዳግማዊት)ን በመተካት የአገሪቱ ርዕሰ-ብሔር ሆኑ።