ውክፔዲያ:ታሪካዊ ማስታወሻዎች/ኅዳር 22
Appearance
- ፲፱፻፵፰ ዓ.ም. በአላባማ ግዛት ውስጥ በሞንትገመሪ ከተማ፣ ልብስ ሰፊዋ ሮዛ ፓርክስ ወጥቶ እብስ ላይ መቀመጫዋን፣ (በወቅቱ ዘረኛ የከተማዋ ሕግ መሠረት)፣ ለነጭ ሰው አልለቅም በማለቷ የ”ሞንትገመሪ ወጥቶ እብስ አድማ” ተከሰተ።
- ፲፱፻፶፩ ዓ.ም. የፈረንሳይ ቅኝ ግዛት የነበረችው የመካከለኛው አፍሪካ ሪፑብሊክ በዛሬው ዕለት ነጻነቷን ተቀዳጀች።
- ፲፱፻፹፫ ዓ.ም. በእንግሊዝ ባህር ስር በብሪታንያ እና በፈረንሳይ አገሮች መካከል የውስጠ መሬት የባቡር መሥመር የተመሠረተበት ቡርቦራ ከባሕሩ በታች አርባ ሜትር ጥልቀት ላይ ተገናኘ።
- ፲፱፻፺፬ ዓ.ም. የኢትዮጵያ አየር መንገድን የመሠረተው የአሜሪካው ትራንስ ወርልድ አየር መንገድ (Trans World Airlines) ከሰባ ስድስት ዓመታት አገልግሎት በኋላ በአሜሪካ አየር መንገድ (American Airlines) ተገዛ።