Jump to content

የዓረብኛ አልፋቤት

ከውክፔዲያ
(ከዓረብኛ ፊደል የተዛወረ)

የዓረብኛ አልፋቤት ወይም የዓረብኛ አብጃድ በተለይ አረብኛን ለመጻፍ የተደረጀው አልፋቤት (አብጃድ) ነው። 28 ፊደሎች ሲኖሩት ከቀኝ ወደ ግራ በተያያዘ ጽሕፈት ይጻፋል።

የተደረጀው በስሜን አረብ ከቀደመው ናባታውያን አልፋቤት በ400 ዓም አካባቢ ነበረ። ይህም ናባታውያን አልፋቤት በፈንታው በ200 ዓክልበ. ያህል በዮርዳኖስአራማይስጥ አልፋቤት ደረሰ፤ የአራማይስጥም በ800 ዓክልበ. ግድም በሶርያፊንቄ አልፋቤት ተነሣ።

ተራ «አብጃዲ» ቀደም-ተከተል
غ ظ ض ذ خ ث ت ش ر ق ص ف ع س ن م ل ك ي ط ح ز و هـ د ج ب ا
28 27 26 25 24 23 22 21 20 19 18 17 16 15 14 13 12 11 10 09 08 07 06 05 04 03 02 01

ከአረብኛ በላይ የዓረብኛ ጽሕፈት ብዙ ሌሎችን ልሳናት ለመጻፍ በጥቅም ላይ ውሏል፤ በተለይም አሁን ኡርዱፋርስኛፐንጃብኛውግርኛ በአረብ ጽሕፈት ይጻፋሉ። ለነዚህም ሌሎች ቋንቋዎች ድምጾች ተጨማሪ ልዩ ፊደላት ተለሙ።