ውክፔዲያ:ታሪካዊ ማስታወሻዎች/ጥቅምት 9
Appearance
- ፲፱፻፳፰ ዓ/ም -የዓለም መንግሥታት ማኅበር በግፍ ኢትዮጵያን በወረረችው ፋሺስት ኢጣልያ ላይ የዱኛ ማዕቀብ ውሳኔ አስተላለፈ።
- ፲፱፻፷፯ ዓ/ም - የኅብረተ-ሰብአዊት ኢትዮጵያ ጊዜያዊ ወታደራዊ መንግሥት፣ የቀድሞ የንጉሠ ነገሥቱን መንግሥት ባለሥልጣናት የሚዳኝ ወታደራዊ የፍትሕ ሸንጎ መሠረተ።
- ፲፱፻፸፪ ዓ.ም.- ስመ ጥሩው የቡልጋ ተወላጅ አርበኛና የጥንታዊት ኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ማኅበር ሊቀ መንበር፣ ደጃዝማች ኪዳኔ ወልደመድኅን በ ፷፬ ዓመታቸው መስኮብ ላይ አረፉ።
- ፲፱፻፸፱ ዓ/ም - የሞዛምቢክን ፕሬዚደንት ሳሞራ ማሼልን እና አብረዋቸው የሚጓዙ ፴፫ ሰዎችን የጫነው አየር ዠበብ በአገሪቱ ውስጥ ሌቦምቦ ተራራ ጋር ሲጋጭ ተሳፋሪዎቹ ሕይወታቸው አልፏል።