ውክፔዲያ:ታሪካዊ ማስታወሻዎች/ኅዳር 4
Appearance
- ፲፱፻፷፯ ዓ/ም - በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ የመጨረሻ ዘመን በድርቅ ምክንያት በወሎ የተከሰተውን ዕልቂት መርምሮ ለክስተቱ ኃላፊነት ተጠያቂውን ወገን እንዲያስታውቅ የተሠየመው የምርመራ ሸንጎ የመጀመሪያውን የጥናት ውጤት ይፋ አደረገ።
- ፲፱፻፸፰ ዓ/ም - በሰሜን ኮሎምቢያ ኔቫዶ ዴል ሩይዝ በሚባለው እሳተ ገሞራ ፍንዳታ የተነሣው የጭቃ ጎርፍ ኻያ ሦስት ሺህ ሰዎች ሕይወታቸውን ሲያጡ አርሜሮ የምትባለዋ ከተማ በጎርፉ ተጥለቀለቃ ተቀበረች።
- ፲፱፻፹፩ ዓ/ም - በደብረ ታቦር ከተማ የተወለደውና በፖርትላንድ ስቴት ዩኒቨርሲቲ የሕግ ተማሪ የነበረው ሙሉጌታ ሥራው የሚባል የሃያ ስምንት ዓመት ኢትዮጵያዊ፤ በፖርትላንድ ከተማ በሦስት ፋሺስታዊ ሰዎች በዘረኝነት መነሻ ተቀጥቅጦ ሞተ። ነፍሱን ይማረው!
- ፲፱፻፺፩ ዓ/ም - የአሜሪካው ፕሬዚደንት ዊሊያም ጄፈርሰን ክሊንተን በአመንዝረኛነት ፖላ ጆንስ በተባለች ሴት ተከሰው ለአራት ዓመታት ከተከራከሩ በኋላ ጥፋተኛነታቸውን ሳያምኑ ስምንት መቶ ኃምሳ ሺህ የአሜሪካ ዶላር በመክፈል ክርክሩን አዘጉ።