ኅዳር ፬
Appearance
ኅዳር ፬ ቀን በኢትዮጵያ ዘመን አቆጣጠር የዓመቱ ፷፬ኛው እና የመፀው ወቅት ፴፱ነኛ ቀን ነው። ከዚህ ዕለት በኋላ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ድረስ፣ በ ዘመነ ሉቃስ ፫፻፪ ቀናት በ ዘመነ ዮሐንስ፤ በ ዘመነ ማቴዎስ፤ እና በ ዘመነ ማርቆስ ደግሞ ፫፻፩ ቀናት ይቀራሉ።
- ፲፱፻፷፯ ዓ/ም - በድርቅ ምክንያት የተከሰተውን ዕልቂት መርምሮ ለክስተቱ ኃላፊነት ተጠያቂውን ወገን እንዲያስታውቅ የተሠየመው የምርመራ ሸንጎ የመጀመሪያውን የጥናት ውጤት ይፋ አደረገ።
- ፲፱፻፸፰ ዓ/ም - በሰሜን ኮሎምቢያ ኔቫዶ ዴል ሩይዝ በሚባለው እሳተ ገሞራ ፍንዳታ የተነሣው የጭቃ ጎርፍ ኻያ ሦስት ሺህ ሰዎች ሕይወታቸውን ሲያጡ አርሜሮ የምትባለዋ ከተማ በጎርፉ ተጥለቀለቃ ተቀበረች።
- ፲፱፻፹፩ ዓ/ም - በደብረ ታቦር ከተማ የተወለደውና በፖርትላንድ ስቴት ዩኒቨርሲቲ የሕግ ተማሪ የነበረው ሙሉጌታ ሥራው የሚባል የሃያ ስምንት ዓመት ኢትዮጵያዊ፤ በፖርትላንድ፣ ኦረጎን ከተማ በሦስት ፋሺስታዊ ሰዎች በዘረኝነት መነሻ ተቀጥቅጦ ሞተ። ነፍሱን ይማረው!
- ፲፱፻፺፩ ዓ/ም - የአሜሪካው ፕሬዚደንት ዊሊያም ጄፈርሰን ክሊንተን በአመንዝረኛነት ፖላ ጆንስ በተባለች ሴት ተከሰው ለአራት ዓመታት ከተከራከሩ በኋላ ጥፋተኛነታቸውን ሳያምኑ ስምንት መቶ ኃምሳ ሺህ የአሜሪካ ዶላር በመክፈል ክርክሩን አዘጉ።
- ፲፱፻፳፪ ዓ/ም - የኢትዮጵያ ንጉሠ ነገሥት መንግስት ዋና መላክተኛ በመሆን አገሪቱ መስከረም ፲፯ ቀን ፲፱፻፲፮ ዓ/ም የዓለም መንግሥታት ማኅበር አባል ስትሆን ወደዠኔቭ ልዑካኑን የመሩት ራስ ናደው (አባ ወሎ) በዚህ ዕለት ጎሬ ላይ አረፉ። ሞታቸውን ይፋ ያደረገው አሜሪካዊ ዶክቶር ቨርጂል ዳወርቲ፣ የህልፈታቸው ምክንያት መርዝ ሊሆን እንደሚችል ጠቁሟል። [1]
- {{en]] P.R.O., FCO 371/1829 - ANNUAL REVIEW FOR ETHIOPIA FOR 1974
- ^ VIRGIL F. DOUGHERTY, M.D to ADDISON E SOUTHARD, American Minister; 29th November 1929; RECORDS OF THE DEPARTMENT OF STATE RELATING TO INTERNAL AFFAIRS OF ETHIOPIA (ABYSSINIA) 1910-29
የኢትዮጵያ ወራት | |
---|---|
መስከረም - ጥቅምት - ኅዳር - ታኅሣሥ - ጥር - የካቲት - መጋቢት - ሚያዝያ - ግንቦት - ሰኔ - ሐምሌ - ነሐሴ - ጳጉሜ |