ኅዳር ፳፪
ኅዳር ፳፪ ቀን በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፹፪ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በ ዘመነ ሉቃስ ፪፻፹፬ ቀናት በ ዘመነ ዮሐንስ፤ በ ዘመነ ማቴዎስ፤ እና በ ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፪፻፹፫ ቀናት ይቀራሉ።
፲፱፻፫ ዓ/ም - የአዲስ አበባ ከተማ የመጀመሪያው የመድሐኒት መደብር (ፋርማሲ)፣ ዶክቶር ሜራብ በተባለ፣ የጆርጂያ ተወላጅ፤ የጊዮርጊስ ፋርማሲ ወይም የጆርጂያ ፋርማሲ (Pharmacie la Géorgie) በሚል ስም ተሠይሞ በዚህ ዕለት ተከፈተ።
፲፱፻፵፰ ዓ.ም. በአላባማ ግዛት ውስጥ በሞንትገመሪ ከተማ፣ ልብስ ሰፊዋ ሮዛ ፓርክስ ወጥቶ እብስ ላይ መቀመጫዋን፣ (በወቅቱ ዘረኛ የከተማዋ ሕግ መሠረት)፣ ለነጭ ሰው አልለቅም በማለቷ የ”ሞንትገመሪ ወጥቶ እብስ አድማ” ተከሰተ።
፲፱፻፶፩ ዓ.ም. የፈረንሳይ ቅኝ ግዛት የነበረችው የመካከለኛው አፍሪካ ሪፑብሊክ በዛሬው ዕለት ነጻነቷን ተቀዳጀች።
፲፱፻፹፫ ዓ.ም. በእንግሊዝ ባህር ስር በብሪታንያ እና በፈረንሳይ አገሮች መካከል የውስጠ መሬት የባቡር መሥመር የተመሠረተበት ቡርቦራ ከባሕሩ በታች አርባ ሜትር ጥልቀት ላይ ተገናኘ።
፲፱፻፺፬ ዓ.ም. የኢትዮጵያ አየር መንገድን የመሠረተው የአሜሪካው ትራንስ ወርልድ አየር መንገድ (Trans World Airlines) ከሰባ ስድስት ዓመታት አገልግሎት በኋላ በአሜሪካ አየር መንገድ (American Airlines) ተገዛ።
፲፱፻፭ ዓ.ም. በኒው ዮርክ ከተማ በ፲፱፻፺፬ ዓ.ም. በሽብርተኛ አመጸኞት የወደሙትን ‘የዓለም የንግድ ማዕከል” (World Trade Center) የሚባሉትን መንታ ሕንጻዎች የነደፈው ሚኖሩ ያማሳኪ የተባለ ‘ትውልደ ጃፓን’ አሜሪካዊ በሲያትል ከተማ ተወለደ።
፲፱፻፷፮ ዓ.ም. የእስራኤልን ሉዐላዊ አገር የመሠረተውና የአገሪቱ የመጀመሪያው ጠቅላይ ሚኒስቴር ዳዊት ቤን ጉርዮን በሰማንያ ሰባት ዓመቱ አረፈ።
፲፱፻፹፯ ዓ.ም. ታዋቂው ደራሲ ፥ የሥነ ጽሑፍ መምሕር ፥ ገጣሚ እና የተውኔት ጠቢብ የነበረው ዳኛቸው ወርቁ