ውክፔዲያ:ታሪካዊ ማስታወሻዎች/ጥቅምት 17
Appearance
- ፲፱፻፱ ዓ.ም. - የወሎው ንጉሥ፤ የልጅ እያሱ አባት ንጉሥ ሚካኤል የልጃቸውን ከሥልጣን መውረድ አዋጅ ተቃውመው በጦር ኃይል ለማክሸፍ ከነሠራዊታቸው ወደ አዲስ አበባ ሲዘምቱ በአልጋ ወራሹ ራስ ተፈሪ መኮንን መሪነት እና በጦር ሚኒስቴሩ በፊታውራሪ ኃብተ ጊዮርጊስ አበጋዝነት የዘመተው ሠራዊት በሰገሌ ጠራ ሜዳ ወረዳ ላይ ገጥመው ከ፭ ሰዐት ውጊያ በኋላ የወሎ ሠራዊት ድል ሆነ። ንጉሡም ተማረኩ።
- ፲፱፻፶፩ ዓ.ም. - በፓኪስታን የአገሪቱ የመጀመሪያው ፕሬዚደንት ኢስካንደር ሚርዛ በ ጄኔራል አዩብ ካን በሚመራ ወታደራዊ መፈንቅለ መንግሥት ከሥልጣን ወረዱ።
- ፲፱፻፷፬ ዓ.ም. - የኮንጎ ዴሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ ስሟን ቀይራ ዛይር ተብላ ተሰየመች።