ኅዳር ፳፪

ከውክፔዲያ
(ከኅዳር 22 የተዛወረ)

ኅዳር ፳፪ ቀን በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፹፪ኛው ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በ ዘመነ ሉቃስ ፪፻፹፬ ቀናት በ ዘመነ ዮሐንስ፤ በ ዘመነ ማቴዎስ፤ እና በ ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፪፻፹፫ ቀናት ይቀራሉ።

ዓቢይ ታሪካዊ ማስታወሻዎች[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

፲፱፻፫ ዓ/ም - የአዲስ አበባ ከተማ የመጀመሪያው የመድሐኒት መደብር (ፋርማሲ)፣ ዶክቶር ሜራብ በተባለ፣ የጆርጂያ ተወላጅ፤ የጊዮርጊስ ፋርማሲ ወይም የጆርጂያ ፋርማሲ (Pharmacie la Géorgie) በሚል ስም ተሠይሞ በዚህ ዕለት ተከፈተ።

፲፱፻፵፰ ዓ.ም. በአላባማ ግዛት ውስጥ በሞንትገመሪ ከተማ፣ ልብስ ሰፊዋ ሮዛ ፓርክስ ወጥቶ እብስ ላይ መቀመጫዋን፣ (በወቅቱ ዘረኛ የከተማዋ ሕግ መሠረት)፣ ለነጭ ሰው አልለቅም በማለቷ የ”ሞንትገመሪ ወጥቶ እብስ አድማ” ተከሰተ።

፲፱፻፶፩ ዓ.ም. የፈረንሳይ ቅኝ ግዛት የነበረችው የመካከለኛው አፍሪካ ሪፑብሊክ በዛሬው ዕለት ነጻነቷን ተቀዳጀች።

፲፱፻፹፫ ዓ.ም. በእንግሊዝ ባህር ስር በብሪታንያ እና በፈረንሳይ አገሮች መካከል የውስጠ መሬት የባቡር መሥመር የተመሠረተበት ቡርቦራ ከባሕሩ በታች አርባ ሜትር ጥልቀት ላይ ተገናኘ።

፲፱፻፺፬ ዓ.ም. የኢትዮጵያ አየር መንገድን የመሠረተው የአሜሪካትራንስ ወርልድ አየር መንገድ (Trans World Airlines) ከሰባ ስድስት ዓመታት አገልግሎት በኋላ በአሜሪካ አየር መንገድ (American Airlines) ተገዛ።

ልደት[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

፲፱፻፭ ዓ.ም. በኒው ዮርክ ከተማ በ፲፱፻፺፬ ዓ.ም. በሽብርተኛ አመጸኞት የወደሙትን ‘የዓለም የንግድ ማዕከል” (World Trade Center) የሚባሉትን መንታ ሕንጻዎች የነደፈው ሚኖሩ ያማሳኪ የተባለ ‘ትውልደ ጃፓን’ አሜሪካዊ በሲያትል ከተማ ተወለደ።


ዕለተ ሞት[ለማስተካከል | ኮድ አርም]

፲፱፻፷፮ ዓ.ም. የእስራኤልን ሉዐላዊ አገር የመሠረተውና የአገሪቱ የመጀመሪያው ጠቅላይ ሚኒስቴር ዳዊት ቤን ጉርዮን በሰማንያ ሰባት ዓመቱ አረፈ።

፲፱፻፹፯ ዓ.ም. ታዋቂው ደራሲ ፥ የሥነ ጽሑፍ መምሕር ፥ ገጣሚ እና የተውኔት ጠቢብ የነበረው ዳኛቸው ወርቁ

ዋቢ ምንጮች[ለማስተካከል | ኮድ አርም]