ውክፔዲያ:ታሪካዊ ማስታወሻዎች/ኅዳር 2
Appearance
- ፲፱፻፲፩ ዓ.ም. - ከአራት ዓመት ጦርነት በኋላ የአንደኛው የዓለም ጦርነት በአንድ በኩል ንምሳ በሌላ በኩል ተቃዋሚዎቿ አባር አገሮች በስምምነትና በፊርማ ውጊያው ከጧቱ አምስት ሰዐት ላይ እንዲያቆም ተስማሙ። ይሄ ድርጊት በየዓመቱ ከጧቱ አምስት ሰዐት ላይ በሁለት ደቂቃ ሕሊናዊ ጸሎት ይከበራል።
- ፲፱፻፶፰ ዓ.ም. - በቀድሞዋ ሰሜን ሮዴዚያ፤ በዛሬይቷ ዚምባብዌ በነጩ ጠቅላይ ሚኒስቴር ኢያን ስሚዝ የሚመራው መንግሥት ከህግ ውጭ አገሪቱን ከብሪታንያ ነጻነት አወጀ።
- ፲፱፻፺፯ ዓ.ም - የፍልስጥኤም ነጻነት ግንባርን እና የፍልስጥኤምን ሕዝብ ከአርባ ዓመት በላይ የመሩት ያሲር አራፋት በተወለዱ በሰባ አምሥት ዓመታቸው በፓሪስ ሆስፒታል አረፉ፡ ወዲያው ማህሙድ አባስ በእሳቸው ምትክ የድርጅቱ መሪ ሆነው ተመረጡ።